ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ለአንድ ካህን ማዕረገ ክህነት ሲሰጡ የሚያሳይ ምስል ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ለአንድ ካህን ማዕረገ ክህነት ሲሰጡ የሚያሳይ ምስል   (Vatican Media)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የአንድ ቄስ ዋና ግዴታ ፍቅርን ህያው ማድረግ ነው አሉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከጳጳሳዊ የላቲን አሜሪካ፣ የብራዚል እና የሜክሲኮ ኮሌጆች አባላት ጋር ሲነጋገሩ በፍቅር ላይ በማሰላሰል “በካህናት ሕይወት ውስጥ ዋና ጭብጥ ነው” ብለውታል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ሐሙስ መጋቢት 26/2016 ዓ.ም  ለላቲን አሜሪካውያን የዘረዓ ክህነት የሕነጻ ትምህርት ሰጪ መምህራን እና የዘርዓ ክህነት ተማሪዎች  እንደተናገሩት "ፍቅር፣ የመጀመሪያው ፍቅር፣ ሁላችን እዚህ የጠራን እርሱ ነው፣ እናም እሱን በሕይወት ማቆየት ዋናው ግዴታችን ነው" ሲሉ ቅዱስነታቸው ተናግረዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለላቲን አሜሪካ፣ ብራዚል እና ሜክሲኮ ጳጳሳዊ ኮሌጆች አባላት ባደረጉት ንግግር “እያንዳንዱ ሙያ የሚወለደው በትንቢት ፍቅር ነው” ሲሉ ለካህናቱ በማሳሰብ እግዚአብሔር “እኛን የሚስብ ልዩ ሥራ እንደሰጠን ተናግረዋል። ወደ እሱ መቅረብ፡ ራሳችንን ለሌሎች አሳልፈን መስጠት ነው፣ በእኛ ውስጥ የሚሠራው እርሱ ክርስቶስ ራሱ ነው” ብለዋል።

ካህናት እንደሚያደርጉት “በክርስቶስ አካል” መሆን ማለት “የኢየሱስ እውነተኛ አምድ” መሆን ማለት ነው፣ በጸሎት፣ የራስን ለጋስ መስዋዕትነት እና ትሕትና ውስጥ ገብቶ መኖር ማለት ነው ሲሉ ቅዱስነታቸው ተናግረዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ጸሎት ማለት እያንዳንዱን ተጨባጭ ሁኔታ ለእግዚአብሔር መገኘት ማቅረብ ማለት እንደሆነ አብራርተዋል።

በመጨረሻም ትህትና ማለት “እኔ ራሴ በጉዞ ላይ እንዳለሁ፣ ጸሎት እንደሚያስፈልገኝ፣ ለማገልገል ከተጠራሁበት  ሰዎች የበለጠ እንደሆነ ማወቅ” ማለት ነው።

ቅዱስ አባታችን ካህናትን እና ሴሚናሪስቶች “እግዚአብሔር በመንገዳችሁ ላይ ያስቀመጣቸውን ሰዎች ምልጃ ኃይሉን እንዳያሳንሱ” ጋብዘዋል። በአንድ ቃል፣ “በእግዚአብሔር ታማኝ ሰዎች ሁሉ ጸሎት ላይ ተመኩ፤ እና ስለ ቤተክርስቲያን አባቶች እና ለእኔም መጸለይ አትርሱ” ያሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የኢየሱስን በረከት እና የአሜሪካ ንግሥት የጓዳሉፕ እመቤታችንን ጥበቃ በመማጸን በረከታቸው በእነርሱ ላይ እንዲሆን ከተመኙ እና ሐዋርያዊ ቡራኬያቸውን ከሰጡ በኋላ ንግግራቸውን አጠናቀዋል።

 

05 April 2024, 18:19