የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኤማኑኤል ማክሮን ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ጋር በኮርሲካ በተገናኙበት ወቅት የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኤማኑኤል ማክሮን ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ጋር በኮርሲካ በተገናኙበት ወቅት  

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ከፕሬዝዳንት ማክሮን ጋር ባደረጉት ስብሰባ የኮርሲካን ጉብኝት አጠናቋል!

በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እና በፈረንሳዩ ፕሬዝደንት መካከል የተደረገ የግል ስብሰባ የቅዱስ አባታችን የኮርሲካ የአንድ ቀን ሐዋርያዊ ጉብኝት ተጠናቋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ከኮርሲካ ከመነሳታቸው ጥቂት ቀደም ብሎ ለርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ "እዚህ የእኛ ግዛት መምጣት ስለቻሉ አመሰግናለው። ይህን ውይይት ለማድረግ እዚህ መምጣቶ ስብዕናዎን ያንፀባርቃል። ለእኔ ለሰጡኝ ጊዜ በጣም አመሰግናለሁ" ሲሉ መናገራቸው ተገልጿል።

በመቀጠልም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እና ፕሬዝዳንቱ በናፖሊዮን ቦናፓርት አየር ማረፊያ ወደምትገኘው ትንሽ ክፍል አብረው ገቡ፣ በአገሩ የሰዓት አቆጣጠር ከቀኑ 6 ሰዓት በፊት ነበር። በየራሳቸው ልዑካን ታጅበው በቫቲካን፣ በፈረንሳይ እና በአውሮፓ ባንዲራዎች ያጌጠ ክፍል ውስጥ ቦታቸውን ያዙ፣ ሥፍራው በሁለት ወንበሮች የታጀበ ሲሆን አንደኛው የጳጳሱ አርማ ያለበት ነው።

እንደቀደሙት ታዳሚዎች፣ እ.አ.አ በ2023 ዓ.ም በቫቲካን ወይም በማርሴይ እና በጂ7 ጉባኤ፣ ማክሮን ለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ያላቸውን ፍቅር ገልጿል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት የጵጵስና ማዕረግ ያላቸው ሜዳሊያዎችን እና ከመንበራቸው የወጡ ሰነዶችን ለማክሮን በስጦታ መልክ አቅርበዋል።

 

15 December 2024, 13:39