ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በ2ኛው የዓለም ጦርነት የፈነዱ አቶሚክ ቦምቦችን ማስታወስ ጸሎት አደረጉ!
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የፈነዱትን የአቶሚክ ቦምቦችን በማስታወስ በጦርነት ውስጥ የሚገኙ አገሮች ውስጥ ሰላም እንዲሰፍን ጥሪ አቅርበዋል። ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በጦርነት በፈራረሱ አገሮች እና ቦታዎች የሰላም ጥሪያቸውን በማደስ በብራዚል በተከሰከሰው የመንገደኞች አይሮፕላን አደጋ ሰለባዎችም ጸሎት ማድረጋቸው ተገልጿል።
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
“በተለይ ሰማዕት በሆነችው ዩክሬን፣ መካከለኛው ምስራቅ፣ ፍልስጤም፣ እስራኤል፣ ሱዳን እና ምያንማር የሰላም ጸሎታችንን እናድስ" ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የተናገሩ ሲሆን ይህንን የተናገሩት ደግሞ እሁድ ነሐሴ 05/2016 ዓ.ም በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ከተካሄደው ከመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት በፊት ባቀረቡት ጥሪ ነው።
ሁሉም ሰው "ለእነዚያ ክስተቶች እና ጦርነቶች ሁሉ ሰለባዎች" እንዲጸልዩ ጋብዟል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ባለፈው አርብ በብራዚል ሳን ፓውሎ ግዛት በደረሰው የአውሮፕላን አደጋ ለሞቱት 61 ሰዎች ጸሎት አቅርበዋል።
12 August 2024, 08:21