ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ በቤተሰብ ላይ በተካሄደ ጠቅላላ ጉባኤ የተሳተፉ ባለ ትዳሮችን ሲያገኙ ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ በቤተሰብ ላይ በተካሄደ ጠቅላላ ጉባኤ የተሳተፉ ባለ ትዳሮችን ሲያገኙ  (Vatican Media)

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ፥ በቤተሰብ መካከል አለመግባባቶች ሲኖሩ መወያየት እንደሚገባ አሳሰቡ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በሲኖዶስ ጉባኤ መካከል ባስተላለፉት አጭር የቪዲዮ መልዕክት፥ በቤተሰብ ውስጥ ስላለው ሲኖዶሳዊነት አፅንዖት በመስጠት መወያየት በማይፈልግ ቤተሰብ ውስጥ ሕይወት እንደሌለ ገልጸዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ቅዱስነታቸው ከሲኖዶሱ የጉባኤ አዳራሽ ዓርብ ጥቅምት 15/2017 ዓ. ም. ባስተላለፉት የሃያ ስምንት ሴከንድ የቪዲዮ መልዕክታቸው፥ በርዕሠ ሊቃነ ጵጵስና ሹመታቸው ውስጥ ውይይት ትልቅ ሥፍራ ያለው እሴት መሆኑን በማረጋገጥ ውይይት ለጤናማ የቤተሰብ ሕይወት አስፈላጊ እንደሆነ አስረድተዋል።

በአለመግባባቶች መካከል ውይይት ሊኖር ይገባል
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በመቀጠልም፥ በቤተሰብ ውስጥ ስላለው ሲኖዶሳዊነት እንዲናገሩ መጠየቃቸውን ገልጸው፥ “አንዳንድ ጊዜ በቤተሰብ ውስጥ ግጭቶች ሲከሰቱ ዘወትር ለውይይት መቅረብ እንደሚገባል ተናግረዋል።

የቤት ውስጥ ግንኙነቶችን በውይይት ካላዳበሩት ውጤቱ ውድቀት ሊሆን እንደሚችል፥ እርስ በርስ የማይወያይ ቤተሰብ ሕይወት ሊኖረው እንደማይችል፣ በመደማመጥ እና በውይይት ላይ የተመሠረተ የሲኖዶስ ዘይቤ ፍፁም የቤተሰባዊ የአኗኗር ዘይቤ ነው” ሲሉ አስረድተዋል።

 

26 October 2024, 15:48