FOOD-WASTE/VATICAN

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት እኛ የምንጥለው ምግብ የተራቡትን ሁሉ መመገብ ይችላል ማለታቸው ተገለጸ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለዓለም አቀፉ የግብርና ልማት ፈንድ (IFAD) ባስተላለፉት መልእክት፣ የምግብ ብክነት ያለውን አደጋ በማስጠንቀቅ የአየር ንብረቱን የሚጎዳ ቢሆንም የዓለምን ረሃብተኞች ሊመመግብ ይችላል ብለዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በ47ኛው የዓለም አቀፉ የግብርና ልማት ፈንድ (IFAD) የአስተዳደር ምክር ቤት ጉባኤ ተሳታፊዎች ላይ ረቡዕ የካቲት 6.2016 ዓ.ም መልእክት አስተላልፈዋል።

“የማንም ሰው ክብር የማይነካበት እና ወንድማማችነት እውን የሚሆንበት፣ ለሁሉም የደስታና የተስፋ ምንጭ የሆነበት ለተሻለ ዓለም ለመመስረት ላደረጉት ቁርጠኝነት፣ ጊዜ እና ጉልበት አድናቆታቸውን ቅዱስነታቸው ገልጿል።

ዓለማችን ዛሬ ከምግብ ጋር የተያያዘ ልብ የሚሰብር እጅግ በጣም ተቃርኖዎች እንዳለባት ቅዱስ አባታችን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የገለጹ ሲሆን "በአንድ በኩል በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በረሃብ ይሰቃያሉ፣ በሌላ በኩል ደግሞ በምግብ ብክነት ውስጥ ከፍተኛ የስሜት መቃወስ ይታያል" ብለዋል።

ይህ ተርፎ የሚጣለው የምግብ ቆሻሻ በየዓመቱ ብዙ የሙቀት አማቂ ጋዞችን እንደሚያመርት ገልጸው፣ በተገቢው ከተጠቀምንበት ደግሞ በመላው ዓለም የሚገኙትን የተራቡ ሰዎችን ሁሉ ለመመገብ በቂ ነው ሲሉ በቁጭት ተናግረዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የአየር ንብረት ለውጥን፣ የሀብት ዘረፋን እና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ህልውና አደጋ ላይ የሚጥሉ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ግጭቶችን ሲገልጹ “ዓለምን ወደ አደገኛ ገደቦች እየገፋን ነው” ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እንዳሉት ቀውሶች በሚኖሩበት ጊዜ ምንም ይሁን ምን መጀመሪያ የሚሠቃዩት በገጠርማ አከባቢ የሚኖሩ ማኅበረሰቦች ናቸው” ብለዋል።

“የአገሬው ተወላጆች የችግር፣ የእጦትና እንግልት ሰለባዎች ናቸው” ሲሉም አክለው የገለጹት ቅዱስነታቸው “ስለ ተፈጥሮ ሀብት አያያዝ ያላቸው እውቀት እና ከአካባቢው ጋር ያላቸው ትስስር የብዝሃ ህይወትን ለመጠበቅ ይረዳል” ሲሉ አፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በመቀጠል ስለሌላ ችላ ስለተባለው የሰዎች ቡድን ተናገሩ፡- ሴቶች የገጠርማ ሥፍራዎች የምግብ መሰረት ናቸው፣ ነገር ግን በተቃራኒው ሴት ወጣቶች የሥልጠና፣ ግብዓት እና እድሎች እጥረት አሉባቸው፣ በተቃራኒው ደግሞ የቤተሰቡ መሰረት ናቸው ብለዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳቱ አሁን ያሉትን ችግሮች በተለይም ረሃብንና ድህነትን እንድንጋፈጥ ያነሳሳናል ረቂቅ ስልቶች ወይም ሊደረስባቸው የማይችሉ ቁርጠኝነት ላይ በመቀመጥ ሳይሆን ከጋራ ተግባር የሚመነጨውን ተስፋ በማጎልበት ነው ብለዋል ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ።  የበለጠ ሁሉን ያሳተፈ የግብርና እና የምግብ ስርዓት ለመገንባት በጋራ ለመስራት ቁርጠኛ መሆን እንደሚገባ የገለጹ ሲሆን በመጨረሻም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የታማኝነት፣ የትብብር እና የአገልግሎት መንፈስ “የመገለል ፣የድህነት እና የሀብት አጠቃቀምን እንዲሁም የአየር ንብረት ቀውሶችን ተፅእኖዎች እንዲወገዱ እንደሚጸልዩ ከገለጹ በኋላ ቅዱስነታቸው መልእክታቸውን አጠናቀዋል።

15 February 2024, 14:52