ፈልግ

Cookie Policy
The portal Vatican News uses technical or similar cookies to make navigation easier and guarantee the use of the services. Furthermore, technical and analysis cookies from third parties may be used. If you want to know more click here. By closing this banner you consent to the use of cookies.
I AGREE
የማታ ጸሎት በላቲን ቋንቋ
መርዐ-ግብር በድምጽ የቀረበ ዘገባ

ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ በዕርገቱ ኢየሱስ ወደ መንግሥተ ሰማያት ይመራናል ማለታቸው ተገለጸ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ዘወትር እሁድ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለሚሰበሰቡ ምዕመናን በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ ተንተርሰው አስተንትኖ እንደምያደርጉ ይታወቃል። በእዚህ መሰረት ቅድስነታቸው በግንቦት 04/2016 ዓ..ም ያደረጉት አስተንትኖ በእለቱ የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የክርስቲያን ማሕበረሰቦች ዘንድ ተክብሮ ባለፈው የዕርገት በዓል ላይ ትኩረቱን ያደረገ ሲሆን በዕርገቱ ኢየሱስ ወደ መንግሥተ ሰማያት ይመራናል ማለታቸው ተገልጿል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በወቅቱ ያደረጉትን የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ ሙሉ ይዘቱን እንደሚከተለው አሰናድተነዋል፣ ተከታተሉን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እሕቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

ዛሬ በጣሊያን እና በሌሎች ሀገራት የጌታ ዕርገት በዓል ይከበራል። በመስዋዕተ ቅዳሴው ሥነ-ሥረዓት ላይ የተነበበው ቅዱስ ወንጌል ኢየሱስ ሥራውን እንዲቀጥሉ ለሐዋርያት ተልዕኮውን አደራ ከሰጠ በኋላ "ወደ ሰማይ ዐረገ በእግዚአብሔርም ቀኝ ተቀመጠ" (ማር 16፡19) ይላል። ወንጌሉ እንዲህ ይላል፡- “ወደ ሰማይ ዐረገ በእግዚአብሔርም ቀኝ ተቀመጠ”።

የኢየሱስ ወደ አብ መመለሱ የሚያሳየን ከእኛ እንደተለየ ሳይሆን መዳረሻ ቦታችን ወደ ሆነው ወደ መንግሥተ ሰማይ ቀድሞን ሂዶ እንደሚጠብቀን ነው የምያሳየን።  ልክ በተራሮች ላይ አንድ ሰው ወደ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ሲወጣ፣ አንድ ሰው በእግር ይጓዛል፣ በችግር እና በመጨረሻም በመንገዱ ላይ መታጠፍ አድማሱ ይከፈታል እና ከእዚያም ወደ ተራራው ጫፍ ከወጣ በኋላ የምያስደስተውን ነገር ከላይ ሆኖ ማየት ይችላል። ከዚያም መላው አካል የመጨረሻውን መውጣት ለመቋቋም የሚያስችል ጥንካሬ ያገኛል። መላው አካል - ክንዶች፣ እግሮች እና እያንዳንዱ ጡንቻ - ወደ ላይ ይደርሳል እና ወደ ጫፍ ለመድረስ ያተኩራል።

እናም እኛ ቤተክርስቲያን ኢየሱስ ወደ መንግሥተ ሰማይ ካረገ በኋላ ከእርሱ ጋር እንደ ገመድ የሚጎትትበት አካል ነን። በቃሉ እና በቅዱስ ቁርባን ጸጋ፣ ወደምንመራበት የአገር ውበት፣ እኛን የሚያነቃን እና የሚያስተዋውቅ እርሱ ነው። ስለዚህም እኛ ደግሞ የእሱ አባላት - እኛ የኢየሱስ አባላት ነን - አንድ እርምጃ የሁሉም እርምጃ እንደሆነ እና ማንም መጥፋት ወይም ወደ ኋላ መቅረት እንደሌለበት አውቀን ከመሪያችን ጋር አብረን በደስታ እንወጣለን ምክንያቱም እኛ አንድ አካል ነን (ቆላ. 1:18፤ 1 ቆሮ 12:12-27)።

በጥሞና አዳምጡ፡ ደረጃ በደረጃ አንድ በአንድ መሮጥ ኢየሱስ መንገዱን ያሳየናል። እነዚህ መወሰድ ያለባቸው እርምጃዎች ምንድን ናቸው? የዛሬው ወንጌል እንደሚለን ያመኑ እና የተጠመቁ ሰዎች “ወንጌልን ይስበካሉ፣ ያጠምቃሉ፣ እባብ በእጃቸው ይይዛሉ፣ አጋናት ያስወጣሉ፣ በሕሙማን ላይ እጃቸውን ይጭናል፣ ያድናሉ” (ማር. 16፡16.18)፤ በማጠቃለያው የፍቅርን ሥራ መሥራት፡- ሕይወትን መስጠት፣ ተስፋን ማምጣት፣ ከማንኛውም ዓይነት ክፋትና ከክፋት መራቅ፣ ለክፋት በመልካም ምላሽ መስጠት፣ ለሚሰቃዩ ሰዎች ቅርብ መሆን። ይህ "ደረጃ በደረጃ" ነው የሚፈጸመው። ይህን ባደረግን ቁጥር ራሳችንን በመንፈስ እንድንለወጥ በፈቀድን መጠን የሱን አርአያ በተከተልን ቁጥር ልክ እንደ ተራራዎች በዙሪያችን ያለው አየር ቀላል እና ንጹህ ሆኖ ይሰማናል፣ አድማሱ ሰፊ እና መድረሻው ቅርብ ይሆናል። እናም ምልክቶች ጥሩ ይሆናሉ፣ አእምሮ እና ልብ ይስፋፋሉ እና ይተነፍሳሉ።

እናም እራሳችንን እንዲህ ብለን ልንጠይቅ እንችላለን፡ የእግዚአብሔር ፍላጎት፣ ወሰን ለሌለው ፍቅሩ፣ ለህይወቱ የዘላለም ህይወት ያለው ፍላጎት፣ በእኔ ውስጥ ሕያው ነውን? ወይስ ትንሽ ደንዝዤ እና ነገሮችን ለማለፍ፣ ወይም ገንዘብ፣ ወይም ስኬት፣ ወይም ተድላ ነው የምፈልገው? እናም ለመንግሥተ ሰማይ ያለኝ ፍላጎት እየጨመረ ይገኛል? ወይስ ወንድሞቼን እና እህቶቼን በትልቁ እና ከራስ ወዳድነት ነፃ በሆነ ልብ እንድወዳቸው፣ ወደ መንግሥተ ሰማይ በሚያደርጉት ጉዞ ላይ አጋሮቼ እንደሆኑ እንዲሰማኝ ያደርገኛል?

በመድረሻው ላይ የደረሰች ማርያም፣ በደስታ አብረን ወደ መንግሥተ ሰማያት ክብር እንድንሄድ ርሷ በአማላጅነቷ ትርዳን።

13 May 2024, 11:33

መልኣኩ ገብርኤል ማሪያምን አበሰራት የሚለው የቀርብ ጊዜ ጸሎት

ሁሉንም ያንብቡ >
Prev
February 2025
SuMoTuWeThFrSa
      1
2345678
9101112131415
16171819202122
232425262728 
Next
March 2025
SuMoTuWeThFrSa
      1
2345678
9101112131415
16171819202122
23242526272829
3031