ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ፥ “ትዳራችሁን እና ልጆቻችሁን እንዲጠብቅላችሁ መንፈስ ቅዱስን ወደ ቤታችሁ ጋብዙት!”

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራችንስኮስ ዘወትር ረቡዕ እለት በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለሚሰበሰቡ ምዕመናን የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንደሚያደርጉ ይታወቃል። በዚህ መሰረት ቅዱስነታቸው በጥቅምት 13/2017 ዓ. ም ያደረጉት የጠቅላላ አስተምህሮ ከእዚህ ቀደም "መንፈስ ቅዱስ እና ሙሽራይቱ። መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ሕዝቦች ተስፋቸው ወደ ሆነው ወደ ኢየሱስ ይመራቸዋል" በሚል ዐብይ አርዕስት ጀምረው ከነበረው አስተምህሮ ቀጣይና "መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ስጦታ፥ መንፈስ ቅዱስ እና ምስጢረ ተክሊል" በሚል ንዑስ አርእስት ባደረጉት የክፍል 10 አስተምህሮ፥ “ትዳራችሁን እና ልጆቻችሁን እንዲጠብቅ መንፈስ ቅዱስን ጋብዙት!” ማለታቸው ተገልጿል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

በዕለቱ የተነበበው የእግዚአብሔር ቃል፥ "ወዳጆች ሆይ፤ ፍቅር ከእግዚአብሔር ስለሆነ እርስ በርሳችን እንዋደድ፤ የሚወድድ ሁሉ ከእግዚአብሔር የተወለደ ነው፤ እግዚአብሔርንም ያውቃል። የማይወድድ ግን እግዚአብሔርን አያውቅም፤ እግዚአብሔር ፍቅር ነውና" (1 ዮሐ 4፡7-8)።

ክቡራን እና ኩብራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በእለቱ ያደርጉትን የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ ሙሉ ይዘቱን እንደሚከተለው አሰናድተነዋል፥

"የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ! ባለፈው ጊዜ አስተምሮዋችን በጸሎተ ሃይማኖት ውስጥ ስለ መንፈስ ቅዱስ የተጠቀሰውን ተመልክተናል። የቤተ ክርስቲያኗ ነጸብራቅ የነበረ ሲሆን ነገር ግን በዚያ አጭር የእምነት መግለጫ ብቻ የቆመ አልነበረም። በምስራቅም ሆነ በምእራብም በታላላቅ አባቶች እና ምሁራን ስለ መንፈስ ቅዱስ ጥናቱ ቀጠለ። ዛሬ በተለይ በላቲን ትውፊት የዳበረውን የመንፈስ ቅዱስ ትምህርት ሁሉንም የክርስቲያን ሕይወት እና በተለይም ጋብቻን የሚመለከተው የምስጢረ ተክሊል ሥርዓተ እንዴት እንደሚያበራ ለማየት ያስችለን ዘንድ ጥቂት መገለጫዎችን ለመሰብሰብ እንወዳለን።

የዚህ አስተምህሮ ዋና ፈጣሪ ቅዱስ አውግስጢኖስ ነው። 'እግዚአብሔር ፍቅር ነው' (1ኛ ዮሐ 4፡8) ከሚለው ራእይ ይጀምራል። አሁን ፍቅር የሚወደውን ፣ የተወደደውን እና አንድ የሚያደርጋቸው እራሱን መውደዱ ያስባል። አብ በቅድስት በሥላሴ ውስጥ፣ እርሱ የሚወድ፣ የሁሉም ነገር ምንጭ እና መነሻ፥ ወልድ የተወደደ ነው። መንፈስ ቅዱስም አንድ የሚያደርጋቸው ፍቅር ነው። የክርስቲያኖች አምላክ በእዚህ የተነሣ 'ብቻ' አምላክ ነው። ነገር ግን ብቻውን አይደለም፤ የእርሱ የኅብረት እና የፍቅር አንድነት ነው። በዚህ መስመር አንዳንዶች መንፈስ ቅዱስን የቅድስት ሥላሴ 'ሦስተኛ አካል ነጠላ' ሳይሆን 'የመጀመሪያ አካል ብዙ' ብለው እንዲጠሩት ሐሳብ አቅርበዋል። በሌላ አነጋገር፣ እርሱ የአብ እና የወልድ መለኮታዊ እና በተለያዩ አካላት መካከል ያለው የአንድነት ማሰሪያ፣ የቤተ ክርስቲያን አንድነት መርህ፣ እሱም በእርግጥ ከበርካታ አካላት የተገኘ 'አንድ አካል' ነው።

እንዳልኩት፣ ዛሬ በተለይ መንፈስ ቅዱስ ስለ ቤተሰብ ምን እንደሚል ላሳስባችሁ እወዳለሁ። መንፈስ ቅዱስ ከጋብቻ ጋር ምን አገናኘው? በጣም ጥሩ! ይህንን መመልከት ምናልባትም አስፈላጊ ነው። እናም ለምን እንደሆነ ለማስረዳት እሞክራለሁ! ክርስቲያናዊ ጋብቻ ራስን የመስጠት ምስጢር ነው። አንዱ ለሌላው፣ ወንድ እና ሴት የመሰጠት ምስጢር ነው። ፈጣሪም 'እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ… ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው' (ዘፍ 1፡27) ሲል ይህን አስቦ ነበር። ስለዚህም ሰዋዊው ጥንዶች የቅድስት ስላሴ የሆነውን የፍቅር ኅብረት የመጀመሪያ እና የመጀመሪያ ደረጃ ግንዛቤ ናቸው።

የተጋቡ ጥንዶችም የመጀመሪያ ብዙ ቁጥር ማለትም 'እኛ' የሚለውን መፍጠር አለባቸው። እንደ 'እኔ' እና 'እናንተ' በመሆን እርስ በርሳችሁ ቁሙ። 'እኛ' እንደመሆናችሁ ልጆቻችሁን ጨምሮ በዓለም ፊት ቁሙ። እናት ለልጆቿ፡- 'አባትህና እኔ...' ስትል መስማት እንዴት ደስ ይላል! ማርያም እና ዮሴፍ ኢየሱስን በቤተ መቅደስ ባገኙት ጊዜ በአሥራ ሁለት ዓመቱ ማለት ነው 'እኔ እና አባትህ ስንፈልግህ ነበር' (ሉቃ. 2፡48) ብላ የነበረ ሲሆን እናም አንድ አባት 'እናትህ እና እኔ' አንድ ሆነን ብሎ ሲናገር መስማት እጅግ በጣም ደስ ይላል። ይህ የወላጆች አንድነት ምን ያህል ልጆች ያስፈልጋቸዋል፣ እና በሚጎድልበት ጊዜ ምን ያህል ይሠቃያሉ!

ነገር ግን ከዚህ ጥሪ ጋር ለመዛመድ፣ ጋብቻ የስጦታው የእርሱ ድጋፍ ያስፈልገዋል። በእርግጥም ዋና ሰጪው እርሱ እግዚአብሔር ነው። መንፈስ ቅዱስ በገባበት ቦታ፣ ራስን የመስጠት አቅም እንደገና ይወለዳል። አንዳንድ የላቲን ቤተ ክርስቲያን አባቶች በቅድስት ሥላሴ ውስጥ የአብና የወልድ የጸጋ ስጦታ መንፈስ ቅዱስም በመካከላቸው ለነገሠው ደስታ ምክንያት እንደሆነ አረጋግጠው ነበር። ይህን ሲናገሩም አልፈሩም። እንደ መሳም እና መተቃቀፍን የመሳሰሉ ለትዳር ሕይወት ተገቢውን ተጨባጭ ምልክቶችን ይጠቀሙ ነበር።

ማንም ሰው እንዲህ ያለው አንድነት ዛሬ ባለው ዓለም ውስጥ ከሁሉም ያነሰ ቀላል ሥራ እንደሆነ አይናገርም፣ ነገር ግን ፈጣሪ እንደፈቀዳቸው የነገሮች እውነት ይህ ነው። ስለዚህም በተፈጥሯቸው ጋብቻዎች ቅዱስ ናቸው። በእርግጠኝነት ከዓለት ይልቅ በአሸዋ ላይ መገንባት ቀላል እና ፈጣን ሊመስል ይችላል። ነገር ግን የኢየሱስ ምሳሌ ውጤቱ ምን እንደሆነ ይነግረናል (ማቴ. 7፡24-27)። በዚህ ሁኔታ ውስጥ እንግዲያውስ ምሳሌውን እንኳን አያስፈልገንም። ምክንያቱም በአሸዋ ላይ የተገነቡ ጋብቻዎች መዘዞች፣ በሚያሳዝን ሁኔታ ሁሉም ሊያዩት ስለሚችሉ ዋጋ የሚከፍሉት ልጆች ናቸው። ብዙ ባለትዳሮችን በተመለከተ፥ በቃና ዘገሊላ ማርያም ለኢየሱስ የተናገረችውን መድገም አለብን። 'የወይን ጠጅ እኮ የላቸውም' (ዮሐ 2፡3)። ሆኖም መንፈስ ቅዱስ ኢየሱስ በዚያ አጋጣሚ የሠራውን ተአምር በመንፈሳዊ ደረጃ ማድረጉን የቀጠለ ነው። ይኸውም ውሃውን ወደ ወይን ጠጅ የቀየረበት እና ወደ አዲስ ደስታ አብሮነት መለወጥ ማለት ነው። ይህ ቅዠት አይደለም። ባለትዳሮች እርሱን ለመጥራት ሲወስኑ መንፈስ ቅዱስ በብዙ ትዳሮች ውስጥ ያደረገው ነገር ነው።

ስለዚህ በትዳር ውስጥ የታጩ ጥንዶችን ለማዘጋጀት ከሚሰጠው የሕግ፣ የሥነ-ልቦናዊ እና ሥነ ምግባራዊ መረጃ ጋር ተያይዞ ይህ 'መንፈሳዊ' ዝግጅት በጥልቀት ቢጠና መጥፎ ነገር አይሆንም። አንድ የጣሊያን ምሳሌ 'በባልና ሚስት መካከል በፍጹም ጣትህን አታስገባ፣ ጣልቃ አትግባ' ይላል። በእውነቱ በባልና በሚስት መካከል የሚቀመጥ 'ጣት' አለ፣ 'የእግዚአብሔር ጣት'፣ መንፈስ ቅዱስ!"


 

23 October 2024, 12:11