ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ከሮም ሀገረ ስብከት ሦስተኛ ቡድን ካህናት ጋር ተገናኙ
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ማክሰኞ ከሰአት በኋላ ሰኔ 04/2016 ዓ.ም በሳሌዢያን ጳጳሳዊ ዩኒቨርሲቲ በዝማሬ እና በጊታር አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
ስብሰባው በዝግ በሮች የተካሄደው በዩኒቨርሲቲው አዳራሽ ውስጥ ነው። ስመተ ክህነት ከተቀበሉ ከ11 እስከ 39 ዓመታት ካስቆጠሩ ከሮማ ሀገረ ስብከት ካህናት ጋር ሦስተኛው እና የመጨረሻው ስብሰባ ቅዱስነታቸው አካሂደዋል።
በግንቦት 7/2016 ዓ.ም በቅዱስ ጁሴፔ አል ትሪንፋሌ ደብር ስመተ ክህነት ከተቀበሉ ከ10 እአስከ 40 ዓመታት በላይ አገልግሎት ካስቆጠሩ ከካህናት እና ከሊቀ ካህናት ጋር በመለኮታዊ ጻድቃን ደቀ መዛሙር ቤት የተደረገውን ተመሳሳይ ስብሰባ ተከትሎ ነበር ይህ ግንኙነት የተከናወነው።
የሮማ ሀገረ ስብከት "ምሰሶዎች"
160ዎቹ ካህናት፣ የሰበካ ካህናት፣ አስተዳዳሪዎች፣ ቀሳውስት እና የኩሪያ ቢሮ ዳይሬክተሮች፣ ጥያቄያቸውን በነፃነት እንዲጠይቁ ከሊቀ ጳጳሱ ግብዣ ተቀብለዋል። የተገኙት ጳጳስ ሚሼል ዲ ቶልቭ በበጎ አድራጎት ዘርፍ ያላቸው ሚና፣ ነገር ግን በትምህርት ቤቶች፣ በማረሚያ ቤቶች እና በሆስፒታሎች ውስጥም የሀገረ ስብከቱ ምሰሶዎች በማለት ገልጸዋቸዋል።
ኤጲስ ቆጶስ ዲ ቶልቭ የዲያቆናት፣ ቀሳውስትና ሃይማኖታዊ ሕይወት ልዑካን ሲሆኑ ጉባኤውን ከጳጳሱ ጋር ያስተዋወቀው ከጸሎትና ከዕለቱ ወንጌል ንባብ በኋላ ነበር።
ሰላምታ ለትምህርት ተቋሙ ማሕበረሰብ
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ለትምህርት ተቋሙ ማህበረሰብ አባላት፡ ፕሮፌሰሮች (የ96 አመት አዛውንት ቄስ ጨምሮ)፣ ተማሪዎች እና ተባባሪዎች ሰላምታ ለመስጠት አስራ አምስት ደቂቃ ያህል ቆይተው ወደ ሳሌዥያን አዳራሽ ገቡ።
ከካህናቱ ጋር ውይይት
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በወቅቱ የነበሩትን ችግሮች ለማሰላሰል ከካህናቱ ጋር በተደረገው ስብሰባ ወረርሽኙ በሚያስከትላቸው መዘዞች ፣በከፋ ድህነት ፣ ጦርነት እና ፍልሰት ፣ የወጣቶች ድንገተኛ አደጋዎች - ከተማዋን ወደ “ተልእኮ ግዛት በመቀየር" ላይ የሚገኙ ተግዳሮቶች በመሆናቸው ለእዚህ ዝግጅት እንደሚያስፈልግ ቅዱስነታቸው በአጽኖት ገልጸዋል።