ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ 6ኛ የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ሆነው የሚያሳይ ምስል ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ 6ኛ የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ሆነው የሚያሳይ ምስል  

ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ በሶሪያ ሰላም እንዲሰፍን የቅድስት ድንግል ማርያምን አማላጅነት ተማጸኑ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በታኅሣሥ 02/2017 ዓ.ም በቫቲክን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ካደረጉ በኋላ ባስተላለፉት መልእክት በሶሪያ ሰላም እንዲሰፍን የተማጸኑ ሲሆን "በታሪኳ በጣም ስስ በሆነው በዚህ ቅጽበት በሶሪያ እየሆነ ያለውን ነገር በየቀኑ እየተከታተልኩ ነው። ያለ ተጨማሪ ግጭቶችና መከፋፈል በሃላፊነት የአገሪቱን መረጋጋትና አንድነት የሚያጎለብት ፖለቲካዊ መፍትሄ ይገኝ ዘንድ ተስፋ አደርጋለሁ" ማለታቸው ተገልጿል።

የሶርያ ሕዝብ በወደደው አገሩ በሰላምና በደኅና እንዲኖር፣ የተለያዩ ሃይማኖቶችም በብዙዎች እየታፈኑ ስለሆነ በወዳጅነትና በመከባበር አብረው እንዲሄዱ በድንግል ማርያም አማላጅነት እጸልያለሁ ያሉት ቅዱስነታቸ ለብዙ ዓመታት የዘለቀው ጦርነት እንዲያበቃ ሁላችንም ልንጸልይ ይገባል ሲሉ ቅዱስነታቸው ተማጽነዋል።

12 December 2024, 11:05