ካርዲናል ፓሮሊን እና ጳጳስ ጁሴፔ ሼን ቢን ካርዲናል ፓሮሊን እና ጳጳስ ጁሴፔ ሼን ቢን  

ካርዲናል ፓሮሊን ለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሱ መታዘዝ ለሀገር ያለንን ፍቅር ያድሳል ማለታቸው ተገለጸ!

የቫቲካን ዋና ጸኃፊ የሆኑት ብፁዕ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን፣ የመጀመሪያው የቻይና ጉባኤ የተካሄደበት 100ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ላይ በተካሄደው ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ ንግግር ሲያደርጉ፣ “ለሌሎች የተልእኮ አገሮች ምሳሌ ነበር” ብለዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

“ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ዜግነታቸው ምንም ይሁን ምን በዓለም ላይ ላሉ ሁሉም ካቶሊኮች መንፈሳዊ መሪ ናቸው። ነገር ግን ይህ ለጳጳሱ መታዘዝ እያንዳንዱ ሰው ለሀገሩ ሊኖረው የሚገባውን ፍቅር አይጎዳውም፣ ይልቁንም ያጠራዋል እና ያነቃቃል” ያሉት ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን ከመቶ ዓመታት በፊት በቻይና የመጀመሪያው ሐዋርያዊ ልዑካን ሊቀ ጳጳስ ሴልሶ ኮስታንቲኒ የተናገሩት እነዚህ ቃላት ዛሬ በጣም ጠቃሚ ናቸው ብለዋል።

ሟቹ ሊቀ ጳጳስ “እንዲህ ያለው ሕብረት ከውጫዊ የፖለቲካ ፍላጎቶች ተጠብቆ በአካባቢው ባህልና ማህበረሰብ ውስጥ ጸንቶ ላለው እምነት ከሁሉ የተሻለ ዋስትና ነው” ሲሉ አብራርተዋል።

ሊቀ ጳጳስ ኮስታንቲኒ ችግሮች፣ መዘግየቶች እና ተቃውሞዎች ቢኖሩም የክርስቶስ ወንጌል በቻይና ምድር ስር እንዲሰድ እና ከአካባቢው ማህበረሰብ እና ባህል ጋር እንዲስማማ ለማድረግ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ሠርተው ነበር ያሉት ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን ሊቀ ጳጳስ ኮስታንቲኒም ማክሰኞ ግንቦት 13/2016 ዓ.ም የመቶኛ ዓመቱ የተከበረውን በቻይና የመጀመሪያው እና እስካሁን ብቸኛው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ጉባኤ በመጀመሪያ ደረጃ ያዘጋጁ እና ያስተዋወቁ እርሳቸው ነበሩ ብለዋል።  በዓለ ሢመቱ የተከበረው በጳጳሳዊው የሁርባኒያና  ዩኒቨርሲቲ ባዘጋጀው ጠቃሚ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ነው። ከፊደስ የዜና ወኪል እና ከቻይና የሐዋርያዊ አስተዳደር ኮሚሽን ጋር በመተባበር ነበር ጉባኤው የተዘጋጀው።

በጠዋቱ ክፍለ ጊዜ ቁልፍ ንግግር ካደረጉት መካከል የቫቲካን ዋና ጸኃፊ የሆኑት ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን ይገኙበታል።

ጥሩ አማኞች፣ ጥሩ ዜጎች

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ባስተላለፉት የቪዲዮ መልእክት ቀደም ብሎ የጉባኤው ዋና አዘጋጅ አቶ ቪንቼንሶ ቡኦኖሞ በመግቢያው ላይ እንደገለፁት ይህ ኮንፈረንስ “ትምህርታዊ እናጂ የበዓል አከባበር አይደለም” ማለታቸውን የጠቀሱ ሲሆን ዝግጅቱ “ታሪካዊ ተሐድሶ” ሳይሆን የጉባኤው ክስተት ራሱ እንዴት “የክርስቲያን መልእክት የሚያመጣው መሠረትና ዋቢ ሆኖ የሚያገለግል ሲሆን ይህም ግሩም አማኞች መኖራቸውን ያረጋግጣል። ምርጥ ዜጎች አንዳሉም ያሳየል" ብለዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከወራት በፊት በሞንጎሊያ ባደረጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት የማጠቃለያ መስውዋዕተ ቅዳሴ ላይ ለቻይና ሕዝብ ባቀረቡት ሰላምታ ላይ አጽንኦት ሰጥተውት የነበረው ጽንሰ ሐሳብ ነበር፣ ካርዲናል ፓሮሊንም በንግግራቸው ደግመው ተናግረዋል።

ሊቀ ጳጳስ ኮስታንቲኒ ከመቶ ዓመት በፊት ስለዚህ ጉዳይ የማያሻማ ቃላትን እንዴት እንደጻፉ አስታውሰዋል። “ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የቻይና ካቶሊኮች አገራቸውን እንዲወዱ እና በዜጎች መካከል ምርጥ እንዲሆኑ ይፈልጋሉ። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ሁሉንም ብሔራትን ይወዳሉ፣ እንደ እግዚአብሔር ተወካይ ሆነም በምድር ያገለግላሉ፣  የእናንተን የተከበረ እና ታላቅ ህዝብ ቻይናን ይወዳሉ እና ከሁሉም ጋር በእኩልነት ይመለከቷችኋል” ማለታቸው ተገልጿል።

የዛሬ የቻይና ጉባኤ እሴት

ታሪክን መለስ ብለን ስንመለከት፣ ካርዲናል ፓሮሊን ምንም እንኳን የሻንጋይ ጉባኤ “ልዩ ምክር ቤት” ቢሆንም፣ “ሰፋ ያለ የቤተ ክርስቲያን ትርጉም” ነበረው ያሉ ሲሆን የቻይናው ጉባኤ “በቀጣዮቹ ዓመታት የራሳቸውን ብሔራዊ ሲኖዶስ ለማክበር ለሚዘጋጁ ሌሎች በርካታ የሚሲዮን አገሮች ምሳሌ” ነበር ብለዋል።

እንደ ካርዲናል ፓሮሊን ገለጻ፣ የተፈጸመውን ነገር ማስታወስ ለአሁኑ የቤተ ክርስቲያን ጊዜም ቢሆን “ትልቅ ዋጋ አለው” ያሉት በርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በሲኖዶሳዊነት ላይ በማሰላሰል የእግዚአብሔርን ሕዝብ “በቤተክርስቲያን ሕይወት ውስጥ ተጠያቂ እና ዋና ተዋናዮች እንዲሆኑ” በመጥራት ላይ ይገኛሉ ብለዋል። ለመጀመሪያ ጊዜ በቻይና  እ.አ.አ ከግንቦት 15 እስከ ሰኔ 12/1924 ዓ.ም በሻንጋይ የተካሄደው ጉባኤ የነበራቸው ልምድም ይኸው ነበር። ሊቀ ጳጳስ ኮስታንቲኒ “ካቴድራል የሚገነቡ ትክክለኛ ሠራተኞችን እንመስላለን” ብለዋል። "ዲዛይኑ የሚሰጠው በስነ ህንፃ ባለሙያ መሐንዲስ ነው፣ ነገር ግን እያንዳንዱ የራሱን ጡብ ወደ ታላቁ ግንባታ ያመጣል። ለእኛ የስነ-ሕንጻው ባለሙያ  ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ናቸው። ሠራተኞቹ ያልፋሉ፣ ካቴድራሉ ግን ይቀራል” ሲሉ ተናግረዋል።

በዚህ ዐውደ-ጽሑፍ ሊቀ ጳጳስ ኮስታንቲኒ የሚሲዮናዊ እና ዲፕሎማሲያዊ “ስልት” በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 15ኛ ማክስሚም ኢሉድ በተሰኘው ሰነድ አነሳሽነት አውጥተዋል፣ ይህም በቻይና ውስጥ የቤተክርስቲያኗ አጠቃላይ ሲኖዶስ እንዲያካሂድ ወደ “ማመን” ወስዶታል ብለዋል።

ሆኖም በመጀመሪያ፣ በበጎ አድራጎት እና በትጋት፣ “ወንጌልን ወደ ቻይና ያመጡትን” “የብዙ የውጭ አገር ሚስዮናውያንን ጥቅም” ሲገነዘቡ ሊቀ ጳጳስ ኮስታንቲኒ የካቶሊክ እምነትን ከቻይና ሕይወት ጋር በተሻለ ሁኔታ ለማዋሃድ ጥረት ማድረግ እንደሚያስፈልግ ተረድተዋል።

"ኮስታንቲኒ ከ'የውጭ ተልእኮ' ጽንሰ-ሀሳብ ወደ 'ሚስዮናዊት ቤተክርስትያን' የመሸጋገርን አጣዳፊነት አይቷል" ሲሉ ካርዲናል ፓሮሊን አጽንዖት ሰጥተው ተናግረዋል።

ስለዚህም የሃይማኖት አባቶችን አገር በቀል ሥራ ማራመድ አስፈለገ።

በዚህ ዓላማ እ.አ.አ “በ1926 የመጀመሪያዎቹን ስድስት ቻይናውያን ጳጳሳት መሾምን ደግፏል፣ እና በዚሁ ዓላማ በሚቀጥለው ዓመት የጌታ ደቀ መዛሙርት ጉባኤን አቋቋሙ።

በተጨማሪም “የካቶሊክ እምነት መፈልሰፍ የበለጠ እውን ሊሆን በሚችልበት” የቻይንኛ ጥበባዊ እና የሕንፃ ቅርጾችን በቅንነት አስተዋወቀ።

ምንም ዓይነት የትችት እጥረት እና በእርሳቸው ላይ እውነተኛ የሚዲያ ዘመቻ እንዳልነበረ ካርዲናል ፓሮሊን አስታውሰዋል። ነገር ግን “ሁልጊዜ ለትችት ምላሽ የሚሰጠው አርቆ በማሰብ ነው” ብለዋል።

የስምምነቱ እድሳት

የሊቀ ጳጳስ ኮስታንቲኒ ቅርስ ወደ ጊዜያችን ይደርሳል፣ እሱም እ.አ.አ ከ 2018 ጀምሮ በቅድስት መንበር እና በቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክ መካከል በኤጲስ ቆጶሳት ሹመት ጊዜያዊ ስምምነት መካከል ያለውን የእርስ በርስ ግንኙነት በማጠናከር ምልክት የተደረገበት ነው።

ካርዲናል ፓሮሊን በጉባዔው ላይ እንዳሉት "ሁላችንም አንዳንድ ነጥቦችን ለማደስ እና ለማዳበር ፍላጎት እንዳለን" የሚገልጽ ስምምነት ነው ብለዋል።

በዚሁ ጊዜ፣ ካርዲናል ፓሮሊን እንዳሉት “በቻይና መረጋጋት እንደሚመጣ” ያላቸውን ተስፋ ገልጿል።

“ምንም እንኳን መጀመሪያ ላይ የጳጳሳዊ ውክልና ወይም ሐዋርያዊ ቤተ ክርስቲያን ባይሆንም፣ አሁንም ግንኙነታችንን ሊያሳድግ እና ሊጨምር ይችላል። ግባችን ይህ ነው ብለዋል።

የሀገሩን ባሕል የተዋጀች ቤተክርስቲያን

እነዚህ ቃላት የተናገሩት በካርዲናል ፓሮሊን ከሻንጋይ ጳጳስ ጁሴፔ ሼን ቢን ጋር በመሆን ነው። “በቻይና የምትገኘውን ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔርን ፈቃድ የምትከተል፣ የቻይናን ጥሩ ባህላዊ ቅርስ የምትቀበል እና የቻይና ማኅበረሰብ ዛሬ የምትቀበለውን ቅዱስ እና የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን መገንባት እንቀጥላለን” ብለዋል ጳጳሱ።

የቻይናው ጳጳስ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን በአገራቸው ላለችበት ጊዜ አራት ነጥቦችን ዘርዝረዋል በመጀመሪያ፣ “የቻይና ቤተ ክርስቲያን እድገት ለክርስቶስ ወንጌል ታማኝ መሆን አለበት” እናም “ለባህላዊ የካቶሊክ እምነት” በማለት ተናግሯል።

አዲሲቷ ቻይና በተመሠረተችበት እ.አ.አ በ1949 ዓ.ም ቤተ ክርስቲያን “ከአዲሱ የፖለቲካ ሥርዓት ጋር ለመላመድ ስትጥር ምንጊዜም ለካቶሊክ እምነቷ ታማኝ ሆና ትኖራለች።

በዚያን ጊዜ “በቻይና መንግሥት የሚተገበረው የሃይማኖት ነፃነት ፖሊሲ የካቶሊክ እምነትን ለመለወጥ ምንም ፍላጎት አልነበረውም ፣ ነገር ግን ቀሳውስት እና የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን የቻይናን ሕዝብ ጥቅም ለማስጠበቅ እና ራሳቸውን ከውጭ ኃይሎች ቁጥጥር ነፃ ያደርጋሉ የሚል ተስፋ ነበረው።

ያለፉት ችግሮች

ጳጳስ ሼን ቢን ስለሁኔታው አስታውሰው የቻይና መንግሥት የአገሪቱ ካቶሊኮች ከቫቲካን ጋር ሃይማኖታዊ ግንኙነት ቢኖራቸው እንደማይቃወሟቸው በወቅቱ የመንግሥት ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ ዢ ዦንግቹን ቢያረጋግጡም እነዚህ ግን የተፈቀዱት በቅድመ ሁኔታ ብቻ ነበር ብለዋል። ከቻይና ሕዝብ ጥቅም ውጪ አልሄዱም፣ የቻይናን ሉዓላዊነት አልጣሱም፣ ቫቲካን በቻይና ላይ የነበራትን የጥላቻ ፖሊሲ ቀይራለች ብለዋል።

በተጨማሪም የሻንጋይ ጳጳስ ቀደም ሲል በቻይና ቤተ ክርስቲያንና በመንግሥት መካከል የተፈጠሩ ችግሮችን አስታውሰዋል፤ ይህ የሆነበት ምክንያት አንዳንድ ሚስዮናውያን “የክርስትና ሃይማኖትን የቻይናን ማኅበረሰብና ባሕል ለመለወጥ አስበዋል” ባላቸው አንዳንድ ሚስዮናውያን የተነሳ “የአውሮፓ ባሕል የበላይ እንደሆኑ አድርገው ስላሰቡ ነው በለዋል።

ይህ “ብዙ ቻይናውያን የተቃወሙት አልፎ ተርፎም የተጠላ” እና “በቻይናውያን መካከል የፍቅር ወንጌል እንዳይስፋፋ እንቅፋት ሆኗል” ብለዋል።

የቻይናዊነት  መንገድ

ዛሬ፣ የቻይና ሕዝብ “የቻይና ሕዝብን በቻይንኛ ዘይቤ በዘመናዊነት በማዘመን ታላቅ መታደስን” ሲከተል፣ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን “በተመሳሳይ አቅጣጫ መንቀሳቀስ አለባት” ሲሉ ጳጳስ ሼን ቢን አረጋግጠዋል። የዛሬው የቻይና ማህበረሰብ እና ባህል ከመቼውም ጊዜ በላይ የጠነከረ ነው ብለዋል።

ቻይናውያን ቄሶችን እና ምዕመናን “አገራቸውን እና ቤተክርስቲያናቸውን እንዲወዱ እና የቤተክርስቲያኗን እድገት ከህዝቡ ደህንነት ጋር በቅርበት እንዲያገናኙ” ጋብዟቸዋል። በዚህ ረገድ የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስን አባባል በመጥቀስ “ጥሩ ክርስቲያን መሆን ጥሩ ዜጋ ከመሆን ጋር የሚስማማ ብቻ ሳይሆን የዚያም ዋነኛ አካል ነው” ብለዋል።

ሁለት ሴት ተናጋሪዎች

በጳጳሳዊ ሁርባኒያና ዩኒቨርሲቲ በተካሄደው ጉባኤ ላይ ሁለት ሴቶች ከተናገሩት መካከል ነበሩ።

አንደኛው በቻይና የማህበራዊ ሳይንስ አካዳሚ የአለም ሀይማኖቶች ተቋም ፕሬዝዳንት ዜንግ ዚያኦዩን እንዳሉት ዛሬ በቻይና እንደ መንግስት 98 ሀገረ ስብከት፣ 9 ተቋማት፣ 6,000 አብያተ ክርስቲያናት እና 6 ሚሊዮን አማኞች ከ8,000 በላይ ገዳማዊያን/ገዳማዊያት፣ ቀሳውስት ይገኛሉ “በሙሉ የእምነት ነፃነት ዋስትና” ሥር ሃይማኖታቸውን እያካሄዱ ይገኛሉ ብለዋል።

በቻይና እና በቅድስት መንበር መካከል የተደረገው ስምምነት እንደገና እንደሚታደስ ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል።

ከዚያ በኋላ በሚላን የካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ የቻይና ታሪክ መምህር የሆኑት ፕሮፌሰር ኤሊሳ ጁኒፔሮ “በቻይናና በዓለም ላይ የካቶሊክ ሚስዮናውያን ከፍተኛ እና ብዙ ጊዜ የማይገመተው ተጽዕኖ” አስታውሰዋል።

አክለውም “ከቻይና ካለው ቤተክርስቲያን የለውጡ ተነሳሽነት መጥቷል ይህም ቤተክርስቲያኗን በተልዕኮ ግዛቶች ውስጥ የለወጠ ነው” በማለት አጽናፈ ሰማይን ለመገመት በመርዳት “ከእንግዲህ የአውሮፓ ባህል ባለቤት ያልሆነች” ስትል ተናግራለች። ቅድስት መንበር ምክር ቤቱን ለማክበር ባለው ጽኑ አቋም እና ተግባር… እምነት በቻይናውያን ቀሳውስት ላይ ጥሏል ብለዋል።

“ይህ፣ ቤተክርስቲያን በቀጣዮቹ አሥርተ ዓመታት ውስጥ ያጋጠሟትን ችግሮች እንድትቋቋም በእጅጉ ረድቷል ” ካሉ በኋላ ንግግራቸውን ደምድመዋል።

 

 

22 May 2024, 15:51