ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ   (VATICAN MEDIA Divisione Foto)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት፡- ግጭቶች ሰላማዊ መፍትሄዎችን፣ ድርድሮችን ይፈልጋሉ ማለታቸው ተገለጸ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በእሁድ ሰኔ 16/2016 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ አስተንትኖ ካደረጉ በኋላ ለዓለም ባስተላለፉት ሳምንታዊ መልእክት መሪዎች በኃላፊነት መንፈስ እንዲሰሩ፣ ሰላም እንዲገነቡ እና ቀጣይ ግጭቶችን እና ጦርነቶችን በድርድር እንዲፈቱ ጥሪ አቅርበዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

"መንፈስ ቅዱስ የገዥዎችን አእምሮ ያብራ፣ ጥበብን እና የኃላፊነት ስሜትን ያሳድርባቸው፣ ግጭትን የሚያባብሱ ድርጊቶችን ወይም ቃላትን ይከላከሉ እና ይልቁንም ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት በቁርጠኝነት ይሥሩ” ሲሉ ቅዱስነታቸው ጥሪ አቅርበዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በእሁድ እለት “የእግዚአብሔር መልአክ ማርያምን ያበሰረበት” የብስራተ ገብርኤል ጸሎት ከምዕመናን ጋር በመቀባበል ከደገሙ በኋላ ባስተላለፉት ሳምንታዊ መልእክት በቅድስት ሀገር እና በዩክሬን የተከሰቱትን አሳዛኝ ክስተቶች በማስታወስ ግጭቶችን ለማሸነፍ "ድርድር ያስፈልጋል" ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ልዩ በሆነ መንገድ ዩክሬንን፣ ፍልስጤምን፣ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን እና እስራኤልን በማስታወስ "ለሰላም መጸለይን እንቀጥል" ሲሉ አሳስበዋል።

"ስለ ሰላም እንጸልይ"

"ስለ ሰላም እንጸልይ!" በማለት መልእክታቸውን የቀጠሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ "በጦርነት ለፈራረሰችው ዩክሬይን” በልዩ ሁኔታ መጸለይ ይኖርብናል ብለዋል። "ሰላም ይውረድ!" ገዢዎች በኃላፊነት መንፈስ እንዲንቀሳቀሱና ግጭቶችን እንዲያስወግዱ ጠይቀዋል።

24 June 2024, 14:16