ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ከዓለም አቀፍ የመንበረ ታቦት አገልጋዮች ጋር በተገናኙበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ከዓለም አቀፍ የመንበረ ታቦት አገልጋዮች ጋር በተገናኙበት ወቅት   (VATICAN MEDIA Divisione Foto)

ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ ለመንበረ ታቦት አገልጋዮች 'ኢየሱስን ለሌሎች አካፍሉ' ማለታቸው ተገለጸ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የኢየሱስን የቅዱስ ቁርባን ፍቅር ለተቸገሩት እንዲያካፈሉ ለአለም አቀፍ የመንበረ ታቦት አገልጋዮች መንፈሳዊ ተጓዢ ተሳታፊዎችን ጥሪ ማቅረባቸው ተገለጸ።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ወደ 50,000 ለሚጠጉ የዓለም አቀፍ የመንበረ ታቦት አገልጋዮች አባላት ባደረጉት ንግግር “ከአንተ ጋር” (ኢሳ 41፡10) በሚል አርዕስት ለዓለም አቀፉ ዝግጅት የተመረጠው መሪ ቃል ጥልቅ ትርጉሙን አጉልተው ነበር የተናገሩት።

ይህ አገላለጽ “የሕይወታችን ምስጢር የሆነውን የፍቅርን ምስጢር ያጠቃልላል” ብሏል።

የመንበረ ታቦት አገልጋዮች ከጳጳሱ ጋር በአደባባዩ ተሰብስበው ነበር፣ ለሳምንት የሚቆይ የሮም ጉዞ አካል የሆነው፣ አሁን ሁለተኛው ቀኑ ነው።

ከእግዚአብሔር ጋር መሆን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በሚያገለግሉበት ሥርዓተ ቅዳሴ፣ እነዚህ ሁለት ቃላት በመጀመሪያ የሚያመለክቱት በቅዱስ ቁርባን ውስጥ፣ “በክርስቶስ ሥጋና ደም ውስጥ እውነተኛና ተጨባጭ ሕልውና የሆነውን እግዚአብሔርን ነው” ብለዋል።

“መስዋዕተ ቅዳሴን የማገልገል ልምድ የመጀመሪያው ርዕሰ ጉዳይ፣ የዚህ ‘ከአንተ ጋር’ ወኪል የሆነው አምላክ እንደሆነ ያስታውሰኛል ብለዋል።

 ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ “ቅዱስ ቁርባንን ስንቀበል፣ ኢየሱስ ‘ከእኛ ጋር’ በመንፈሳዊም ሆነ በሥጋዊ፣ በቃላት ሳይሆን በዚያ “የፍቅር ተግባር ማለትም በቅዱስ ቁርባን” ውስጥ መሆኑን እንለማመዳለን ሲሉ ተናግረዋል።

ኢየሱስ ከእኛ ጋር ስለሆነ በእውነት ከእርሱ ጋር መሆን እንችላለን

በቅዱስ ቁርባን ውስጥ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በመቀጠል እንደ ተናገሩት ከሆነ የመንበረ ታቦት አገልጋዮች “ጌታ ኢየሱስን ‘ከአንተ ጋር ነኝ’ ሊሉት የሚችሉት በቃላት ብቻ አይደለም፣ ነገር ግን በልብና በአካል፣ በፍቅር ጭምር ሊሆን ይገባዋል” ያሉ ሲሆን በትኩረት በአእምሮ፣ በልብ እና በአካል በማገልገል፣ “ከእናንተ ጋር ያለው የእግዚአብሔር ምሥጢር በአዲስ መንገድ ከሌሎች ጋር እንድትሆኑ የሚያስችል አቅም ይሰጣችኋል” በዚህም “እኔ እንደ ወደድኳችሁ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ” የሚለውን ትእዛዙን ይፈጸማል" ሲሉ ተናግረዋል።

"የኢየሱስ 'ከአንተ ጋር'፣ ለፍቅሩ ምስጋና ይግባውና፣ ለሌሎች የምናካፍለው የእኔ፣ ያንተ፣ የእኛ 'ከአንተ ጋር' ይሆናል ሲሉ አጽኖት ሰጥተው ተናግረዋል።

ከባልንጀሮቻችን ጋር መቀራረብ

ስለዚህ ከኢየሱስ ጋር መሆን ከባልንጀሮቻችን ጋር መቀራረብንን ያመላክታል፣ “በቃል ሳይሆን በተግባር፣ በምልክት፣ በልባችሁ”፣ ከእኛ ለሚለዩት እንኳን “ወደ ማንወዳቸው”፣ ለባዕድ አገር ዜጎች፣ “አይረዱንም ብለን ለምናስባቸው ሰዎች” ወደ ቤተ ክርስቲያን ፈጽሞ ለማይመጡ፣ በአምላክ አናምንም ከሚሉት ሁሉ ጋር የወንድማምችነት መንፈስ ማጠናከር ይኖርብናል ብለዋል።

በማጠቃለያው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እንዲህ ያለ ትርጉም ያለው መሪ ቃል ስለመረጡ አዘጋጆቹን አመስግነዋል፣ ምእመናን ደግሞ ወደ ሮም በመምጣታቸው “የኢየሱስ መሆን ደስታን ለመካፈል፣ የፍቅሩ አገልጋዮች በመሆናችን፣ ቁስላችንን የሚፈውስ፣ የቆሰለው የኢየሱስ ልብ አገልጋዮች ናችሁ። ከሞት እንድንድን እርሱም የዘላለም ሕይወትን ይሰጠናል ብለዋል።

31 July 2024, 10:39