በኮንጎ በጎማ ውስጥ በተፈናቃዮች ካምፖች ውስጥ የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ የመከላከል ሂደት የሚያሳይ ምስል በኮንጎ በጎማ ውስጥ በተፈናቃዮች ካምፖች ውስጥ የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ የመከላከል ሂደት የሚያሳይ ምስል   (ANSA)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በዝንጀሮ ፈንጣጣ ለሚሰቃዩ ሰዎች ጸሎት ማድረጋቸው ተገለጸ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እሁድ ነሐሴ 19/2016 ዓ.ም ከመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት በመቀጠል ባስተላለፉት ሣምንታዊ መልእክት እደገለጹት በዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ ለሚሰቃዩ ሰዎች በተለይም በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ወረርሽኙን በመታገል ላይ ከሚገኙት እና አሁን የአለም የጤና ድንገተኛ አደጋ ላለባቸው ሰዎች ያላቸውን አጋርነት ገልጸዋል። ለኒካራጓ ሕዝብ ያላቸውን ድጋፍ በመግለጽ በኢየሱስ ላይ ያላቸውን ተስፋ እንዳያጡ ጥሪ አቅረበዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

እሁዱ በመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ማጠቃለያ ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በዓለም አቀፍ ደረጃ በሜምፖክስ (የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ) ለተጠቁ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ያላቸውን ቅርበት የገለጹ ሲሆን ይህም አሁን የዓለም አቀፍ የጤና ድንገተኛ አደጋ ነው ። በተለይ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ወረርሽኙ የተስፋፋ ባለበት በዚህ ወቅት ይህ በሽታ ላለባቸው ሰዎች ሁሉ ጸሎት እያደረጉ መሆናቸውን ቅዱስነታቸው ገልጿል።

"በዚህ በሽታ በጣም በተጠቁ አገሮች ውስጥ ላሉት አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት የተሰማኝን ሀዘኔን እገልጻለሁ እናም መንግሥታት እና የግል ኢንዱስትሪዎች ማንም ሰው በቂ የህክምና አገልግሎት እንድያገኝ ያላቸውን ቴክኖሎጂ እና ህክምና እንዲያካፍሉ አበረታታለሁ" ሲሉ ተናግረዋል።

ለኒካራጓ ጸሎት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በተጨማሪም "የተወደዳችሁ የኒካራጓ ሕዝቦች" በኢየሱስ ላይ ያላችሁን ተስፋ በድጋሚ አድሱ ሲሉ የማበረታቻ ቃላትን አቅርበዋል።

“መንፈስ ቅዱስ ሁል ጊዜ ታሪክን ወደ ከፍተኛ ፕሮጀክቶች እንደሚመራ አስታውስ። ንጽሕት ድንግል በፈተና ጊዜ ትጠብቃችሁ የእናትነት ርኅራኄዋን እንዲሰማችሁ ትርዳችሁ። እመቤታችን ከተወዳጁ የኒካራጓ ሕዝብ ጋር ትሁን" ካሉ በኋላ መልእክታቸውን ደምድመዋል።

 

26 August 2024, 10:13