ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ፥ “ኢየሱስ ክርስቶስ ከዲያብሎስ የማታለል ሴራ ይጠብቀናል!”
“ኢየሱስም በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ ከዮርዳኖስ ተመለሰ፥ በምድረ በዳም በመንፈስ ተሞላ። ለአርባ ቀን በዲያብሎስ ተፈተነ። በእነዚያም ቀኖች ምንም አልበላም፤ ቀኖቹም በተፈጸሙ ጊዜ ተራበ። ዲያቢሎስም ፈተናውን ሁሉ ከጨረሰ በኋላ ለጊዜው ከእርሱ ተለየ። ኢየሱስም በመንፈስ ኃይል ወደ ገሊላ ተመለሰ፤ ስለ እርሱም በዙሪያው ባለው አገር ሁሉ ተወራ” (ሉቃ. 4: 1-2 ፣ 13-14)።
ክቡራት ክቡራን፥ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተገኙት ምዕመናን ያቀረቡት ሳምንታዊ አስተምህሮ ትርጉም ጠቅላላ ይዘት ከዚህ ቀጥሎ እናቀርብላችኋለን፥
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን
“ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ! ኢየሱስ ክርስቶስ በዮርዳኖስ ወንዝ ከተጠመቀ በኋላ ወዲያውኑ ‘በዲያብሎስ ይፈተን ዘንድ መንፈስ ወደ ምድረ በዳ ወሰደው’ (ማቴ 4: 1)። አነሳሱ የሰይጣን ሳይሆን የእግዚአብሔር ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምድረ በዳ በመሄዱ የመንፈስ ቅዱስን ፍላጎት ታዘዘ እንጂ በጠላት ወጥመድ ውስጥ አልወደቀም። ይህን ፈተና ካለፈ በኋላ ‘በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ወደ ገሊላ ተመለሰ’ ተብሎ ተጽፎአል (ሉቃ. 4፡14)።
ኢየሱስ ክርስቶስ በምድረ በዳ ራሱን ከሰይጣን ነፃ ካወጣ በኋላ ራሱን ነጻ ማድረግ ይችላል። ወንጌላውያን በብዙ የተጨናነቁ ሰዎች የነጻነት ታሪክን ጉልህ ያደረጉት በዚህ ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ ለተቃዋሚዎቹ እንዲህ አለ፡- ‘እኔ አጋንንትን በብኤልዜቡል የማወጣ ከሆነ፣ ልጆቻችሁ በማን ያስወጡአቸዋል’ (ማቴ 12፡27)።
በዛሬው አስተምህሮአችን ዲያቢሎስን በተመለከተ አንድ እንግዳ ክስተት እንመለከታለን። በተወሰነ የባሕል ደረጃ ሰይጣን እንደሌለ ይታመናል። ይህም የጋራ ንቃተ ህሊና ማጣት፣ የመነጠል ምልክት ወይም በአጭሩ ዘይቤ ነው። ነገር ግን ሻርል ባውዴሊየ የተባለ አንድ ሰው እንደጻፈው፥ ‘የዲያብሎስ ትልቁ ተንኮል ሰዎች እርሱ እንደሌለ እንዲያምኑ ማድረግ ነው’። ሆኖም ዓለማችን በአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች፣ በአስማተኞች፣ በመናፍስታዊ ድርጊቶች፣ በኮከብ ቆጣሪዎች፣ በክታብ ሻጮች እና ሰይጣንን በሚከተሉ ቡድኖች የተሞላ ነው። ዲያብሎስ ከተባረረ በኋላ ተመልሶ በመስኮት በኩል ሊናገር ይችላል። በእምነት ኃይል ቢባረርም በአጉል አምልኮ በኩል ተመልሶ ይመጣል።
የሰይጣንን መኖር ጠንካራ ማረጋገጫ ማግኘት የሚቻለው በኃጢአተኞች ወይም እርሱ በገባባቸው ሰዎች ውስጥ ሳይሆን በቅዱሳን ውስጥ ነው! እውነት ነው ዲያብሎስ በየአካባቢያችን በምናያቸው ጽንፍ እና ኢ-ሰብዓዊ በሆኑ የክፋት ዓይነቶች በኩል ሥራውን እየሠራ ይገኛል። ነገር ግን በዚህ መንገድ ድርጊቱ የት እንደሚያበቃ እና የራሳችን ክፋት የት እንደሚጀመር በትክክል ማወቅ አይቻልም። በግል ጉዳዮችም ቢሆን በእርግጥ እሱ መሆኑን በእርግጠኝነት መናገር አይቻልም። በዚህ ምክንያት ቤተ ክርስቲያን አጋንንትን የማስወጣት ሥራን በተመለከተ በጣም አስተዋይ እና ጠንካራ ናት። በአንዳንድ ፊልሞች እንደምንመለከተው አይደለም!
ዲያብሎስ ለመደበቅ ቢሞክርም በቅዱሳን ሕይወት ወደ አደባባይ ይወጣል። ይብዛም ይነስ ሁሉም ቅዱሳን እና ታላላቅ አማኞች ከዚህ ከጨለማ እውነታ ጋር ያደረጉትን ተጋድሎ ይመሰክራሉ። ነገር ግን ሁሉም በዘመናቸው በነበራቸው ጭፍን አመለካከት የተታለሉ ወይም ሰለባዎች እንደሆኑ በትክክል መገመት አይቻልም።
ከክፉ መንፈስ ጋር የሚደረግ ትግል ኢየሱስ ክርስቶስ በምድረ በዳ ድልን ከተቀዳጀው፥ እግዚአብሔርም በቃሉ እንደተናገረው፥ ሦስት ጊዜ ምላሽ የሰጠውም በዚህ መንገድ ነው። ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ኢየሱስ ክርስቶስ ሳይሆን ነገር ግን እኛ መንቃት እንዳለብን ይነግረናል፡- ‘በመጠን ኑሩ፣ ንቁም! ጠላታችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን በመፈለግ እንደሚያገሣ አንበሳ ዙሪያውን ይንጎራደዳል’ (1ኛ ጴጥሮስ 5፡8)። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም በበኩሉ፡- ‘ለዲያብሎስ ሥፍራ አትስጡት’ (ኤፌ 4፡27) በማለት ያስጠነቅቃል።
ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀሉ የዚህን ዓለም አለቃ ኃይል ለዘላለም አሸንፏል (ዮሐ. 12.31)። አንድ የቤተ ክርስቲያን አባት እንዳሉት፥ ‘ዲያብሎስ በሰንሰለት እንደ ውሻ ታስሯል፤ አደጋን በመቃወም ወደ እርሱ ከሚቀርቡት በቀር ማንንም መንከስ አይችልም... ይጮኻል፣ ይለምናል፣ ነገር ግን ወደ እርሱ ከሚጠጉት በቀር ሌሎችን መንከስ አይችልም’።
ለምሳሌ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ አድናቆት ሊቸረው ከሚገባው በርካታ አዎንታዊ ግብአቶች በተጨማሪ፥ ዲያብሎስ ዕድል ሊያገኝ የሚችልባቸውን ሥፍር ቁጥር የሌላቸው መንገዶችን ያቀርባል። በዚህም ብዙዎች ተሳስተው ይወድቃሉ። ዘመናዊ የመገናኛ ቴክኖሎጂ ብዙ የተለያዩ የድምጽ እና የምስል መልዕክቶች የሚቀርቡበት ሰፊ ‘ገበያ’ ነው። በድረ ገጽ አማካይነት የሚተላለፉ አስነዋሪ የወሲብ ፊልሞችን እንደ ምሳሌ እንውሰድ። ይህ በዓለማችን በጣም የተስፋፋ ክስተት ነው። ክርስቲያኖች ጥንቃቄን በማድረግ በኃይል ሊቃወሙት ይገባል።
በታሪክ ውስጥ የዲያብሎስ ድርጊት ተስፋ ሊያስቆርጠን አይገባም። በዚህ ጉዳይ ላይ የመጨረሻው ሃሳብ, እምነት ማጠንከር እና የራስን ደህንነት መጠበቅ መሆን አለበት። ኢየሱስ ክርስቶስ ዲያብሎስን አሸንፎ እኛም ድሉን የራሳችን እናደርገው ዘንድ መንፈሱን ሰጠን። የእግዚአብሔር ዕርዳታ ለመንጻታችን አገልግሎት ካደረግነው ጠላት ለርሱ ጥቅም ሊያውለው ይችላል። ስለዚህም በዝማሬአችን፥
‘መንፈስ ቅዱስ ሆይ ናልን! ጠላትን ከእኛ ወዲያ አርቅልን፤ ሰላምን ቶሎ ስጠን፤ መሪያችን ከሆንከው ከአንተ ጋር ክፉ ነገር ሁሉ እናስወግዳለን።’”