የኢየሱስ ቅዱስ ልብ የኢየሱስ ቅዱስ ልብ 

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በቅዱስ ልብ ላይ 'ልቡን ላጣው' ዓለም ሰነድ ሊጽፉ ነው መባሉ ተገለጸ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በመስከረም ወር ላይ በኢየሱስ ቅዱስ ልብ ላይ የሚያጠነጥን ሰነድ ይፋ እንደሚያደርጉ ተገልጿል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ- ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ “የቤተ ክርስቲያንን የመታደስ መንገድ ለማብራት፣ ነገር ግን ልቡ የጠፋ ለሚመስለው ዓለም ትልቅ ነገር ለመናገር” ለዚያ አምልኮ የተዘጋጀ ሰነድ ለመጻፍ መዘጋጀታቸውን አስታውቀዋል።

ሳምንታዊውን አጠቃላይ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ለመታደም ለተገኙት ምዕመናን ቅዱስነታችው ባደረጉት ንግግር በሰኔ ወር የመጀመሪያ የሆነው፣ ለኢየሱስ ቅዱስ ልብ የተወሰነው ወር - እ.አ.አ ባለፈው ታህሳስ 27/2024 ዓ.ም የቅድስት ማርጋሬት ማርያም አላኮክ የኢየሱስ የተቀደሰ ልብ ራእይ የመጀመሪያውን 350ኛ አመት እንዳከበሩ አስታውሰዋል።

በዚህ እለት በብዙ የአለም ሀገራት የዚህ አምልኮ በዓላት መጀመራቸውን እና በሚቀጥለው አመት እ.አ.አ ሰኔ 27/2025 ዓ.ም እንደሚያጠናቀቁም ተናግረዋል።

በዚህ ምክንያት፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እንዳሉት፣ “ከቀደሙት መፃሕፍቶች ውድ ነጸብራቆችን እና ከቅዱሳት መጻህፍት ጀምሮ ያለውን ረጅም ታሪክ የሚሰበስብ ሰነድ ዛሬ ወደ መላው ቤተክርስቲያን ይህን መንፈሳዊ ውበት የተሞላውን አምልኮ ለማስተዋወቅ የሚያስችል ሰነድ እየተዘጋጀ ነው” ማለታቸውም ተገልጿል።

“የቤተ ክርስቲያንን የመታደስ ጎዳና ሊያበሩ በሚችሉ የጌታ ፍቅር ገጽታዎች ላይ ማሰላሰላችን በጣም ጠቃሚ እንደሚሆን አምናለሁ። ግን ደግሞ ልቡ የጠፋ ለሚመስለው አለም ትልቅ ነገር ለመናገር ያሰበ ሰነድ ነው” ብሏል።

ስለዚህም ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ይህንን ሰነድ በሚቀጥለው መስከረም ለሕዝብ ይፋ ለማድረግ በማሰብ በዚህ የዝግጅት ጊዜ ምእመናን በጸሎት እንዲያጅቧቸው ጠይቀዋል።

ስለ ሰላም ጸሎቶች

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ምእመናን አብረዋቸው እንዲጸልዩ ጠይቀዋል።

"ጌታን ስለ እናቱ አማላጅነት ለሰላም እንለምናለን" በማለት ብዙ ጊዜ እንደሚያደርጉት ጸሎታቸውን "በተሰቃየችው ዩክሬን ሰላም፣ ፍልስጤም ውስጥ ሰላም፣ እስራኤል ሰላም፣ በምያንማር...." በማለት ቅዱስነታቸው ስለሰላም ተማጽነዋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ "ጌታ የሰላም ስጦታን እንዲሰጠን እና ዓለም በጦርነት እንዳይሰቃይ እንጸልይ" ካሉ በኋላ መልእክታቸውን አጠናቀዋል።

 

05 June 2024, 14:42