ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ 6ኛ የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ በቫቲካን ውስጥ ከሚሰሩ ሰራተኞች እና ቤተሰቦቻቸው ጋር በረገናኙበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ 6ኛ የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ በቫቲካን ውስጥ ከሚሰሩ ሰራተኞች እና ቤተሰቦቻቸው ጋር በረገናኙበት ወቅት  (Vatican Media)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ለቫቲካን ሠራተኞች፡ ቤተ ክርስቲያንን ያለታይታ እና በየዋሕነት አገልግሉ አሉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከቫቲካን ሠራተኞች ጋር የገና በዓል ሰላምታ ልውውጥ ካደርጉ በኋላ በሥራ ቦታ ክርስቲያናዊ ምስክርነታቸውን እንዲሰጡ ያበረታታሉ።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

"እግዚአብሔር በተወለደ ሕፃን ትንሽነት ውስጥ ራሱን ይሰውራል” ።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ሐሙስ ዕለት ታኅሳስ 11/2016 ዓ.ም ለቫቲካን ሰራተኞች የገና ሰላምታ ባቀረቡበት ወቅት ዋና ነጥብ አድርገው “ድብቅነት እና ትንሽነት” የሚሉትን መንትያ ቃላት ተጠቅመዋል።

በየዓመቱ እንደሚያደርገው፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ከጌታ ልደት በዓል በፊት ከቫቲካን ሠራተኞች እና ከቤተሰቦቻቸው ጋር የደስታ ሰላምታ እንደ ሚለዋወጡ ይታወቃል።

ድብቅነት እና ትንሽነት

ቅዱስ አባታችን በተዘጋጀው ንግግራቸው፣ የኢየሱስ መወለድ “ትልቅ የሆነ ትይንት ሳይሆን ወይም ጫጫታ የሌለው፣ ይልቁንም በስውርና በትንሽነት የሚታወቅ ዘይቤ” የሆነውን አምላክ የመረጠውን ዘይቤ እንደሚገልጥ አስታውሰዋል።

“እነዚህ ባህሪያት” በማለት በታላቅነቱ ሊያስደነግጠን ወይም በታላቅነቱ ሊጫነን ወደ እኛ የማይመጣውን፣ ነገር ግን ራሱን በጣም ተራ በሆነ መንገድ እንዲገኝ የሚያደርግ፣ አንድ ሆኖ ወደ እኛ የመጣውን የእግዚአብሔርን የዋህ ባህሪ ያሳየናል” ሲሉ ቅዱስነታቸው ተናግረዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ኢየሱስ በቤተልሔም በበረት ውስጥ መወለዱን አመልክተዋል ይህም እግዚአብሔር ከሁሉም ጋር ለመቀራረብ ያለውን ፍላጎት ያሳያል ያሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ “እርሱ የሕጻናት እና የመጨረሻዎቹ አምላክ ነው፣ እናም ከእርሱ ጋር፣ ሁላችንም ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባትን የምንማርበትን መንገድ እንማራለን፡ በግልጽ እና በሰው ሰራሽ ሃይማኖቶች ሳይሆን፣ እንደ ሕፃናት ትናንሽ በመሆናችን ነው እግዚአብሔር ወደ መንግሥቱ የሚጠራን” ሲሉ ተናግረዋል።

በሥራ ቦታ የክርስቲያን ምስክር

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በመቀጠል የቫቲካን ሰራተኞች የኢየሱስን ድብቅነት እና ትንሽነት በዕለት ተዕለት ሥራቸው እንዲመስሉ ጋብዘዋል።

"እዚህ በቫቲካን ውስጥ የምትሰሩት ሥራ በእለት ተእለት ድብቅነት ውስጥ ነው የሚሰራው፣ ብዙ ጊዜ ቀላል የማይመስሉ ስራዎችን በመስራት በምትኩ ለቤተክርስቲያን እና ለህብረተሰቡ አገልግሎት ለመስጠት አስተዋፅዖ ያደርጋል" ብሏል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በቫቲካን ውስጥ ተቀጥረው የሚሠሩ ሰዎች ከሥራ ባልደረቦቻቸው ጋር በሚኖራቸው ግንኙነት "በምስጋና፣ በእርጋታ እና በትህትና" ክርስቲያናዊ ምስክርነት እንዲሰጡ አሳስበዋል።

የልደቱ ትዕይንት በተመለከተ አክለውም የተናገሩት ቅዱስነታቸው ሥራቸው በተደበቀ እና በማይታይበት ጊዜም እንኳ ፍሬ እንደሚያፈራና “የደስታ ሽቶ” እንደሚያስገኝ በመግለጽ ትሁት የሆነ ልብ እንዲኖራቸው ቅዱስነታቸው ግብዣ አቅርበዋል።

ፍቅር ምንም ድምጽ አያሰማም

ቅዱስ አባታችን የገና ሰላምታ ለቫቲካን ሰራተኞቻቸው እና ቤተሰቦችም አቅርበዋል ዓለማችን በማህበራዊ ሚዲያ መስኮት ሁሉንም ነገር ለአለም ለማሳየት እንደምትሻ ጠቁመዋል።

“ወይኑ ጥሩ ስለመሆኑ ሳይጨነቁ ውድ የሆነ  ከፍተኛ ጥራት ያለው በመስታወት የተሰራ ብርጭቆዎችን የመፈለግ ያህል ነው” ብሏል።

ይሁን እንጂ በቤተሰብ ውስጥ፣ መልክ እና ጭምብሎች በጥቂቱም ቢሆን ጥቂት ዋጋ እንዳላቸው ሆኖ ይቆጠራሉ፣ ምክንያቱም የቤተሰብ ህይወት በጥሩ ሁኔታ ለመስራት "በፍቅር፣ ገርነት እና የጋራ መግባባት ጥሩ ወይን" መሞላት አለበት ብለዋል።

"እናም ፍቅር - እኛ በደንብ እንደምናውቀው - ምንም ድምጽ አያሰማም" ያሉት ቅዱስነታቸው  "በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎች ድብቅነት እና ትንሽነት ውስጥ እናገኘዋለን፣ እንዴት መለወጥ እንዳለብን በምናውቅ እንክብካቤ ውስጥ" እናገኛቸዋልን ብለዋል።

በቤተሰብ ውስጥ እንክብካቤ እና ዓላማ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የቫቲካን ሰራተኞች ቤተሰቦቻቸውን በቅዱስ ቤተሰብ አርአያነት እንዲንከባከቡ ባቀረቡት የገና በዓል አመታዊ የሰላምታ መልእክት ገልጸዋል።

"ይህ ለእናንተ የእኔ ምኞቴ ነው፡ በቤታችሁ እና በቤተሰቦቻችሁ ውስጥ፣ በእለት ተእለት ህይወት ውስጥ ለሚኖሩ ጥቃቅን ነገሮች፣ ለአነስተኛ የምስጋና ምልክቶች፣ እርስ በርስ ለመተሳሰብ እና ለመከባበር በትኩረት እንድትከታተሉ እጋብዛለሁ” ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው አመታዊውን የገና በዓል መልእክታቸውን አጠናቀዋል።

22 December 2023, 15:21