ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ በዓለም የሰላም ቀን መልእክት ላይ AI ለሰላም ያለውን ስጋት በማንሳት አስጠንቅቀዋል!
የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን
አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ሁልጊዜም “ሰላምና የጋራ ጥቅምን ለማስከበር፣ የግለሰቦችን እና ማህበረሰቦችን ሁለንተናዊ ልማትን ለማስከበር” በሕግ መመራት አለባቸው ያሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በእዚሁ ለዓለም ሰላም ቀን ባስተላለፉት ዓመታዊ መልእክት፣ የዓለም መሪዎች የሰው ሰራሽ የማሰብ ችሎታን በማዳበር ረገድ እድገት “በመጨረሻም ለሰው ልጆች ወንድማማችነት እና ሰላም የሚያገለግል” መሆኑን እንዲያረጋግጡ አሳስበዋል።
‘አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ እና ሰላም’ በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው መልእክት በቫቲካን ይፋ የሆነው እ.አ.አ ሐሙስ እለት ታኅሳስ 14/2023 ዓ.ም 57ኛው የዓለም የሰላም ቀን እ.አ.አ ጥር 1/2024 ከመከበሩ በፊት ከሁለት ሳምንታት ይፋ ይሆነ መልእክት ነው።
የቴክኖ-ሳይንሳዊ እድገቶች ተፈጥሯዊ አሻሚነት
በዚህ ውስጥ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ትኩረታቸውን ወደ “ሥነ ምግባራዊ ልኬት” ያዞሩ ሲሆን ስለእነዚህ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች የሰው ልጅን በሁሉም የሕይወት ዘርፎች ላይ ለውጥ እያደረጉ ነው፣ ይህም በሳይንስና በቴክኖሎጂ ውስጥ በማንኛውም እድገት ውስጥ ያለውን አሻሚነት በማጉላት ነው።
በአንድ በኩል “በሰው ልጅ ማኅበረሰብ ውስጥ የላቀ ሥርዓት እንዲሰፍን፣ የበለጠ ወንድማማችነት እና ነፃነት እንዲሰፍን አስተዋጽኦ ካበረከተ የሰው ልጅን ወደ ተሻለ ደረጃ እና ወደ ዓለም ለውጥ ሊያመራ ይችላል” ብሏል።
በሌላ በኩል የቴክኖ ሳይንሳዊ እድገቶች በተለይም በዲጂታል ሉል ወይም መዘውር ውስጥ “በሰዎች እጅ ብዙ አማራጮችን እያስቀመጡ ነው፣ ከእነዚህም መካከል አንዳንዶቹ ሕልውናችንን አደጋ ላይ የሚጥሉና የጋራ ቤታችንን አደጋ ላይ የሚጥሉ ናቸው” ሲሉ ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው አስፍረዋል።
የትኛውም የቴክኖሎጂ ፈጠራ “ገለልተኛ” አይደለም
መልእክቱ የትኛውም ሳይንሳዊ ምርምር እና የቴክኖሎጂ ፈጠራ “ገለልተኛ” እንዳልሆነ ያስታውሳል፡- “እንደ ሙሉ ሰው እንቅስቃሴዎች፣ የሚከተሏቸው አቅጣጫዎች በማንኛውም እድሜ ውስጥ በግል፣ በማህበራዊ እና በባህላዊ እሴቶች የተቀመጡ ምርጫዎችን ያንፀባርቃሉ። ስለሚያስገኙት ውጤትም ተመሳሳይ ነገር ሊባል ይገባል፡- በትክክል የሰው ልጆች በዙሪያችን ወዳለው ዓለም የመቅረብ መንገድ ፍሬ እንደመሆናቸው መጠን፣ የኋለኛው ደግሞ ሁልጊዜ ሥነ ምግባራዊ ልኬት አላቸው፣ ሙከራቸውን በነደፉ እና ምርታቸውን ወደ አቅጣጫ በሚመሩ ሰዎች ከሚደረጉ ውሳኔዎች ጋር እና ልዩ ዓላማዎች ጋር በጥብቅ የተቆራኘ ነው።
ይህ በ AI (ሰውስ ሰራሽ የማሰብ ችሎታ) ላይም ይሠራል ምክንያቱም "የማንኛውም ሰው ሰራሽ የማሰብ ችሎታ መሳሪያ - ምንም እንኳን መሰረታዊ ቴክኖሎጂው ምንም ይሁን ምን - በቴክኒካዊ ዲዛይኑ ላይ ብቻ ሳይሆን በባለቤቶቹ እና በገንቢዎቹ ዓላማዎች እና ፍላጎቶች ላይ እንዲሁም በእሱ ሁኔታዎች ላይ የተመሰረተ ቅጥር ነው የሚደርገው” ብለዋል በመልእክታቸው።
ስለዚህ “የእድገቱ አስተዋጾ ለሰው ልጅ የወደፊት ዕጣ ፈንታ እና በህዝቦች መካከል ሰላም እንዲሰፍን ጠቃሚ አስተዋጽኦ ያደርጋል ብለን መገመት አንችልም። ያ አወንታዊ ውጤት የሚገኘው እራሳችንን በኃላፊነት ስሜት ለመስራት እና እንደ ‘ማካተት፣ ግልጽነት፣ ደህንነት፣ ፍትሃዊነት፣ ግላዊነት እና አስተማማኝነት’ ያሉ የሰው ልጅ እሴቶችን ካከበርን ብቻ ነው” ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በመልእክታቸው ጽፈዋል።
የስነምግባር ጉዳዮች
በመሆኑም “በዚህ ዘርፍ የሚነሱትን የሥነ ምግባር ጉዳዮች በመመርመር እና አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የሚቀጥሩትን ወይም የሚጎዱትን ሰዎች መብት የማስጠበቅ ኃላፊነት ያለባቸው አካላት ማቋቋም” ያስፈልጋል።
"ዓይናችንን የማስፋት እና የቴክኖ-ሳይንሳዊ ምርምርን ወደ ሰላም እና የጋራ ጥቅም ለማስከበር የግለሰቦችን እና ማህበረሰቦችን ሁለንተናዊ እድገትን የማቅረብ ግዴታ አለብን" ሲሉ ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው ላይ አስፍረዋል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ "የሁሉም የሰው ልጅ የህይወት ጥራት መሻሻልን የማያመጣ የቴክኖሎጂ እድገቶች፣ ነገር ግን በተቃራኒው ኢእኩልነትን እና ግጭቶችን የሚያባብሱ፣ እንደ እውነተኛ እድገት ሊቆጠሩ አይችሉም" ብለዋል።
መልእክታቸው በ AI የሚነሱትን በርካታ ተግዳሮቶችን አጉልቶ ያሳያሉ፣ እነሱም “(ስነ-ሰብዕ) አንትሮፖሎጂካል፣ ትምህርታዊ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ” ናቸው ሲሉ ተናግረዋል።
ለዴሞክራሲያዊ ማህበረሰቦች ስጋት
አንዳንድ መሣሪያዎች ወጥነት ያላቸውን ጽሑፎች የማምረት ችሎታ ለምሳሌ፣ “ለአስተማማኝነታቸው ዋስትና አይሆንም። ይህ ደግሞ “የሐሰት ዜናዎችን በሚያሰራጩ የመገናኛ ብዙኃን ላይ እምነት ማጣት እንዲፈጠር አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ በሐሰት መረጃ ዘመቻ ላይ ሲሰማሩ ከባድ ችግር ይፈጥራል” ብለዋል ጳጳሱ።
እነዚህን ቴክኖሎጂዎች አላግባብ መጠቀም ሌሎች አሉታዊ ውጤቶችን ሊያስከትል ይችላል "እንደ መድልዎ፣ በምርጫ ውስጥ ጣልቃ መግባት፣ በማህበረሰብ የግል ሕይወት ላይ የሚደርገው ክትትል መጨመር፣ ዲጂታል ማግለል እና የግድየለኝነት ፍልስፍና መባባስ ከህብረተሰቡ ጋር ያለው የግንኙነት ልዩነት እየጨመረ ይሄዳል" እነዚህ ሁሉ ለዓለም ሰላም ጠንቅ ናቸው ሲሉ ቅዱስነታቸው ለዓለም የሰላም ቀን ባስተላለፉት መልእክት ገልጸዋል።
በመቀጠልም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በዲሞክራሲያዊ ማህበረሰቦች እና በሰላም አብሮ መኖር ከ AI እና ያልተገደበ የሰው ኃይል አምልኮ ሥርዓት ጋር አብሮ መኖር ሊያስከትል የሚችለውን አደጋ አስጠንቅቀዋል፡- “በቴክኖሎጂ አማካኝነት ማንኛውንም ገደብ ለማለፍ ሃሳብ በማቅረብ፣ ሁሉንም ነገር ለመቆጣጠር ባለን ጥልቅ ፍላጎት የተነሳ በራሳችን ላይ ያለንን ቁጥጥርን እናጣለን” ብለዋል።
አልጎሪዝም (ስልተ ቀመር) የሰብአዊ መብቶችን እንዴት እንደምንረዳ መወሰን የለበትም
አድልዎ፣ ማጭበርበር ወይም ማህበራዊ ቁጥጥርን ጨምሮ በ AI የሚነሱትን “የሚነድ” የስነ-ምግባር ጉዳዮች ላይ አጥብቆ ተናግሯል፡- “ግለሰቦችን በሚከፋፍሉ አውቶማቲክ ሂደቶች ላይ መታመን፣ ለምሳሌ በሰፊው የክትትል አጠቃቀም ወይም የማህበራዊ ክብር ስርዓቶችን መቀበልም እንዲሁ ሊሆን ይችላል። በዜጎች መካከል የደረጃ አሰጣጥን በማቋቋም በማህበራዊ ትስስር ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ ይኖረዋል” ሲሉ ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው ገልጸዋል።
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳቱ "የሰብአዊ መብቶችን እንዴት እንደምንረዳ ለመወሰን ስልተ ቀመሮች መፍቀድ የለባቸውም" ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ አፅንዖት ሰጥተዋል፣ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች በስራ ቦታ ላይ የሚያሳድሩትን ተፅእኖ አጉልተው ተናግረዋል።
አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የጦር መሳሪያ
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በተለይ ገዳይ ራስ ገዝ የጦር መሣሪያ ስርዓቶች በእንግሊዘኛው “Lethal Autonomous Weapon Systems” (LAWS) በመጥቀስ የተራቀቁ የጦር መሣሪያዎችን በአሸባሪዎች እጅ የመዝለቅ አደጋ ላይ ትኩረት በመስጣት “አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ መሣሪያን ስለማዘጋጀት” ያሳስበናል ብለዋል።
"በጣም የላቁ የቴክኖሎጂ መተግበሪያዎች ግጭቶችን በአመጽ ለመፍታት ለማመቻቸት ሳይሆን ለሰላም መንገድ የሚጠርጉ መሆን አለባቸው" ብለዋል ቅዱስነታቸው ለዓለም የሰላም ቀን ባስተላለፉት መልእክት።
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በአዎንታዊ ጎኑ እንደተናገሩት አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ “በግብርና፣ በትምህርት እና በባህል ላይ ያሉ ጠቃሚ አዳዲስ ፈጠራዎችን፣ መላው አገራትን እና ህዝቦች የተሻሻለ የኑሮ ደረጃ፣ እንዲሁም የሰው ልጅ ወንድማማችነት እድገትን በማስተዋወቅ የሰው ልጅን ሁለንተናዊ እድገት ለማሳደግ ያስችላል። እናም ማህበራዊ ጓደኝነት" ሊፈጥር ይቻላል ሲሉ ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው ላይ አስፍረዋል።
በትምህርት ረገድ ያለው ተግዳሮት
መልእክቱ በአዲሶቹ ትውልዶች ላይ “በቴክኖሎጂ በተስፋፋው የባህል አካባቢዎች” በትምህርት ላይ የሚያጋጥሙትን ፈተናዎች አጉልቶ ያሳያል።
በዚህ ረገድ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ወጣቶችን “በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ” አጠቃቀም ረገድ በአስቸኳይ ማስተማር እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል። ይህ ትምህርት “ከሁሉም በላይ ወሳኝ አስተሳሰብን በማስተዋወቅ ላይ ያተኮረ መሆን አለበት” ብሏል።
AIን ለመቆጣጠር ዓለም አቀፍ ስምምነት ያስፈልጋል
ስለዚህ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ እድገትና አጠቃቀምን የሚቆጣጠር አስገዳጅ ዓለም አቀፍ ስምምነትን በጋራ እንዲፀድቅ አሳስበዋል። በውስጥ አጠቃቀሙን ለመቆጣጠር ዓለም አቀፍ ድርጅቶች የባለብዙ ወገን ስምምነቶችን በመድረስ እና አተገባበርን እና አፈጻጸማቸውን በማስተባበር ወሳኝ ሚና ሊጫወቱ ይችላሉ።
መልእክቱ “በአዲሱ ዓመት መጀመሪያ ላይ ጸሎቴ ነው” ሲል መልእክቱ ይደመድማል ፣ “የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ዓይነቶች በፍጥነት ማደግ በአሁኑ ጊዜ በዓለማችን ላይ የሚታየውን የእኩልነት እና የፍትህ መጓደል ጉዳዮችን በአዎንታዊ መልክ እንዲቀይር እና እንደሚያሳድግ በተጨማሪም ጦርነቶችን እንዲያስቆም ይርዳ። እንዲሁም ግጭቶች፣ እንዲሁም በሰብዓዊ ቤተሰባችን ላይ የሚደርሰውን ብዙ ዓይነት ስቃዮችን ያስወግድ” ዘንድ ጸሎቴ ነው ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው መልእክታቸውን አጠናቀዋል።