ታኦኢስቶች እና ክርስቲያኖች በሆንግ ኮንግ የውይይት መድረክ ማዘጋጀታቸው ተገለጸ!  ታኦኢስቶች እና ክርስቲያኖች በሆንግ ኮንግ የውይይት መድረክ ማዘጋጀታቸው ተገለጸ!  

ታኦኢስቶች እና ክርስቲያኖች በሆንግ ኮንግ የውይይት መድረክ ማዘጋጀታቸው ተገለጸ!

በቅድስት መንበር ሥር የሚተዳደረው እና በተለያዩ የሃይማኖት ተቋማት መካከል ውይይት እንዲደረግ የሚሰራው ጽኃፈት ቤት ከመጋቢት 2-4/2016 ዓ.ም በሆንግ ኮንግ የሚካሄደውን ሶስተኛውን የክርስቲያን-ታኦኢስት ውይይት ማሰናዳቱ ተገልጿል።

የእዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ክርስቲያኖች እና ታኦኢስቶች በሁለቱ ሃይማኖታዊ ወጎች መካከል የሚደረገውን ውይይት ለመቀጠል በማስበ በሚቀጥለው ሳምንት በሆንግ ኮንግ ሊገናኙ ነው።

በቅድስት መንበር ሥር የሚተዳደረው እና በተለያዩ የሃይማኖት ተቋማት መካከል ውይይት እንዲደረግ የሚሰራው ጽኃፈት ቤት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ መሠረት ዝግጅቱ በዩኤን ዩን ኢንስቲትዩት ሎ ዋይ ቱዋን ዋን ሆንግ ኮንግ ከመጋቢት 2 እስከ 4/2016 ይካሄዳል ሲል ገልጿል።  

ሦስተኛው የክርስቲያን-ታኦኢስት ውይይት ከሆንግ ኮንግ ሀገረ ስብከት እና ከሆንግ ኮንግ ታኦኢስት ማኅበር ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ነው። ለሶስት ቀናት የሚቆየው ዝግጅት “በሃይማኖቶች መካከል ስምምነት ያለው ማህበረሰብን ማፍራት” በሚል መሪ ሃሳብ ላይ ያተኩራል።

ተሳታፊዎቹ ከሆንግ ኮንግ፣ ከቻይና ህዝባዊ ሪፐብሊክ፣ ፈረንሳይ፣ ጣሊያን፣ ታይዋን፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ማሌዥያ፣ ፊሊፒንስ፣ ቬትናም እና ሲንጋፖር ከአካባቢው ሲቪል ባለስልጣናት የተውጣጡ የሁለቱ ሃይማኖታዊ ወጎች ምሁራን እና ተከታዮችን ያካትታሉ።

ጋዜጣዊ መግለጫው እንዲህ ይላል:- “የሚስማማ ማኅበረሰብ ለመገንባት የበኩሎን አስተዋጽኦ ለማድረግ በሚፈልጉበት ጊዜ ተሳታፊዎች በሚከተሉት መሪ ሃሳቦች ላይ ያሰላስላሉ። ፣ 'ታኦ/ መንገድ እና ዴ/ በጎነት በውይይት እና ልምምድ'፣ 'ቅድስና በታኦይዝምና ክርስትና' እና 'የሃይማኖታዊ አስተሳሰቦችን እና እሴቶችን በአለም አቀፍ ደረጃ ማሰራጨት” በሚል መሪ ሐሳብ እንደሚካሄድ ተገልጿል።

ውይይቱ ታኦስቶችን እና ክርስቲያኖችን የጋራ መግባባታቸውን እንዲያጎለብቱ እድል ለመስጠት ይጥራል፣ይህም “አለመስማማት መከራ እና ስቃይ እንዴት እንደሚፈጥር” በመመርመር እና “የተበታተነውን አለምን ለመፈወስ” በጋራ መሥራት ይኖርብናል ሲል መግለጫው አክሎ ገልጿል።

 

11 March 2024, 11:56