በኢንዶኔዢያ የደረሰው የእሳተ ጎመራ አደጋ በኢንዶኔዢያ የደረሰው የእሳተ ጎመራ አደጋ   (AFP or licensors)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በኢንዶኔዥያ እሳተ ገሞራ የተጎዱትን በማስታወስ ለዓለም ሰላም ጸለዩ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እሁድ ህዳር 1/2017 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ ተንተርሰው አስተንትኖ ካደረጉ በኋላ ለዓለም ባሰታለለፉት መልእክት በኢንዶኔዥያ በተከሰተው የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ለተጎጂዎች እና በስፔን ቫሌንሺያ በጎርፍ ለተጎዱ ሰዎች ጸሎታቸውን እና ሀዘናቸውን አቅርበዋል። በሞዛምቢክ ስላለው አለመረጋጋት እና በዩክሬን፣ በፍልስጤም፣ በእስራኤል፣ በምያንማር እና በሱዳን ያለው ደም መፋሰስ እንዲቆም ውይይት እንዲደረግ ጠይቋል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እሁድ እለት ባደረጉት የመላከ እግዚአብሔር ጸሎት ማጠቃለያ ላይ ባደረጉት ንግግር የኢንዶኔዢያ ፍሎሬስ ደሴት ከሳምንት በፊት በጀመረው የእሳተ ጎመራ ፍንዳታ ለተጎዱ ሰዎች ያላቸውን ቅርበት ገልጸው የአካባቢው ባለስልጣናት የአደጋ ጊዜ እርዳታዎች ተደራሽ እንዲሆኑ ቅዱስነታቸው ጥሪ አቅርበዋል።

በኢንዶኔዥያ እሳተ ገሞራ ለተጎዱ ሰዎች ጸሎት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ለተጎጂዎች፣ ለተፈናቀሉት እና ለቤተሰቦቻቸው ጸሎታቸውን አቅርበዋል። ነዋሪዎችን ከአካባቢው ለማራቅ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ተፈናቃዮችን ወደ ሌላ ሥፍራ ለማሻገር ሥራ በጀመሩበት ወቅት 10 ሰዎች መሞታቸው የተረጋገጠ ሲሆን በደርዘን የሚቆጠሩ ቆስለዋል። ቀደም ሲል በጥር ወር የሌዎቶቢ ላኪ-ላኪ እሳተ ገሞራ ፍንዳታ 6,500 የሚያህሉ ነዋሪዎችን ለቀው እንዲወጡ አስገድዷቸው ነበር።

ቫለንሺያን ስፔን

በስፔን ቫለንሲያ እና አከባቢዋ በቅርብ ሳምንታት በከባድ የጎርፍ መጥለቅለቅ መመታቷ ይታወቃል፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ሁሉም ሰው ለህዝቡ እንዲፀልይ እና የነፍስ አድን እና የእርዳታ ጥረቶችን ለመርዳት በሆነ መንገድ ለማገዝ የሚደርገውን ጥረት ለመደገፍ ሕዝቡ እጁን እንዲዘረጋ ጠይቀዋል።  በጥቅምት ወር መገባደጃ ላይ የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ ከፍተኛ የጎርፍ አደጋ ደቡባዊ እና ምስራቃዊ ስፔንን ነካ። ከ200 የሚበልጡ ሰዎች ህይወታቸውን ያጡ ሲሆን የአደጋ ጊዜ አገልግሎቶች በመቶዎች የሚቆጠሩ አሁንም የጠፉ ሰዎችን ፍለጋ ቀጥለዋል። የተፈጥሮ አደጋው በስፔን ህያው ትውስታ ውስጥ እጅግ የከፋ ተብሎ ተጠርቷል።

በሞዛምቢክ ውስጥ ውይይት እንዲደረግ ጥሪ ቀርቧል

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳቱም ሀሳባቸውን ወደ ደቡብ ምስራቅ አፍሪካዊቷ አገር ሞዛምቢክ አዙረው ለሳምንታት የዘለቀ ህዝባዊ አመጽ የቀጠለው ባለፈው ወር የተደረገውን ምርጫ ተከትሎ አለም አቀፍ የመብት ተሟጋች ድርጅቶች በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎች መሞታቸውን ገልጸዋል።

ከሞዛምቢክ እየመጣ ስላለው አሳሳቢ ዜና ያሳሰባቸው ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ሁሉም ሰው በውይይት እና በድርድር እንዲሳተፍ አሳስበዋል። አሁን ያለው ሁኔታ በዴሞክራሲ፣ በፍትህና በሰላም ጎዳና ላይ እምነት እንዳያሳጣ ሁሉም ሰው እንዲጸልይ አሳስበዋል።

ለዓለማችን ሰላም ጸሎቶች

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በተለይም ሆስፒታሎች እና ሌሎች የሲቪል ሕንፃዎች እየተመታባቸው ያሉትን በዩክሬን የሚገኙ ዜጎች እየተሰቃዩ መሆናቸውን በማስታወስ ለዓለም ሰላም ጸሎት እንዲደረግ አሁንም ጥሪያቸውን አቅርበዋል።  ለፍልስጤም፣ ለእስራኤል፣ ለሊባኖስ፣ ለሚያንማር፣ ለሱዳን እና ለመላው አለም ሰላም የፀሎት ጥሪያቸውን አድሷል።

11 November 2024, 11:08