ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በፖርቱጋል የዓለም የወጣቶች ቀን በተከበረበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በፖርቱጋል የዓለም የወጣቶች ቀን በተከበረበት ወቅት  (AFP or licensors)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ 'ወጣትነታችሁ ለኢየሱስ ስጦታ ይሁን' ማለታቸው ተገለጸ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በፓራጓይ ለተሰበሰቡት የወጣት አገልጋዮች ስብስብ ባስተላለፉት መልእክት፣ ወጣት ምዕመናን ክርስቶስ እንዲለውጣቸው እና ወጣትነታቸውን 'ለኢየሱስ እና ለአለም ስጦታ አድርገው እንዲኖሩ' ጥሪ አቅርበዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

"ወጣትነታችሁ ለኢየሱስ እና ለአለም ስጦታ ይሆን ዘንድ፣ ህይወታችሁን ዋጋውን በጠበቀ እና ፍሬያማ በሆነ መልኩ አሳልፉ፣ ክርስቶስ የተፈጥሮ ብሩህ ተስፋችሁን ወደ እውነተኛ ፍቅር ይለውጠው፤ መስዋዕትነትን የሚያውቅ ፍቅር ይኑራችሁ፣ ቅን፣ ሕይወታችሁ ፍሬያማ እንዲሆን፣ እውነተኛና በተገባ መንገድ ኑሩ" ማለታቸው ተገልጿል።

ይህን ማበረታቻ ነበር ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እ.አ.አ ከሐምሌ 15-20/2024 ዓ.ም በአሱንቺዮን፣ ፓራጓይ ለተሰበሰበው የካሪቢያን እና የላቲን አሜሪካ ብሔራዊ የወጣቶች አገልግሎት መሪዎች ስብሰባ ላይ ባስተላለፉት መልእክት የገለጹት።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ለተሳታፊዎቹ የሰላምታ መልእክት በማቅረባቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው፣ ወጣቶች ክርስቶስ ኃይላቸውን ተጠቅመው ታላላቅ ሥራዎችን እንዲሠሩ ጠይቀው፣ የወጣቶች አገልግሎት ለቤተ ክርስቲያን ያለውን ጥቅም አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

“የኢየሱስ ‘ተነሣ’ የሚለው ትእዛዝ ሥራንም ኃላፊነትንም ያመለክታል” በማለት ተናግሯል።

እግዚአብሔርን አትፍሩ

"በእኛ በኩል የሚያልፈውን በጆሮአችን የሚያንሾካሾከውን፣ ወደ እኛ ጎንበስ ብሎ በወደቅንበት ጊዜ ሁሉ እጁን የሚዘረጋልንን ጌታን አትፍሩ" በማለት በመልእክታቸው የተናገሩት ቅዱስነታቸው ኢየሱስ "በእግራችን" እንድንቆም ይፈልጋል” በማለት ተናግረዋል። "ተነሥቷል" እና ስለዚህ "ወደ ህይወታችሁ እንዲገባ ለማድረግ መፍራት የለብንም" ያሉት ቅዱስነታቸው "የልባችሁን ደጆች ለእርሱ ክፈቱለት፣ ከእርሱ ለሚመጣው አዲስ ሕይወት ልባችሁን ዝግጁ አድርጉ" ማለታቸው ተገልጿል።  

"በአጠገባችን የሚያልፈውን፣ በጆሮአችን የሚንሾካሾከውን፣ ወደ እኛ ጎንበስ የሚለውን፣ በምንወድቅበት ጊዜ ሁሉ እጁን የሚዘረጋልንን እግዚአብሔር አትፍሩ” ሲሉ በድጋሚ ተናግረዋል።

ማርያም በእናትነት ፍቅር አብራን ትጓዛለች

ቅዱስ አባታችን በመቀጠል የተሰበሰቡትን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አደራ ሰጥተዋል።

ከልጆች፣ ከአዋቂዎችና ከአረጋውያን ጋር በየትውልድ ኅብረት እንዲኖራቸው፣ እርሷ ማለትም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በጉዞዋችሁ ታጅባችሁ ዘንድ፣ በእናትነት ፍቅር ታማልድላችሁ ዘንድ፣  ሲኖዶሳዊ፣ ደቀ መዝሙር የምትሆኑ በቤተክርስቲያን ውስጥ ዋና ተዋናዮች እንድትሆኑ እና ሚስዮናዊ መንፈስ እንድታዳብሩ እርሷ በማልጅነት ትርዳችሁ" ብለዋል።

በመጨረሻም ቅዱስነታቸው በተለየ መንገድ "ይህ ስብሰባ እንዲሳካ በትጋት የሰሩትን ወጣት ፓራጓውያንን አመሰግናለሁ" ካሉ በኋላ ንግግራቸውን አጠናቀዋል።

18 July 2024, 15:33