ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ በብራዚል የሚገኙ ሊቀ ጳጳስ የተከሰተውን የጎርፍ አደጋ እንዲያግዙ ጥሪ አቀረቡ!
የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን
ከሚያዝያ ወር መጨረሻ ጀምሮ በደቡብ ብራዚል በጣለው ከባድ ዝናብ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 137 ደርሷል።የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር ከ600,000 በላይ ሆኗል። በጣም አስገራሚው ሁኔታ በአርጀንቲና እና በኡራጓይ ድንበር ላይ በሪዮ ግራንዴ ዶ ሱል ግዛት ውስጥ ነው አደጋው የተከሰተው፣ የዝናብ መጠኑ እየጨመረ በሚሄድበት እና በሚቀጥሉት ሰዓታት ውስጥ የከፋ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።
የጳጳሱ አጋርነት
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በዚህ አደጋ ለሚሰቃዩት ሁሉ ለሊቀ ጳጳሱ ባደረጉት የስልክ ጥሪ በዋነኛነት ድሃውን ህዝብ ይጎዳል ያሉ ሲሆን ቅዳሜ ግንቦት 03/2016 ዓ.ም ለፖርቶ አሌግሬ ሊቀ ጳጳስ ጄይም ስፔንገር እና ለብራዚል ጳጳሳት ብሔራዊ ጉባኤ ፕሬዝዳንት ጥሪ አቅርቧል። ለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በአባትነት ስሜት የተሰማቸውን ስሜት የገለጹት ሊቀ ጳጳሱ፣ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ለሪዮ ግራንዴ ዶ ሱል ሕዝብ የሚያጽናና ቃል የገለጹበትን ጥሪ ማግኘታቸው እንዳስገረማቸው ተናግረዋል። "በዚህ አደጋ ለሚሰቃዩ ሁሉ አጋርነቴን እገልጻለሁ፣ እኔ ወደ በጸሎት ከእናንተ ጋር ነኝ ብለዋል።
ተጨባጭ እገዛ
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እሁድ ግንቦት 4 ቀን በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተገኙ ምዕመናን በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ ተንተርሰው ካደረጉት የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ በመቀጠል ባስተላለፉት ሳምንታዊ መልእክት መገባደጃ ላይ በከባድ ዝናብ ለተጎዱ ሰዎች አጋርነታቸውን ገልፀዋል። "ለግዛቱ ህዝብ ፀሎቴን ላረጋግጥላችሁ እፈልጋለሁ" ብለዋል ። የሪዮ ግራንዴ ዶ ሱል፣ ብራዚል፣ በከባድ ጎርፍ የተመታችው ጌታ የሞቱትን ይቀበላቸው፣ ቤተሰቦቻቸውን ጌታ መጽናናቱን ይስጣቸው ማለታቸው ተገልሷል።
ሊቀ ጳጳስ ስፔንገር በበኩላቸው የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ መንፈሳዊ ቅርበት ተጨባጭ በሆነ የገንዘብ ድጋፍ በተጨባጭ የእርዳታ ምልክት የታጀበ ነው ማለታቸውም ተገልጿል።