የሩስያን ወታደራዊ ጥቃት በመሸሽ ሰዎች በኪየቭ በሚገኘው በሜትሮ ጣቢያ ውስጥ ሲጠለሉ የምያሳይ ምስል የሩስያን ወታደራዊ ጥቃት በመሸሽ ሰዎች በኪየቭ በሚገኘው በሜትሮ ጣቢያ ውስጥ ሲጠለሉ የምያሳይ ምስል 

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በጦርነት ለተመቱ አገሮች ሰላም እንዲሰፍን ጸለዩ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በህዳር 04/2017 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተገኙ ምዕመናን የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ካደረጉ በኋላ በማጠቃለያ ላይ በጦርነት የተሠቃዩ አገሮችን በተለይም ዩክሬን ፣ ቅድስት ሀገር እና ምያንማር አስታውሰዋል ።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

በጦርነት የተጎዱ አገሮችን በጸሎት ማስታወስ እንዳንረሳ በማለት የተናገሩት ቅዱስነታቸው "ወንድሞች እና እህቶች" በጦርነት ለሚሰቃዩ የማሕበረሰብ ክፍሎች መጸለይ በፍጹም እንዳትታክቱ ማለታቸው ተገልጿል፣ በተለይም "ሰማዕት የሆነችው ዩክሬይንን! ዩክሬንን አንርሳ" ሲሉ ተማጽነዋል።

በተመሳሳይ “ፍልስጥኤምን፣ እስራኤልን፣ ምያንማርን እና በጦርነት ላይ ያሉ ብዙ አገሮችን እንዳንረሳ” በማለት የተናገሩት ቅዱስነታቸው በተለየ ሁኔታ በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ በጥይት ወደ ተገደሉት 153 ንጹሐን ፍልስጤማውያን ፊታቸውን አዙረዋል። እነሱን እያሰብን “ስለሰላም እንጸልይ፤ በጣም ሰላም እንፈልጋለን፣ በጣም ብዙ!” ሲሉ ንግግራቸውን አጠቃለዋል።

 

13 November 2024, 16:10