ፈልግ

በማዕከላዊ ጋዛ ሰርጥ በዲር አል ባላህ የእስራኤል ጥቃት ከተፈጸመ በኋላ ያስከተለውን ጉዳት የምያሳይ ምስል በማዕከላዊ ጋዛ ሰርጥ በዲር አል ባላህ የእስራኤል ጥቃት ከተፈጸመ በኋላ ያስከተለውን ጉዳት የምያሳይ ምስል  (REUTERS)

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በመካከለኛው ምሥራቅ ያለውን አለመግባባት ለማጥፋት ሰላም እንዲሰፍን ጸለዩ!

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ሮብዕ ነሐሴ 1/2016 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው የጳውሎስ 6ኛ የመሰብሰቢያ አዳርሽ ሳምንታዊውን የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ካጠናቀቁ በኋላ ቅዱስነታቸው በመካከለኛው ምሥራቅ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ተማጽነዋል፣ በዩክሬን፣ ምያንማር እና ሱዳን ሰላም እንዲሰፍን፣ በፓኪስታን እና አፍጋኒስታን ያለው የዘር መድሎ እንዲቆም ከፍተኛ ጥረት እና ጸሎት እንዲደረግ ጠይቀዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ረቡዕ አጠቃላይ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ለታደሙ ምእመናን “ሰላምን እንዲሹ፣ ጠብን እንዲተው፣ ፍቅር ጥላቻን እንዲያሸንፍ እና በቀል በይቅርታ እንዲፈታ እጸልያለሁ” ብለዋል።

በመካከለኛው ምሥራቅ ያለውን ሁኔታ “በታላቅ ጭንቀት” መከታተሌን እቀጥላለሁ ያሉት ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮ አፋጣኝ የተኩስ አቁም ጥያቄያቸውን ደጋግመው አቅርበዋል “ከጋዛ ጀምሮ በሁሉም ረገድ ሰብዓዊ ሁኔታው ​​በጣም አሳሳቢ ነው፣ ጦርነት በዘላቂነት ሊፈታ ይገባዋል” ብለዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለጠቃላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ታዳሚዎች እና ምእመናን “በጦርነት ለተሰቃዩት ዩክሬን፣ ለማያንማር እና ሱዳን” ጸሎታቸውን ማቅረብ እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።

እ.ኤ.አ. በ 2014 ክሬሚያ በህገ-ወጥ መንገድ በራሻ ጦር ወደ ራሻ ግዛት ከተጠቃለለች በኋላ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተገድለዋል ወይም ቆስለዋል ፣ እና በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ዜጎች ተፈናቅለዋል ፣ ይህም በዶንባስ ግጭት እና በኋላም በ 2022 ሩሲያ በዩክሬን ላይ ሙሉ ወረራ ከፈጸመች በኋላ የተከናወነ ነው።

እ.አ.አ በየካቲት 2021 ዓ.ም ታትማዳው (የሀገሪቱ ጦር) በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠውን መንግሥት ካስወገደ በኋላ የእርስ በርስ ጦርነት ማያንማር ውስጥ ተጀመረ። በተከተለው ጦርነት ቢያንስ 50,000 ሰዎች ሞተዋል፣ 8,000 ንፁሀን ዜጎችን ጨምሮ፣ 2.3 ሚሊዮን ሰዎች ደግሞ ተፈናቅለዋል።

በሱዳን ደግሞ ከ13,000 እስከ 15,000 የሚደርሱ ሰዎች ሲሞቱ ከ33,000 በላይ ቆስለዋል እ.አ.አ ከሚያዚያ 2023 ዓ.ም ጀምሮ በተቀናቃኞቹ ወታደራዊ ቡድኖች መካከል የእርስ በርስ ጦርነት ሲካሄድ ቆይቷል። ወደ 7.7 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች በአገር ውስጥ ተፈናቅለዋል፣ ከ2 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ደግሞ ከሀገር ወጥተው ተሰደዋል።

"እነዚህ በጦርነት የተሞከሩ ህዝቦች በቅርቡ በጣም የሚፈለጉትን ሰላም ያገኙ ዘንድ ይሁን" ሲሉ ቅዱስነታቸው ተናግሯል፣ "እነዚህ በጦርነት የተሞከሩ ህዝቦች በጣም የሚፈለገውን ሰላም በቅርቡ ያግኙ" ሲሉ በድጋሚ ተማጽነዋል።

በፓኪስታን እና አፍጋኒስታን ውስጥ እየተሰራፋ የሚገኘው የዘር መድልዎ እንዲቆም ቅዱስነታቸው ጥሪ አቅርበዋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በተጨማሪም “በፓኪስታን እና አፍጋኒስታን ክልሎች የዘር መድልዎ በተለይም በሴቶች ላይ የሚደርሰው መድልዎ እንዲወገድ” እንደገና ጥረቶችን እና ጸሎቶች እንዲደረጉ ጠይቀዋል።

08 August 2024, 08:18

በቅርብ ጊዜ ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጋር የተደረገው ግንኙነት

ሁሉንም ያንብቡ >