ቫቲካን በሮም ከተማ ለሚገኙ ከ300 በላይ ድሆች የኮቪድ 19 ክትባት ለመስጠት ቃል ገባች
ቫቲካን ቅዳሜ ሚያዝያ 30/2013 ዓ.ም ኮቪድ -19 ክትባቶችን የመኖሪያ ቤት ለሌላቸው እና ለአደጋ ተጋላጭ ለሆኑ ሰዎች መከተብ መጀመሯ ተገለጸ። በቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ ስድስተኛ አዳራሽ ውስጥ የሚካሄደውን ይህን የኮቪድ 19 ክትባት የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ጽ / ቤት እያስተባበረ ይገኛል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በወረርሽኙ ሳቢያ በከባድ ችግር ውስጥ ያሉ አገሮችን ለመርዳት ከወዲሁ ያስቻለው ታግዶ የነበረው የክትባት ስርጭት በመለቀቁ የተነሳ በችግር ውስጥ የሚገኙ ብዙ አገራትን ለመርዳት መቻሉ ተገልጿል።የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን
ቫቲካን ከእዚህ ቀደም 1400 በላይ የሚሆኑ ድሆችን እና ለበሽታ ተግላጭ የሆኑ ሰዎች የኮቪድ 19 ክትባት በነጻ መስጠቷ የሚታወስ ሲሆን ይህም ክትባት በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የበጎ አድራጎት ጽህፈት ቤት ድጋፍ እና ተነሳሽነት የተካሄደ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ክትባቱ በተለይም ደግሞ የመኖሪያ ቤት ለሌላቸው እና በጎዳና ላይ ለሚገኙ ሰዎች የበኩሉን አስተዋጾ ማበርከቱ ተገልጿል። በቫቲካን በቅዱስ ጴጥሮስ ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኘው “የምሕረት እናት” ክሊኒክ ለሁለት ሳምንት ያህል የኮቪድ 19 ክትባት መከተብ ከሚፈልጉ ሰዎች ማመልከቻዎችን እንደ ተቀበለ የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የበጎ አድራጎት ጽሕፈት ቤት ዋና ኃላፊ ካርዲናል ኮንራድ ክራውስስኪ ለቫቲካን ሬዲዮ ገልጸዋል። ቅዳሜ ሚያዝያ 30/2013 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው የጳውሎስ ስድስተኛ አዳራሽ ውስጥ 300 ያህል ሰዎች ክትባቱን እንደ ሚቀበሉ ይጠበቃል። እነዚህ ሰዎች በተለያዩ ምክንያቶች አብዛኛውን ጊዜ አካባቢውን በሚያገለግሉ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች የማይረዱ ሰዎች ናቸው። ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ በተመሳሳይ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ወደ 1400 ድሃ ሰዎች በቫቲካን ክትባት አግኝተዋል።