ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የጤንነቴ ሁኔታ እየተሻሻለ ነው፣ ጵጵስናዬን የመልቀቅ ዕቅድ የለኝም ማለታቸው ተገለጸ!
የእዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን
ብዙም ውሳኔ ማድረግ ብቻ ሳይሆን አብዮታዊ በሚመስል መልኩ ለቅድስት ድንግል ማርያም ቃል ገብቻለሁኝ፣ ከሞትኩኝ ቡኋላ “በቅድስት ማርያም ሜጀር ባዚሊካ ውስጥ መቀበር እፈልጋለሁ። ቦታው አስቀድሞ ተዘጋጅቷል" ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ተናግረዋል።
የ87 አመቱ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ዓላማቸውን ለሜክሲኮ ብሮድካስቲንግ ኤን+ ሲገልጹ፣ የሊቃነ ጳጳሳትን የቀብር ሥነ ሥርዓት ለማቃለል እንደሚሠሩም አስረድተዋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ምንም እንኳን ስለ ሞት ቢያስቡም - በከፊል በእርጅና ምክንያት "እንደሚመጣ" የገለጹ ሲሆን ከርዕሰ ሊቃነ ጵጵስናቸው ግን በፈቃዳቸው የመልቀቅ ሀሳብ በእቅዳቸው ውስጥ ፈጽሞ እንደ ሌለ አክለው ገልጸዋል።
በተቃራኒው ቅዱስ አባታችን እ.አ.አ በ 2024 ወደ ቤልጂየም ለመጓዝ ፍላጎት እንዳላቸው የገለጹ ሲሆን በተጨማሪም ወደ ፖሊኔዥያ እና አገራቸው አርጀንቲና ለመሄድ በመጠባበቅ ላይ መሆናቸውን ቅዱስነታቸው ገልጸዋል።
በቅድስት ማርያም ሜጄር ቤተክርስቲያን ውስጥ የመቀበር ፍላጎት
ቃለ ምልልሱን ያደረጉት በታዋቂው ጋዜጠኛ ቫለንቲና አላዝራኪ ጋር ሲሆን አገሯ ሜክሲኮ “እናቷ” የሆነችውን የጓዳሉፔ እመቤታችንን የምታከብርበት ዕለት ነበር። በቃለ ምልልሱ ወቅት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ያላቸውን “ታላቅ ፍቅር” ደጋግመው ገልጸዋል። ለእዚህም ነው በሮም ከተማ ውስጥ በሚገኘው በቅድስት ማርያም ሜጀር ባዚሊካ ውስጥ መቀበር እንደ ሚፈልጉ ቅዱስነታቸው የተናገሩት።
ምርጫው ታሪካዊ አዲስ ነገርን ያመላክታል፣ በተለይም በቅርብ ጊዜ ከነበሩት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጋር በተያያዘ፣ ሁሉም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ውስጥ ነበር የተቀበሩት (የመጨረሻው በነዲክቶስ 16ኛ፣ እ.አ.አ በታህሳስ 31 ቀን 2022 ነበረ የቀብር ሥነ-ሥራታቸው የተከናወነው)። ይሁን እንጂ በቅድስት ማርያም ሜጀር የመቀበር ውሳኔ ጳጳሱ ከ100 ጊዜ በላይ ከጎበኙት ባዚሊካ ጋር ያላቸውን ትስስር ያጠናክራል፡ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሆነው በተመረጡበት ማግስት እ.አ.አ መጋቢት 14 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ከዚያ በፊት እና ከእያንዳንዱ ዓለም አቀፍ ጉዞ በኋላ እና በመጨረሻ ባለፈው ሳምንት እ.አ.አ ታህሳስ 8/2023 ባላቲን ቋንቋ “Salus Populi Romani” በአማሪኛው በግርድፉ ሲተረጎም “የሮም ከተማ ሕዝቦች አዳኝ ወይም ጠባቂ” በመባል በሚታወቀው እና በአብዛኞቹ የሮም ከተማ ነዋሪዎች ከፍተኛ ክብር የሚሰጠው፣ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ሕጻኑን ኢየሱስን በእጆቹዋ ላይ አቅፋ መያዙዋን የሚያሳየው ምስል ሥር “ወርቃማ ጽገሬዳ” ማስቀመጣቸው እና ጸሎት አድርገው መመለሳቸው ይታወሳል።
“ይህ የእኔ ታላቅ ፍቅር ነው። የእኔ ታላቅ አምልኮ። እናም በፊት እኔ ወደ ሮም ስመጣ [ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሆነው ከመመረጣቸው በፊት ማለት ነው) ወደ ሮም ስመጣ ሁልጊዜ እሁድ ጠዋት እዛ እሄድ ነበር፣ እዚያም ለጥቂት ጊዜ እቆይ ነበር። በጣም ትልቅ ትስስር አለ” ብለዋል ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ። የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳቱን የቀብር ሥነ ሥርዓት ከሊቀ ጳጳሱ የክብረ በዓሉ ዋና አዘጋጅ ጋር እንዳዘጋጁ ገልጿል። ሥነ ሥረዓቱን "ብዙ አቅልለናል" ብለዋል። በቅርቡ የተደረገው የርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ የቀብር ሥነ ሥርዓት የበነዲክቶስ 16ኛ ሲሆን ይህም የተከናወነው እ.አ.አ በጥር 5/2022 ዓ.ም በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የተደረገ ነው።
ከቤኔዲክት 16ኛ ጋር ያላቸው ግንኙነት
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የቤኔዲክት 16ኛ ሕልፈት አንደኛ ዓመት ሊከበር ጥቂት ቀናት ሲቀረው ቀደም ብሎ ለአሥር ዓመታት እንደ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሆነው ስያገለግሉ ከኖሩት ከቀደሞ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጋር ስለነበራቸው ግንኙነት ተናግሯል። “ከጳጳስ ቤኔዲክት ጋር የነበረኝ ግንኙነት በጣም የቀረበ ነበር። አንዳንድ ጊዜ ልጠይቃቸው እሄድ ነበር። እና እርሳቸው በታላቅ ጥበብ ሀሳባቸውን ይሰጡኝ ነበር። እርሳቸው ግን ‘አየህ (የምታስበውን)’ ፈጽም ይሉኝ ነበር፣ ነገሮችን በሙሉ በእጄ ይተው ነበር። እርሳቸው ሁል ጊዜ ረድተውኛል። በዚህ ረገድ በጣም ለጋስ ነበሩ ብለዋል ።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እ.አ.አ በ 2022 በመጨረሻዎቹ አከባቢ መታመማቸውን እና ለእርሳቸው ጸሎት መጠየቃቸውን ከአንድ ነርስ እንደሰማሁ ቀድሞውንም “ለመሰናበት” መቻል እንደ “ጸጋ” ነው ሲሉ ገልፀውታል “ደማቅ ነበር፣ ነገር ግን ከዚያ ወዲያ መናገር አልቻሉም እና እጄን አጥብቀው ያዙ። ያ ጥሩ ነበር መሰናበት። ቆንጆ ነበር። ከሦስት ቀንም በኋላ ከእዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። የቀድሞ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክት 16ኛ ታላቅ ሰው፣ ትሁት፣ ቀላል ሰው ነበሩ፣ ውስንነታቸውን ሲያውቁ፣ ለመናገር በቂ ድፍረት ነበራቸው። ይህን ሰው አደንቃለሁ” ብለዋል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ቤኔዲክት 16ኛ ከአሁን በኋላ አለመኖራቸውን “አላስተዋሉም” ብለዋል፣ በዚህም ምክንያት የእርሳቸው ከርዕሰ ሊቃነ ጵጵስና በገዛ ፈቃዳቸው መልቀቅ በማተር ኤክሌዚያ መኖሪያ ውስጥ ከነበሩት የመጨረሻዎቹ የህይወት ዓመታት ጋር ተመሳሳይ ነው፡ ልባም፣ ጸጥተኛ፣ ተፈጥሯዊ ነበር " ይህንን በደንብ አላስተዋልኩም ነበር ብለዋል። አንዳንድ ጊዜ በጳጳሱ መካነ መቃብር ላይ ለመጸለይ እሄዳለሁ እና በእርሳቸው በኩል አልፋለሁ። ነገር ግን እርሳቸው ሲመክሩኝ እንደነበረው አላስተዋልኩም፣ ሌላ ሰው እየመከረኝ እንዳለ አላስተዋልኩም። በነጻነት ነገሮችን የማድረግ ጥበብ ነበራቸው። ግን እንደበፊቱ ተመሳሳይ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
ከርዕሰ ሊቃነ ጵጵስና የመልቀቂያ እቅድ የለኝም።
እንደሌሎች አጋጣሚዎች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የቤኔዲክት 16ኛ ፈለግ ለመከተል አንድ ቀን እንደማይቀር ተናግረው የነበረ ቢሆንም፣ ነገር ግን አሁን ጊዜው እንዳልሆነ ደጋግመው ገልጸዋል። ከዓመት በፊት፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከኤቢሲ የዜና አውታር ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ በጵጵስና ዘመናቸው መጀመሪያ ላይ - እንደተለመደው - በወቅቱ የቫቲካን ዋና ጸሐፊ ለነበሩት ታርቺስዮ በርቶኔ የሕክምና እክል በሚደርስባቸው ወቅት ከርዕሰ ሊቃነ ጵጵስናቸው አገልግሎት በፍቃዳቸው እንደ ሚለቁ የምያመለክት ደብዳቤ ማቅረባቸውን አስታውቀዋል። ደብዳቤው ባለበት ይቀራል፡- “ስለ እሱ አላስብም። እናም የቤኔዲክትን ድፍረት አይቻለሁኝ። መቀጠል እንደማይችሉ ሲያውቁ 'በቃ' ማለትን መረጡ። እናም ይሄ ለእኔ እንደ ምሳሌ ይጠቅመኛል፣ እናም ጌታን 'በቃኝ' እንድል እንዲረዳኝ እጠይቃለሁ፣ በመጨረሻ ግን እሱ በሚፈልግበት ወቅት ይሆናል” ሲሉ ተናግረዋል።
እርጅና እና ጤና
አንዳንድ ተቺዎች እንደሚሉት እውነት ነው ወይ ተብሎ የተጠየቀው የቀድሞ መሪ ካለፈ በኋላ “ጠንካራ” ሆነዋል፣ በሌላ በኩል ደግሞ ተሳዳቢዎቹ “የበለጠ ጨካኝ፣ የበለጠ ጨካኝ ሆነዋል” ተብለው ያስባሉ ለሚለው ጥያቄ ቅዱስነታቸው በቀልድ ምላሽ የሰጡ ሲሆን "አይ አንድ ሰው በዙሪያው ያሉትን ትንንሽ ልጆችን በጥፊ እንደ ማጮል ይቆጠራል ....” በማለት ከልጆቻቸው ጋር በሚኖራቸው ግንኙነት ከአባቶች ጋር ያለውን ንጽጽር ተናግሯል፡- “አንዳንድ ጊዜ ማስተማር ያስፈልጋል፣ ነገር ግን ሰዎች እዚህ ረገድ በጣም ጥሩ ናቸው። ውስብስብ ነኝ አንዳንዴም ትንሽ ትዕግስት ላይኖረኝ ይችላል በእዚህ የተነሳ ሰዎች ይተቹኛል ....በሮም ኩሪያ ውስጥ ያሉ ሰዎች በጣም ጥሩ ናቸው” ሲሉ የመለሱ ሲሆን ጋዜጠኛው “አሁን ግን እነርሱን አጥብቀው አልያዙም …” ብሎ ላቀረበላቸው ጥያቄ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳቱም ሲመልሱ፣ “አያቶች እንኳን እየተሻሻሉ ነው፣ ይህ የሕይወት እርጅና አካል ነው” ሲሉ መልሰዋል።
ስለ "እርጅና" ሲናገሩ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ - በቅርብ ጊዜ በብሮንካይተስ በሽታ ተይዘዋል እና ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ በጂሜሊ ሆስፒታል ውስጥ ሁለት ጊዜ ቀዶ ጥገና ተደረጎላቸው እንደነበረ አስታውሰው- የጤንነታቸው ሁኔታ ደካማነት አምነዋል፣ ነገር ግን ስለ ጤና ሁኔታቸው መሻሻል አረጋግጠዋል። “ደህና ስሜት ይሰማኛል፣ ጥሩ ስሜት ይሰማኛል” ሲሉ ተናግሯል፣ “ለጤንነቴ እንድትፀልዩ እፈልጋለው” ምክንያቱም “እርጅና በራሱ አይመጣም… እራሱን አያስተካክልም፣ እራሱን እንደሚያሳይ ያሳያል” በማለት ተናግሯል። በሌላ በኩል፣ “የእርጅና ስጦታዎችን እንዴት መቀበል እንዳለብህ ማወቅ አለብህ” እና “ከሌላ እይታ አንጻር ጥሩ መስራት እንደምትችል ማወቅ አለብህ” ብሏል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ “አንዳንድ ጊዜ ነገሮችን መሥራት እና መንቀሳቀስ እንደምፈል ስለሚሰማኝ ግድየለሽ እንደሆንኩ ይነግሩኛል” ብለዋል ። እርሱ “ደህና ነኝ” የሚል ምልክት ነው ይሉኛል ብለዋል።
መጪ ጉዞዎች
ብሮንካይተስ እ.አ.አ በታህሳስ ወር መጀመሪያ ላይ ወደ ዱባይ ለኮፕ 28 የሚደረገውን ጉዞ እንዲሰረዝ አስገድዶታል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ “እውነት ነው፣ ሁሉም ጉዞዎች አሁን እንደገና እየታሰቡ ነው። በጣም ሩቅ የሆኑት እንደገና ይታሰባሉ። ገደቦች አሉ አይደል? እዚህ ሁሉም ነገር ያበቃል እና ሌላ ነገር እንደሚጀምር እንዲገነዘቡ የሚያደርግ ገደብ፣ እርጅና ብዙ ነገር ያደርግሃል፣ ያምራል” ሲሉ ተናግረዋል።
የጳጳሱ ጉዞዎች እንደገና እየተገመገሙ ቢሆንም፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ አሁንም በሚቀጥለው ዓመት ሦስት ጉብኝቶችን ለማድረግ ተስፋ ያደርጋሉ፡ ወደ ቤልጂየም፣ ፖሊኔዥያ እና አርጀንቲና።
የመጀመሪያው፣ ወደ ቤልጂየም፣ በንጉሥ ፊሊፕ እና በንግሥት ማቲልዴ የተጋበዘበት “ደህንነቱ የተጠበቀ ነው” ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ተናግረዋል። የተቀሩት ሁለቱ "በመጠባበቅ ላይ" ናቸው "ነገሮች እንዴት እንደሚሄዱ እናያለን" ብለዋል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ስለ ፖሊኔዥያ ጉብኝት በይፋ ሲናገሩ ፣ ባለፈው ዓመት በሰጡት ቃለመጠይቆች ሁሉ ወደ ትውልድ አገራቸው የመመለስን ሀሳብ ሲጠቅሱ ይህ የመጀመሪያ ጊዜ ነው ።
አዲሱ ፕሬዝዳንት ጃቪየር ሚሌይ በምርጫ ማሸነፋቸው ጳጳሱን ወደ አርጀንቲና በስልክ ጋብዘው ነበር። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከዚህ ቀደም አዲሱ ፕሬዚዳንት ይጠቀምባቸው ስለነበረው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ስለተገለጹት አገላለጾች ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፡- “በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት ነገሮች በዋዛ ይነገራሉ፣ በጥቅሶች እላለሁ፡ በቁም ነገር ይነገራል፣ ግን ጊዜያዊ ነገሮች ናቸው። ትንሽ ትኩረትን ለመፍጠር የሚያገለግሉ ነገሮች፣ ግን በራሳቸው ይጠፋሉ። አንድ ፖለቲከኛ በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት ከሚናገረው እና በኋላ በሚሰራው መካከል ብዙ መለየት አለብህ ፣ ምክንያቱም ከዚያ በኋላ ተጨባጭነት ፣ የውሳኔዎች ጊዜ ይመጣል” ሲሉ ተናግረዋል።