2021.12.15 Gruppo di cristiani che pregano insieme davanti la Bibbia

የወጣቶች አገልግሎት

ክርስቶስ ሕያው ነው!

የወጣት አገልግሎት" በልማድ እንደሚከናወነው" በማኅበራዊና ባሕላዊ ለውጦች ተጽእኖ ያርፍበት ነበር በተለመዱት መርሃ ግብሮቻችን ውስጥ ወጣት የሕብረተሰብ ክፍሎች" አብዛኛውን ጊዜ ለሚያስፈልጓቸው ነገሮች" ለችግሮቻቸውና ለጉዳዮቻቸው ምላሽ አያገኙም የቡድኖች ብዛታቸው እድገታቸው እና እንቅስቃሴያቸው በዋነኛነት ከወጣቱ ጋር የመተሳሰሩን ነገር ልንወስደው የምንችለው" አዳዲስ መንገድን የሚያሳየው የመንፈስ ቅዱስ ሥራ እንደሆነ ነው ቢሆንም" እንዲህ ያሉ ቡድኖች በቤተ ክርሰትያን አጠቃላይ የሐዋርያዊ እንክብካቤ ውስጥ እንደሚሳተፉ" እንዲሁም ደግሞ በመኻከላቸው ይበልጥ ሕብረት እና የክንዋኔዎቻቸው ትስስር አስፈላጊ እንደሚሆን ማየት መልካም ይሆናል ምንም እንኳን ወጣቶችን መቅረብ አዳጋች ቢሆንም" ሁለት ነገሮች ግን ግልጽ እየሆኑ መጥተዋል: ስብከተ ወንጌልን ለእነርሱ ለማዳረስ ጠቅላላ ማኅበረሰቡ መሳተፍ እንዳለበትና በሐዋርያዊ ተልዕኮ ወጣቶች በአስቸኳይ የመግባታቸው አስፈላጊነት እየታየ ነው።

ሲኖዳዊ የሆነ ሐዋርያዊ እንክብካቤ

ወጣት የሕብረተሰብ ክፍሎች ራሳቸው የወጣት አገልግሎት ወኪል መሆናቸውን በግልጽ መናገር እፈልጋለሁ በእርግጥም" ሊረዱና እና ሊመሩም ያስፈልጋል" ነገር ግን በዚያውም ልክ በአዳዲስ አቀራረቦች" በፈጠራና" እንዲያበለጽጉትም ነጻነት ሊኖራቸው ይገባል ስለዚህ አሁን የወጣት አገልግሎት ማኑዋል ዓይነትን ሐሳብ ለማቅረብ ሙከራ አላደርግም ይበልጥ ግድ የሚለኝ ወጣት የሕብረተሰብ ክፍሎች" በራሳቸው ቋንቋ የሚናገሩ የሌሎች ወጣቶችን ችግር ለማየት" የራሳቸው እይታ" የፈጠራ ችሎታ" እውቀት እንዲኖራቸው ለማገዝ ነው።

ወጣቶች አዳዲስ ስልቶችን እና ዘዴዎችን እንድናይ ያግዙናል ለምሳሌ" ዐዋቂዎች ሁሉ ነገር በትክክል መታቀዱ" ስብሰባዎች እና የሚወሰኑ ጊዜያት ጉዳይ ሲያስጨንቋቸው; ብዙ ወጣቶች ግን የዚህ አይነት ሐዋርያዊ አቀራረብ ምንም ያህል አያሳስባቸውም የወጣት አገልግሎት ይበልጥ የሚለወጡ ነገሮችን ለመለወጥ የተመቻቸ መሆን አለበት - ወጣቶችን ዝግጅቶች ሲኖሩ መጋበዝ ወይም ለመማር ብቻ ሳይሆን ለመነጋገር" በዓል ለማክበር" ለመዘሙር" እውነተኛ ታሪኮችን ለማዳመጥ" ከሕያው እግዚአብሔር ጋር ስለተደረገ ግንኙነት ተሞክሮን በሚያካፍሉበት ሁኔታ እንዲገናኙ ማድረግ ይበልጥ ጠቃሚነት ይኖረዋል።

በዚያውም ልክ" እሴቶቻቸውን ያሳዩ ልምዶችን ይበልጥ ልብ ልንላቸው ይገባል - ስልቶቹ" ቋንቋና በእርግጥም ወጣቶች ወደ ክርስቶስና ወደ ቤተ ክርስትያን ለማምጣት አመርቂ የሆኑ ዓላማዎችን ትኩረት መስጠት ከየት እንደሚመጡ" ምን ምልክት እንደተቀበሉ" 'ወግ አጥባቂ' ይሁኑ" 'ልዝብ' ወይም 'ባሕላዊ' ወይም 'ተራማጅ' ምንም ለውጥ የለውም ዋነኛው ነገር መልካም ፍሬ ያፈራው እና የወንጌልን ደስታ በአመርቂ ሁኔታ ያስተላለፈውን ነገር ሁሉ እንድንጠቀምበት ነው።

206. የወጣት አገልግሎት ሲኖዳዊ_ሸንጎአዊ መሆን አለበት: 'አብሮ መጓዝን' “መንፈስ ለእያንዳንዱ የቤተ ክርሰትያን አባል ላይ እንደ ጥሪው" ሚናው" ኀላፊነትን በመጋራት... በመንፈስ ቅዱስ ቀስቃሽነት" አሳታፊ ወደሆነ ቤተክርስትያን " የራሱ የሆነውን የሚያደንቅ" ታማኝ ምዕመናን" ወጣት ወንዶችንና ሴቶችንም ጨምሮ" የተቀደሱ ሰዎችን" እንዲሁም ቡድኖችን" ማኅበራትን እና የንቅናቄዎችን አስተዋጽኦ በምሥጋና መቀበል ማንም ሊገለል ወይም ራሱን ሊያገልል አይገባም”።

በዚህ መንገድ" አንዱ ከሌላው በመማር" ተጨባጭ አስደናቂ ባለ ብዙ ገጽታ የክርስቶስ ቤተ ክርስትያን መሆን እንዳለባት እንመሰክራለን ወጣቱን ትውልድ የምትማርክ መሆን አለባት" ምክንያቱም አንድነቷ ትልቅ ሳይሆን" መንፈስ ቅዱስ ያለማቋረጥ የተለያዩ ስጦታዎችን የሚያፈስስባት እንደገና የሚያድሳት እና ከእጦትዋም እንደገና የሚያነሣት ናት።

በሲኖዱ" የወጣት አገልግሎትን ለማደስ ምክንያቱም አሁን ካለው የወጣት ባሕል ጋር ንግግር ለመፍጠር የማያስችል በመሆኑ ውጤታማ ካልሆኑ አቀራረቦች ነጻ ለማውጣት ብዙ ተጨባጭ እቅዶች ቀርበዋል በዚህ ስፍራ ሁሉንም መዘርዘር አልችልም አብዛኛዎቹ የሲኖዱ የመጨረሻ ሰነድ ውስጥ ሊገኙ ይችላሉ።

ምንጭ፡ “ክርስቶስ ሕያው ነው”! በሚል አርዕስት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ይፋ ካደረጉት ድኅረ ሲኖዶሳዊ ሐዋርያዊ ምክር ከአንቀጽ 202-209 ላይ የተወሰደ።

አዘጋጅ እና አቅራቢ ባራና በርገኔ ቫቲካን

22 December 2023, 13:40