TOPSHOT-ISRAEL-PALESTINIAN-CONFLICT

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት፡- ለጦር መሳርያ ሳይሆን ለሰላም አዎንታዊ ምላሽ መስጠት ያስፈልጋል አሉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በጋዛ አፋጣኝ የተኩስ አቁም እንዲደረግ እና እዚያ ያሉ ታጋቾች በሙሉ እንዲፈታ በድጋሚ ጥሪ ማቅረባቸው ተገለጸ።

የእዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ታኅሳስ 03/2016 በቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ 6ኛ የስብሰባ ዳራሽ ዘወትር ረቡዕ ለእት የሚያደርጉትን የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስትምህሮ ካጠናቀቁ በኋላ ባስተላለፉት መልእክት  በጋዛ ያለው ጦርነት እንዲቆም አዲስ ጥሪ አቅርበዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

"በእስራኤል እና በፍልስጤም መካከል ያለውን ግጭት በብዙ ጭንቀት እና ስቃይ መከታተሌን ቀጥያለሁ" ያሉት ቅዱስነታቸው “አፋጣኝ ሰብአዊ የተኩስ አቁም ጥሪዬን በድጋሚ አቀርባለሁ፣ እዚያ ብዙ ስቃይ አለ፣ ስቃዩ ሊያበቃ ይገባል” ማለታቸው ተገልጿል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ አክለውም "ሁሉም በግጭቱ ላይ የተሳተፉ አካላት ድርድሩን እንደገና እንዲቀጥሉ አበረታታለሁ እናም ሁሉም ለጋዛ ህዝብ ሰብአዊ እርዳታ ለማግኘት አስቸኳይ ቁርጠኝነት እንዲያደርጉ ጥሪ አቀርባለሁ" ብለዋል ።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ “ይህ በእስራኤላውያን እና ፍልስጤማውያን ላይ እይደረሰ ያለው ታላቅ ስቃይ ያበቃ ዘንድ ታጋቾች በአስቸኳይ ይፈቱ” በማለት ሁሉም የእስራኤል ታጋቾች በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጠይቀዋል።

“እባካችሁ ለጦር መሳርያ እንቢታችሁን፣ ለሰላም አዎንታዊ ምላሻችሁን ግለጹ!” ማለታቸው ተዘግቧል።

ጋዛ በ'ጠቅላላ ውድቀት' ጫፍ ላይ ናት

እስራኤል አሁን ትኩረቷን በደቡብ በሚገኘው ካን ዮኒስ ላይ በማድረግ የጋዛ ወረራዋን ቀጥላለች። በግብፅ ድንበር አቅራቢያ በራፋህ እና በተያዘው ዌስት ባንክ ውስጥ በጄኒን ጦርነት ተካሂዷል።

ይህ ሁሉ ሲሆን በሰብአዊ ቀውሱ ላይ እይደረሰ የሚገኘው ችግር ያበቃ ዘንድ አለም አቀፍ ጫና እየጨመረ ነው። የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን እስራኤል በጋዛ ላይ እያደረሰችው ባለው አድሎአዊ የቦምብ ጥቃት ዓለም አቀፍ ድጋፍ ማጣት መጀመሯን ተናግረዋል።

የተባበሩት መንግስታት የፍልስጤም ስደተኞች ኤጀንሲ በበኩሉ የተቀረው የጋዛ ሰርጥ አጠቃላይ የሲቪል ስርዓት ውድቀት ላይ ነው ብሏል። በጋዛ በሃማስ ቁጥጥር ስር የሚገኘው የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጦርነቱ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ከ18,000 በላይ ሰዎች መሞታቸውን ገልጿል።

ሃማስ ከ1,200 በላይ ሰዎችን ከገደለ እና ከ200 በላይ ሰዎችን ካገተ በኋላ እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላይ ከፍተኛ ጥቃት መክፈቷ ይታወሳል።

13 December 2023, 11:28