ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ እያንዳንዱ የርኅራኄ ተግባር የተስፋ ምልክት ነው ማለታቸው ተገለጸ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለዓለም የድሆች ቀን በተዘጋጀው መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባደረጉት ስብከት፣ በድሆች ስቃይ ውስጥ የእግዚአብሔርን መገኘት እንድንገነዘብ እና ኢፍትሃዊነትን በመጋፈጥ በተስፋ እና በርኅራኄ እንድንቀሳቀስ ጥሪ አቅርበዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በእለቱ በተነበበው የወንጌል ንባብ ላይ የቀረቡትን የምጽዓት ምስሎች በማንፀባረቅ ህዳር 08/2017 የተከበረውን የዓለም የድሆች ቀን በማስመልከት በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ በተካሄደው መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ የሚሰማቸውን ጥልቅ የጭንቀት ስሜት በመገንዘብ ስብከት አድርገዋል። ቃሉ እንዲህ ይላል፡- “ፀሐይ ትጨልማለች፣ ጨረቃም ብርሃኗን አትሰጥም፣ ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ።” ይህ ለርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የዓለማችንን ስቃይ ማለትም ረሃብን፣ ጦርነትን፣ እኩልነትን እና የሚከተለው ግድየለሽነት ያስታውሰናል ብለዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ- ቫቲካን

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ማህበራዊ ሚዲያ ፍርሃትን እና ስጋትን በሚያሰፋበት ዓለም ለተስፋ መቁረጥ መሸነፍ ቀላል እንደሆነ አስጠንቅቀዋል። ነገር ግን፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በመቀጠል፣ እግዚአብሔር የሚቀርበው በጨለማ ውስጥ ነው፣ “ልክ ሁሉም ነገር የሚፈርስ በሚመስል ጊዜ፣ እግዚአብሔር ይመጣል፣ እግዚአብሔር እኛን ለማዳን በአንድነት ይሰበስበናል” ኢየሱስ በሞቱ እና በትንሳኤው በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ በጣም ጨለማ የሆነውን ጊዜ ወደ ድነት መባቻ ቀይሮታል ሲሉ ጳጳሱ አስረድተዋል።

በተስፋ መቁረጥ ውስጥ የተስፋ ምልክቶች

ከዚያም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በጸደይ ወቅት የበለስ ዛፍ የምያከናውነውን ምስል ጠቅሰዋል። ይህንንም በማሰብ ምእመናን እጅግ አስከፊ በሆኑ እውነታዎች ውስጥም ቢሆን የተስፋ ምልክቶችን እንዲፈልጉ አሳስቧል። ጌታ በድሆች እና በስቃይ መካከል መገኘቱ ቀጠለ፣ “ግፍ፣ ስቃይ እና ድህነት ብቻ ያለ በሚመስልበት፣ ጌታ እኛን ነፃ ለማውጣት ይቀርባል” በማለት ተናግረዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ተግባር ይህንን ተስፋ እንዲታይ ማድረግ ነው ብለዋል። በፍትህ፣ በአብሮነት እና በበጎ አድራጎት ተግባራት እያንዳንዳችን “የጌታ መገኘት ምልክቶች” መሆን እንችላለን፣ ይህም ለሚሰቃዩ ሁሉ ቅርብ መሆኑን እናሳያለን ብለዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ስብከታቸውን በማጠናቀቅ ምእመናንን በማሳሰብ ለውጥ የሚጀምረው በትንንሽና ዕለታዊ ተግባራት ነው። እንዴት እንደምንኖር፣ አካባቢያችንን እንደምንንከባከብ፣ ወይም ሀብታችንን እንዴት እንደምንጋራ፣ እያንዳንዱ የርህራሄ ተግባር የተስፋ ምልክት ሊሆን ይችላል። "እና ይህን ለቤተክርስቲያን እናገራለሁ፣ ለመንግሥት እላለሁ፣ ለአለም አቀፍ ድርጅቶች እላለሁ፣ ለእያንዳንዱ እና ለሁሉም እላለሁ: እባካችሁ ድሆችን አንርሳ" በማለት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ስብከታቸውን ደምድመዋል።

18 November 2024, 10:36