ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ አሁንም በጦርነት ለሚሰቃዩ ሰዎች ጸሎት ማድረጋችንን እንቀጥል አሉ!
የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን
በወቅቱ ቅዱስነታቸው ባስተላለፉት መልእክት የጦርነት አስከፊነትን ተቋቁመው ላሉት ህዝቦች አጋርነታቸውን የገለጹ ሲሆን "እንዲህ በከባድ ሙከራ ከተሞከረው ውድ የዩክሬን ህዝብ እና በፍልስጤም እና በእስራኤል እንዲሁም በሌሎች የአለም ክፍሎች በአስፈሪው ጦርነት ለሚሰቃዩት በፀሎት ለእነርሱ ያለኝን ቅርበት አድሳለሁ" ብሏል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱም ሁሉም ሰዎች በጦርነት ውስጥ ስላሉ አገሮች እንዲጸልዩ አበረታተዋል።
“ለእነዚህ ጦርነትን ለሚታገሱ ሰዎች እንጸልይ፣ እናም በአገሮች ባለ ሥልጣናት ልብ ውስጥ የሰላምን ዘር እንዲዘራ ወደ ጌታ እንጸልይ” ብሏል።
ለዓለማቀፋዊ ቀውሶች የጳጳሱ ስጋት
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለሰላም የምያቀርቡትን ጥሪ በአደባባይ መግለጻቸውን በፍጹም አላቋረጡም፣
ሰኞ ዕለት በቅድስት መንበር ዕውቅና ለተሰጣቸው አምባሳደሮች ዓመታዊ “የዓለም መንግሥት” ንግግር ባደረጉበት ወቅት በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ሥጋት በዝርዝር ገልጿል።
በጋዛ ውስጥ ያለው የእስራኤል-ሃማስ ጦርነት እና በዩክሬን ውስጥ ያለው የሩሲያ ጦርነት ዓለም አቀፋዊ ትኩረት እና አሳሳቢነት የሚጠይቁትን ሁኔታዎች ዝርዝር ውስጥ አስቀምጧል።
በተመሳሳይ ጊዜ ተከማችተው የሚገኙትን እጅግ በጣም ብዙ የጦር መሣሪያዎችን አውግዘው ነበር፣ "ተቃራኒው እውነት ነው፡ የጦር መሳሪያዎች መገኘት አጠቃቀማቸውን ያበረታታል እና ምርታቸውን ይጨምራል" ብለዋል ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ፣ "የጦር መሳሪያዎች አለመተማመንን ይፈጥራሉ እናም የአገር ሀብትን ያወድማሉ" ብለዋል።