ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ የስደተኞችን ሕይወት መጠበቅ እና ማዳን ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል አሉ።
የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በጄኔቫ እየተካሄደ ላለው ዓለም አቀፍ የስደተኞች መድረክ ባስተላለፉት መልእክት የስደተኞችን ችግር መፍታት የጋራ ኃላፊነት መሆኑን ጠቁመው፣ አብሮነትን፣ አቀባበልን እና ትብብርን የሚናገሩ ተከታታይ የተስፋ ምልክቶችን በመልእክታቸው ላይ አመልክተዋል።
የቫቲካን ዋና ጸሐፊ በሆኑት ብጹዕ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን የተነበበው መልእክታቸው በዓለም ትልቁ የስደተኞች ጉዳይ ላይ የተደረገ ዓለም አቀፍ ስብሰባ ነበር። በአለም አቀፍ የስደተኞች ጥቅል ሕግ ውስጥ የተቀመጡትን አላማዎች ተግባራዊ እንዲሆኑ የተነደፈ መድረክ ነው።
የተስፋ ምልክቶች
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ስደተኞችን ለመቀበል ድንበሮች እና ልባቸው ክፍት የሆኑ አገሮችን እና አስተናጋጅ ማህበረሰቦችን በመዘርዘር በየቀኑ የሚያጋጥሟቸውን የተስፋ ምልክቶች ጠቅሰዋል። በባህር ላይ ህይወትን ለማዳን በቀጣይነት የነፍስ አድን ሥራ የሚሰሩትን እና በስደተኞች መቀበያ ማዕከላት ውስጥ የሚደርገውን ትብብር እና መስተንግዶ ቅዱስነታቸው አድንቀዋል። በተጨማሪም “ሕይወታቸውን ለመለወጥ ለሚንቀሳቀሱ ማኅበረሰቦች የበኩላቸውን አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ስደተኞችን ተስፋ አጽንቷል። እናም እያንዳንዳችን አሁንም ትብብርን የአለም አቀፍ ችግሮች ቁልፍ መፍትሄ አድርገን የምንቆጥረው በእዚህ ምክንያት እንደ ሆነ ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው አስረድተዋል።
ነፃ ምርጫ
እያንዳንዱ ሰው የመሰደድ ወይም ያለመሰደድ መብትን በመልዕክታቸው ደጋግሞ በመጥቀስ “ሁሉም ሰው በአገሩ የተከበረ ሕይወት የመምራት ዕድል ሊኖረው ይገባል” ብለዋል።
በዚህ ረገድ “አንድ የተወሰነ ማሽቆልቆል” ብሎ የሚመለከተውን ነገር በመቃወም “በዛሬው እለት ወደ 114 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች በግዳጅ እየተፈናቀሉ ነው፣ ብዙዎቹም በአገር ውስጥ በግጭት፣ በአመጽ እና በስደት፣ በሃይማኖታዊ እምነቶች እንዲሁም በየአየር ንብረት ለውጥ ውጤቶች” ምክንያት እየተፈናቀሉ ይገኛሉ ያሉስ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በዓለም ዙሪያ "114 ሚሊዮን ሰዎች በግዳጅ ተፈናቅለዋል" ሲሉ በመልእክታቸው ገልጸዋል።
በቂ ያልሆነ ዓለም አቀፍ ምላሾች
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የስደት ምክንያቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተወሳሰቡ እየጨመሩ መጥተዋል፣ “ነገር ግን የእኛ ምላሽ እነዚህን አዳዲስ እና አንገብጋቢ ፈተናዎች በበቂ ሁኔታ አልቀረፈም” ሲሉ በመልእክታቸው ያስተላለፉት ቅዱስነታቸው "በዚህም ምክንያት ከለላ እየፈለግን ወይም ከተስፋ ቢስ ተስፋ እየሸሸን በየብስ እና በባህር ላይ ለጠፋው ስፍር ቁጥር የሌለው ህይወት ማዘናችንን እንቀጥላለን" ብሏል።
የሰውን ህይወት መጠበቅ እና ማዳን
“የሰውን ሕይወት መጠበቅና ማዳን ከምንም በላይ ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል” ሲሉ ቅዱስ አባታችን ፅኑ እምነታቸውን ደግመው ገልጸዋል።
በተትረፈረፈ ዜና እና ስታቲስቲክስ በተጨናነቀ ዓለም ውስጥ “ከነዚህ ቁጥሮች በስተጀርባ የሰው ልጆች ፊቶች እንዳሉ እንዘነጋለን፣ እያንዳንዳቸው የራሳቸው ታሪክ እና ስቃይ አላቸው” ሲሉ ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው የገለጹ ሲሆን “እያንዳንዱ ቁጥር እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን ወንድሞቻችንን እና እህቶቻችንን ይወክላል” ብሏል።
ለአደጋ በምያጋልጥ ሁኔታ ስደተኞችን ወደ አገር ቤት እንዲመለሱ ማድረግ
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ “በአስተማማኝና በፈቃደኝነት የሚሰደዱ ሰዎችን ወደ አገራቸው የመመለሱ መርህ በጥብቅ መከተል ያስፈልጋል” ሲሉ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በመልእክታቸው የተናገሩ ሲሆን “ማንም ሰው ከባድ የሰብአዊ መብት ረገጣ አልፎ ተርፎም ሞት ሊደርስበት ወደሚችልበት አገር መመለስ የለበትም” ብለዋል።
በተቃራኒው "ሁላችንም በራችንን የሚያንኳኩትን ለመቀበል፣ ለማስተዋወቅ፣ ለመሸኘት እና ለማዋሃድ ዝግጁ እና ክፍት የሆኑ ማህበረሰቦችን ለመፍጠር ተጠርተናል" በማለት በመልእክታቸው ላይ ያስፈሩት ቅዱስነታቸው ለዚህም “ስደተኛ መሆን ደረጃን መስጠት ብቻ ሳይሆን እግዚአብሄር የሰጠንን የሰው ልጅ ክብር እውቅና መስጠት እንደሆነ መቀበል አለብን” ብለዋል።
አክለውም “የአንድ ሰብዓዊ ቤተሰብ አባላት እንደመሆናችን መጠን እያንዳንዱ ግለሰብ ቤቴ ብሎ የሚጠራው ቦታ ሊኖረው ይገባዋል። ይህም ማለት ምግብ ማግኘት፣ የጤና እንክብካቤ፣ ትምህርት ማግኘት እና የተከበረ ሥራ ማግኘት ማለት ነው” ብለዋል ።
“የአንድ ሰብዓዊ ቤተሰብ አባላት እንደመሆናችን መጠን እያንዳንዱ ግለሰብ ቤቴ ብሎ የሚጠራው ቦታ እንዲኖረው ይገባዋል። እሱም አንድ ሰው “የሚረዳበት እና የሚካተትበት፣ የሚወደድበት እና የሚንከባከበው” ቦታ ያለው፣ የሚሳተፍበት እና የሚያዋጣበት ቦታ አለው ማለት ነው” በማለት ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው ተናግረዋል።
መብቶች እና ግዴታዎች ያላቸው ሰዎች
ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ስደተኞች “መብት እና ግዴታ ያላቸው ሰዎች እንጂ የእርዳታ ዕቃዎች አይደሉም” የሚለውን እውነታ በመደገፍ “አዲስ ጅምር መከልከል እንደሌለባቸው” እና ችሎታቸውን እና ክህሎቶቻቸውን ለምያስተናግዳቸው አገር ማህበረሰቦች እንደ ግብዓት እንዲጠቀሙ ሊፈቀድላቸው ይገባል ብለዋል ።
አክለውም "ስደተኞችን እንደ የመፍትሄው አካል በማካተት ብቻ እንደ ሰው ማደግ እና በሚኖሩበት ቦታ ዘራቸውን መዝራት ይችላሉ" ብለዋል።
ወሳኝ ጊዜ
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ “በወሳኝ ጊዜ ላይ እንደቆምን እና “የሰው ልጅ እና የወንድማማችነት ባህል ወይም ከግዴለሽነት ባህል” አንዱን እንድንመርጥ ተጠርተናል ብለዋል ።
“የሥልጣኔ መሰበር አደጋን ለመከላከል ታሪክ የኅሊና ምርመራ ማድረግ እንድንችል ታሪክ እየፈተነን ስለሆነ ውሳኔው በጣም አስፈላጊ ነው” ሲሉ ይህ የዓለም አቀፍ ሸንጎ ከኛ ጋር የሚስማማ የባለብዙ ወገንነት ምሳሌ እንደሚሆን ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
"በዚህም ይህ መድረክ እ.አ.አ የ1951 ዓ.ም የስደተኞች ስምምነት 'መንፈስ' እና 'ራዕይ' እንደገና እንዲያንሰራራ ለማድረግ እንደሚሰራ ልባዊ ተስፋዬ ነው፣ "በተመሳሳይ ጊዜ አጋጣሚውን ተጠቅሞ የወንድማማችነት መርሆዎችን በማረጋገጥ፣ በትብብር እና ሸክም መጋራት መተባበር እደሚፈጥር ተስፋ አደርጋለሁ፣ "የተጠራነው የሰው ልጅን እና ወንድማማችነትን ወይም ደግሞ አሉታዊ የሆነውን የግዴለሽነትን ባህል እንድንመርጥ ነው" ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው መልእክታቸውን አጠናቀዋል።