FILES-INDONESIA-MYANMAR-ROHINGYA-REFUGEE-DISINFORMATION

ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ የሮሂንጊያን ችግር በማስታወስ ጦርነቶች እየተቀሰቀሱ በመሆናቸው የሰላም ጥሪ አቀረቡ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለሮሂንጊያ ስደተኞች ስቃይ ዓለም አቀፋዊ ትኩረት እንዲሰጥ ልዩ ጥሪ አቅርበዋል እናም ሁሉም በዩክሬን ፣ በቅድስት ሀገር በፍልስጤም እና በእስራኤል፣ እንዲሁም በሌሎች ቦታዎች እየተካሄዱ ባሉ ጦርነቶች ውስጥ ለሰላም እንዲጸልዩ አሳስበዋል ።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

"ጦርነቶችን አንርሳ። ሰማዕት የሆኑትን ዩክሬንን፣ ፍልስጤምን፣ እስራኤልን፣ ሮሂንጋዎችን እና በሁሉም ቦታ ያሉ ብዙ ጦርነቶችን አንርሳ። ለሰላም እንጸልይ" በማለት በብጥብጥ እና ጦርነት እየታመሰች በምትገኘው አለማችን ሰላም ይሰፍን ዘንድ ጥሪ በድጋሚ ያቀረቡት ቅዱነታቸው በዚህ ቃላት ነበር ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ 6ኛ የስብሰባ አዳራሽ እርሳቸው ዘወትር ረቡዕ እለት የሚያደርጉትን የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ለመከታተል ለተገኙ ምዕመናን ያደርጉትን የመጠቃለያ ንግግር  የደመደሙት።

"ጦርነት ሁሌም ሽንፈት ነው ሁሌም ለሰላም እንፀልይ ሰላም እንፈልጋለን" ሲሉ አስምረውበታል።

ለሮሂንጊያ፣ ምያንማር ሕዝቦች ያቀረቡት ጥሪ

እ.ኤ.አ. በ2017 ምያንማርን እና ባግላዴሽን የጎበኙት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በሮሂንጊያ ስደተኞች ላይ እየደረሰ ያለውን ስቃይ በመቃወም ድምጻቸውን ደጋግመው አሰምተዋል።

እ.አ.አ ከ1982 ጀምሮ በማይናማር ዜግነታቸው የተነፈጉት የሮሂንጋያ ሕዝቦች፣ አገር አልባ ያደረጋቸው፣ በዓለማችን ላይ ከፍተኛ ስደት ከሚደርስባቸው አናሳ ብሔረሰቦች መካከል አንዱ እንደሆነ ሲገለጽ፣ ለብዙ አስርት ዓመታትም በየብስ ወይም በጀልባ ወደ ጎረቤት አገሮች ተሰደዋል።

እ.አ.አ በጥር 24/2021 ዓ.ም በማያንማር በርማ ከተካሄደው መፈንቅለ መንግሥት በኋላ ያለው የሮጊያን ማሕበረሰብ ስቃይ እየጨመረ መምጣቱ ይታወቃል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በቅርቡ እ.አ.አ በጥር 28/2024 ዓ.ም ለሮጊያን ሕዝቦች ሰብአዊ እርዳታ እንዲደረግ ተማጽነዋል፣ ሁሉም ሰው የውይይት ጎዳና እንዲከተል አሳስበዋል።

"ለሦስት ዓመታት ያህል የህመም ጩኸት እና የጦር መሣሪያ የምያንማርን ሕዝብ የፈገግታ ቦታ ወስደዋል" ብሏል።

ከበርማ ጳጳሳት ጋር በጋራ በመሆን "የጥፋት መሳሪያዎች ወደ የሰው ልጆች እድገት እና የፍትህ መሥርያነት እንዲቀየሩ” ቅዱስነታቸው በጋራ ጸልየዋል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ሰላም ጉዞ መሆኑን ቢገነዘቡም፣ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ “የውይይት እርምጃዎችን እንዲወስዱ እና ማስተዋልን እንዲለብሱ” ጥሪ አቅርበዋል “የምያንማር ምድር ወንድማማችነትን የማስታረቅ ዓላማ ላይ ይደርስ ዘንድ” በጋራ እንጸልይ ብለዋል።

"የእያንዳንዱን ሰው ፍላጎት ለማረጋገጥ ሰብአዊ እርዳታ እንዲያልፍ ይፍቀዱ" ብለዋል።

ከሦስት ዓመታት በፊት ሥልጣኑን ከያዘው ወታደራዊ መንግሥት ጋር በምያንማር የሚካሄደው ጦርነት ተባብሶ ብዙዎች ሀገሪቱ አሁን በእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ትገኛለች እስከማለት ደርሷል።

07 February 2024, 13:56