ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ ኦሽዊትዝ-ቢርኬናው የናዚ ማጎሪያ ካምፕ በጎበኙበት ወቅት ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ ኦሽዊትዝ-ቢርኬናው የናዚ ማጎሪያ ካምፕ በጎበኙበት ወቅት  

ር.ሊ.ጳ ፍራችስኮስ ከሆሎኮስት (እልቂት) አመታዊ መታሰቢያ ቀን በፊት ጦርነቶች እንዲቆሙ ጥሪ አቀረቡ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ረቡዕ ጥር 15/2016 ዓ.ም ባደረጉት የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ምብቂያ ላይ በኦሽዊትዝ-ቢርኬናው የናዚ ማጎሪያ እና የጥፋት ካምፕ ነፃ የወጡበትን ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚዘክርበት ቀን ከመድረሱ በፊት ባስተላለፉት መልእክት ጦርነቶች እንዲቆሙ ተማጽነዋል፣ በሰላማዊ ዜጎች ላይ እየደረሰ ያለውን የቦምብ ድብደባ አውግዘዋል ። ዩክሬን እና በጋዛ የቀጠለው የሰብአዊ ቀውስ በአስቸኳይ እንዲቆም ጥሪ አድርገዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

"በሚቀጥለው ቅዳሜ እ.አ.አ በጥር 27/2024 ዓለም አቀፍ የሆሎኮስት መታሰቢያ ቀን ነው። ባለፈው ምዕተ-አመት የመጀመሪያ አጋማሽ ላይ የተከሰተውን በሚሊዮን የሚቆጠሩ አይሁዶች እና የሌላ እምነት ተከታይ ሰዎች ላይ ያደረሰው አሰቃቂ ግድያ መታሰቢያ በምናከብርበት ወቅት ይህንን አሰቃቂ ተግባ ማውገዝ ሁሉም ሰው ይህንን ጉዳይ እንዳይረሳው ይርዳል። የጥላቻ እና የዓመፅ አመክንዮ በፍፁም ሊጸድቅ አይችልም ምክንያቱም የእኛን ሰብአዊነት ይክዳል” ሲሉ መናገራቸው ተገልጿል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮ በቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ ስድስተኛ አዳራሽ ባደረጉት ሳምንታዊ አጠቃላይ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ መጨረሻ ላይ በእነዚህ ቃላት መጪውን ቀን ይጠብቁ ነበር፣ ይህም በየዓመቱ የኦሽዊትዝ-ቢርኬናው የነጻነት በዓል - ትልቁ የናዚ ማጎሪያ እና የሞት ካምፕ እንደ ነበረ የምናስታውስበት እና ጦርነትን እና ተመሳሳይ የሆኑ እልቂቶችን የምንቃወምበት ምክንያት እና ወቅት ነው። የኦሽዊትዝ ማጎሪያ ካምፕ በፖላንድ ኦሽዊሲም ከተማ አቅራቢያ የሚገኝ ሰፊ የማጎሪያ እና የእልቂት ካምፖ ነበር። በሁለተኛው የዓለም ጦርነት እ.አ.አ ከ1940 እስከ 1944 ባለው ጊዜ ውስጥ ከአንድ ሚሊዮን የሚበልጡ እስረኞች አብዛኞቹ አይሁዳውያን በእዚህ የማጎሪያ ጣቢያ ውስጥ ተገድለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ስለሰላም ጥረት ሲጠይቁ "ጦርነት እራሱ የሰውን ልጅ መካድ ነው" ብለዋል።

“ሰላም እንዲወርድ፣ ግጭቶች እንዲቆሙ፣ የጦር መሣሪያዎችን እንዲቆሙ፣ ለደከመው ሕዝብ እፎይታ እንዲሰጡ” እማጸናለሁ ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በድጋሚ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን "ጦርነት እራሱ የሰው ልጅን መካድ ነው...ስለ ሰላም መጸለይ አንታክት" ብለዋል።

ሰላማዊ ዜጎችን በመምታቱ በቦምብ ጥቃት ተሸብረዋል

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ሐሳባቸው በመካከለኛው ምሥራቅ ለሚገኙ ፍልስጤም እና እስራኤል፣ እንዲሁም ዩክሬን በተለየ መንገድ በማሰብ እንደ ተናገሩት “በሰላማዊ ሰዎች የሚዘወተሩ ቦታዎች ላይ የደረሰውን የቦምብ ፍንዳታ” “አስጨናቂ” ዜናን በመቃወም አጽንኦት ሰጥተው የተናገሩ ሲሆን "ሞትን፣ ጥፋትን፣ መከራን መዝራት" አባካችሁን አቁሙ ብለዋል።

በዚህ መንገድ "ያሸነፉ" ብቸኛዎቹ ሰዎችን ማወቅ ከፈለጋችሁ አሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለሐሳባቸው አጽኖት ሲሰጡ “የጦር መሳሪያ አምራቾች ብቻ ናቸው” ያሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በማጠቃለያው “ለተጎጂዎች እና ለሚወዷቸው ሰዎች እጸልያለሁ፣ እናም ሁሉም በተለይም የፖለቲካ ኃላፊነት ያለባቸው ሰዎች ጦርነቶችን በማቆም የሰውን ሕይወት እንዲጠብቁ እማጸናለሁ” ብለዋል።

"አንርሳ፡ ጦርነት ሁሌም ሽንፈት ነው ሁሌም" ሲሉ በምሬት ተናግረዋል።

ጦርነቶችን በማስቆም የሰውን ልጅ ሕይወት እንዲጠብቁ በተለይም የፖለቲካ ኃላፊነት ያለባቸው ሰዎችን ሁሉ እማጸናለሁ። አንርሳ፡ ጦርነት ሁሌም ሽንፈት ነው ሁሌም” ሲሉ በድጋሚ ከተናገሩ በኋላ ቅዱስነታቸው ንግግራቸውን አጠናቀዋል።

 

 

24 January 2024, 14:53