ር.ሊ.ጳ. በፖላንድ መንፈሳዊ ንግደት እያደረጉ የሚገኙትን ሴቶች ወንጌልን በደስታ እንዲመሰክሩ አበረታ
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እሁድ ነሐሴ 12/2016 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ከተሰበሰቡ ምዕመናን ጋር የመልአከ እግዚአብሔርን ጸሎት ከደገሙ በኋላ በፖላንድ አገር በሚገኘው በፒካሪ ሳልኬይ በሚገኘው የማርያም በተመቅደስ ባሕላዊ እና መንፈሳዊ በሆነ መልኩ በተካሄደው መንፈሳዊ ንግደት ላይ ለተሳተፉት ሁሉ መልእክት ማስተላለፋቸው ተገልጿል።
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በእሁድ ነሐሴ 12/2016 ዓ.ም ላይ "በቤተሰብ እና በማህበረሰቡ ውስጥ በደስታ ወንጌልን መስክሩ" ሲሉ በፒካሪ ሳልኬይ የማርያም ቤተመቀድስ በተደርገው መንፈሳዊ ንግደት ላይ ለተሳተፉ በአስር ሺዎች ለሚቆጠሩ ልጃገረዶች እና ሴቶች የሰላምታ መልእክት ልከዋል። ይህ የአምልኮ ቦታ በ17ኛው ክፍለ ዘመን በማርያም ስም የተሰየመ ቦታ ነው፥ በባህሉ መሠረት የወንዶች መንፈሳዊ ንግደት የሚካሄደው በግንቦት ወር ሲሆን የሴቶች መንፈሳዊ ንግደት ደግሞ በነሐሴ ወር ይካሄዳል።
ዘንድሮም ብፁዕ ካርዲናል ገርሃርድ ሙለር መስዋዕተ ቅዳሴውን መርተው አስተምህሮአቸውን ያቀረቡ ሲሆን በዕለቱም “በኢየሱስ መስቀል ሥር መቆም እንጂ በፍርሃት አለመሸሽ እውነተኛ ክርስቲያን የሚያደርገው ነገር ነው” ሲሉ አሳስበዋል። አክለውም በመስቀል ሥር ያሉት የሴቶች ትዕይንት የሴቶችን ልዩ ውለታ ያሳየናል ወይም ደግሞ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ እንዳመለከቱት የሴቶች ሃይማኖታዊ አዋቂነት ነው ሲሉ ተናግረዋል።
19 August 2024, 10:36