ዓለም አቀፍ ካቶሊካዊ ምእመናን ማኅበራት ለጠቃሚ ለውጥ እንዲቆሙ የሚያበረታታ አዋጅ መጽደቁ ተነገረ
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን
በቅድስት መንበር የምእመናንና የቤተሰብ ሕይወት መምሪያ ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት ባወጣው ጠቅላላ ድንጋጌው ከዓለም አቀፍ ካቶሊካዊ ምዕመናን ማኅበራት የሚመረጡ የመንግሥት እና ዓለም አቀፍ መንግሥታዊ ተቋማት ተወካዮች የአገልግሎት ዘመን ከ10 ተከታታይ ዓመታት እንዳይበልጥ የሚጠይቅ መሆኑ ታውቋል። ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ ያጸደቁ አዋጅ ተግባራዊ የሚሆነው በሦስት ወራት ጊዜ ውስጥ ተግባራዊ የሚሆን እና በቅድስት መንበር የምእመናንና የቤተሰብ ሕይወት መምሪያ ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት በኩል የተቋቋሙ የምእመናን ማህበራትን እና ሌሎች አካላትን የሚያገድድ አዋጅ መሆኑ ታውቋል።
የአዋጁ ዓላማ በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ውስጥ ተሰማርተው የሚሠሩ ካቶሊካዊ ዓለም አቀፍ ማኅበራት አባላት ከቤተ ክርስቲያን ጋር የጠበቀ ኅብረትን በመፍጠር “ጤናማ ለውጥ” እንዲስፋፋ የሚያደርጉ ትክክለኛ አገልግሎቶችን እንዲያቀርቡ ለማድረግ መሆኑ ታውቋል።
ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ ከእርሳቸው በፊት መላዋ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያንን የመሩት ርዕሳነ ሊቃነ ጳጳሳት የተጓዙበትን መንገድ በመከተል፣ የቤተክርስቲያኗን የረጅም ዓመታት ልምድን እና የምዕመኗን የወንጌል ልኡክነት ጥሪ እንዲታከልበት በማለት ሃሳባቸውን የገለጹበት አዋጅ መሆኑን የምእመናንና የቤተሰብ ሕይወት መምሪያ ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት አስታውቋል (ከወንጌል የሚገኝ ደስታ ቁ. 29-30)። አዋጁ ለሰው ልጅ የግል ነጻነት ቅድሚያን በመስጠት፣ የራስ-አመላካችነትን፣ ሁለገብነትን እና ጠቅላላነትን መሰርት በማድረግ የቅዱስ ሲኖዶስ አንደነትን የሚያመለክት መሆኑ ታውቋል።
በቅድስት መንበር የምእመናንና የቤተሰብ ሕይወት መምሪያ ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት በማከልም የተዘጋጀው ሰነድ፣ አልፎ አልፎ በመንግሥት በኩል የሚቀመጡ ገደቦች መኖራቸውን ቢገነዘብም፣ ለማስተዳደር የሚመረጡ አካላት፣ በግል ፍላጎታቸው እና ምርጫቸው የሚውስዱት ውሳኔዎች በሕዝቡ ላይ የሚያነሳውን ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ረገጣን እና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን እና ሌሎች ሕገ ወጥ ተግባራትን ለማስቀረት ያለመ መሆኑን አስታውቋል። የተሳሳተ የምንግሥት አስተዳደር አላስፈላጊ ግጭቶችን እና አመጾችን በመቀስቀስ ማኅበራዊ ሕይወትን ወደ ችግር ውስጥ የሚመራ እና የወንጌል ተልዕኮን ሂደት የሚያዳክም መሆኑን ሰነዱ ገልጿል።