ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ከዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በፊት 'ተጨማሪ ሰብዓዊ መብት' እንዲከበር አሳስበዋል!
የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በየዓመቱ እ.አ.አ መጋቢት 8 ቀን ለሚከበረው ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በዓል ረቡዕ የካቲት 27/2016 ዓ.ም መልእክት አስተላልፈዋል።
መልእክቱ በሮም በተካሄደው ጉባኤ ላይ "የሴት መሪዎች፡ ወደ ብሩህ የወደፊት ጊዜ" በሚል መሪ ቃል በንባብ መልክ ቀርቧል። ጉባሄውን ያዘጋጁት በካሪታስ ኢንተርናሽናልስ እና በቅድስት መንበር የአውስትራሊያ እና የእንግሊዝ ኤምባሲዎች ናቸው።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ባስተላለፉት መልእክት የካሪታስ ኢንተርናሽናልስ ዋና ጸሃፊ እና የእንግሊዝ እና የአውስትራሊያ አምባሳደሮች ይህንን የሐሳብ ቀን በጋራ እንደሚያስተናግዱ በማወቄ ደስ ብሎኛል ብለዋል።
በጉባሄው ላይ እንዲሳተፉ የተደረገላቸው “ደግ ግብዣ”ም ምስጋናቸውን ገልጿል። በዝግጅቱ ላይ መሳተፍ ባይችሉም፣ ቅዱስ አባታችን ሁሉንም ተሳታፊዎች በእነሱ ላይ “ሁሉን ቻይ የሆነውን የእግዚአብሔርን የጥበብ ስጦታ” እንዲደርሳቸው እንደ ጸለዩም ገልጸዋል።
ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ጉባኤው ፍሬ እንዲያፈራ ጸለዩ “በሁሉም በቤተክርስቲያን እና በዓለም ዙሪያ የሴቶች እና የወንዶች እኩል እና አጋዥ የሆነ ሰብዓዊ መብት መከበርን ለማሳደግ በሚደረገው ቁርጠኝነት ሁሉም እንዲሳተፉ ቅዱስነታቸው ጥሪ አቅርበዋል።