ብጹእ ካርዲናል ፓሮሊን በ 'ሰው ሁን' (#BeHuman) ዝግጅት ላይ ከነበሩ ተሳታፊዎች ጋር ብጹእ ካርዲናል ፓሮሊን በ 'ሰው ሁን' (#BeHuman) ዝግጅት ላይ ከነበሩ ተሳታፊዎች ጋር 

ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን ‘ያለ ውይይት ሰላም አይኖርም’ አሉ

የቅድስት መንበር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብጹዕ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን በሮም የሚካሄደው የ “ሰው እንሁን” ዐብይ ዝግጅት አካል የሆነው እና 30 የሚሆኑ የኖቤል ተሸላሚዎች የተሰበሰቡበትን የቫቲካን ‘የሰላም ውይይት መድረክ’ ማስጀመራቸው ተነግሯል።

  አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

“ራስን የመከላከል የማይገሰስ መብት እንዳለ የማምን ብሆንም፥ ጦርነት ሁል ጊዜ በጦርነቱ የሚሳተፉ አካላት የሚንኮታኮቱበት ብቻ ሳይሆን የሰብአዊነት ውድቀትም ጭምር ነው”

ከላይ ያለውን የጠቀሱት የቫቲካን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብፁዕ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን በሮም የተካሄደውን ‘የሰላም መድረክ’ ሲከፈቱ የተናገሩት ነው።

ሁሉም ጦርነቶች ከሰው ልጅ ክብር ጋር የሚቃረኑ ሲሆኑ፥ ‘በተፈጥሮዋቸው ችግሮችን ለመፍታት የተቀርጹ ሳይሆን፣ ከዚህም ይልቅ ችግሮችን ሲያባብሱ ነው’ የሚስተዋለው።

ግንቦት 2 ቀን 2016 ዓ.ም. የተጀመረው ዝግጅት ብጹዕ ካርዲናሉን ጨምሮ የጓቲማላውን ሪጎበርታ መንቹ ቱምን፣ የሩሲያውን ዲሚትሪ ሙራቶቭ እና የየመኑን ታዋኮል ካርማንን ያካተተ ወደ 30 የሚጠጉ የኖቤል የሰላም ተሸላሚዎች የተገኙበት ሲሆን፥ የኔልሰን ማንዴላ ባለቤት የሆኑት ማሼል ማንዴላ እና የናሳ አስተዳዳሪ ቢል ኔልሰንን የመሳሰሉ ታዋቂ ሰዎች የተገኙበት ዝግጅት ነበር።

ይህ በ“ፍራቴሊ ቱቲ ጳጳሳዊ ተቋም” የተዘጋጀውን በሰብአዊ ወንድማማችነት ላይ ያተኮረው ሁለተኛው የዓለም አቀፍ ስብሰባ የሆነው “#ሰው እንሁን” ዘመቻ አርብ እና ቅዳሜ ነበር የተካሄደው።

በዚህ ዘመቻ የተሳተፉት ሳይንቲስቶች፣ ኢኮኖሚስቶች፣ ዶክተሮች፣ ሥራ አስኪያጆች፣ አትሌቶች እና ተራ ዜጎች ሲሆኑ፥ ሁሉም በወንድማማችነት መርህ ላይ በመንተራስ፣ ከጦርነት እና ከድህነት ሌላ አማራጭ ለመሻት የተሰባሰቡ ለህዝብ ክፍት የሆኑ አስራ ሁለት የመወያያ መድረኮችን የያዙ እንደሆኑ እና አንዳንዶቹም የቀጥታ ስርጭት ሽፋን እንደነበራቸው ተገልጿል።

ጦርነት የሰውን ክብር ይነካል

  “እግዚአብሔር ሰዎችን የፈጠረው በሰላም እንዲኖሩና ፍጥረትን እንዲጠብቁ እንጂ እንዲያጠፉት አይደለም”

ብጹእ ካርዲናል ፓሮሊን አጽንዖት ሰጥተው እንደተናገሩት ጦርነት የሰውን ክብር በማሳነስ እና እራሱን ከፍጥረት በተቃራኒ በማስቀመጥ ያለውን ሚና በመግለጽ፥ “የሌሎችን ክብር ማጥቃት ብቻ ሳይሆን የራስን ክብርም ጭምር ያሳንሳል” ብለዋል።

“ጦርነት ብቻ” የሚለውን ጽንሰ-ሐሳብ እንደገና ማጤን

እንደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ገለጻ፣ ዛሬ ላይ “ጦርነት ብቻ” የሚለው ጽንሰ-ሐሳብ ጥያቄ ውስጥ መግባት አለበት፥ ምክንያቱም “ግጭቶች በአንጻራዊ ሁኔታ ውስን በሆነበት ዘመን የመነጨ በመሆኑ ሲሆን፥ የኑክሌር እና የጅምላ አውዳሚ ጦር መሳሪያዎች በተስፋፉበት በዚህ ዘመን ይህ ጽንሰ-ሐሳብ በራሱ እንደ ከፍተኛ ችግር ይታያል” ብለዋል።

ከጦር መሳሪያ ይልቅ ዲፕሎማሲ ይቅደም

ብፁዕ ካርዲናሉ በመክፈቻ ንግግራቸው እሁድ ዕለት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ያወጁትን ‘ቡል ኦፍ ኢንዲክሽን ኦፍ ዘ ጁብሊ’ የተሰኘውን በቀይ ቀለም የታተመ መልዕክት በመጥቀስ፣ ያለ ውይይት እንዴት ሰላም እንደማይገነባ ብቻ ሳይሆን ጦርነት እንደሚቀሰቀስ ጭምር እና የዲፕሎማሲውን ድምጽ እንዴት በመሳሪያ እንደሚተካ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

በመቀጠልም ብጹዕ ካርዲናሉ በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሱ ተለይተው የቀረቡትን ሶስት በቁርጠኝነት መፈፀም ከሚገቡን ውስጥ የተካተቱትን ‘የፍትህ መጓደልን መንስኤዎች መፍታት፣ ፍትሃዊ ያልሆኑ እና የማይታለፉ እዳዎችን ማስተካከል እና የተራቡትን ማርካት በሚል የተቀመጡትን ጠቅሰዋል።

ዛሬ ባለው ዓለም ውስጥ ትልቅ ኢፍትሃዊነት የሆነው ድህነት

እንደ ብጹዕ ካርዲናል ፓሮሊን ገለጻ “ከኢፍትሃዊነት ነፃ መውጣት ነፃነትን እና ሰብአዊ ክብርን ያጎናጽፋል” ብቻም ሳይሆን “ማህበራዊ ፍትህን፣ በተለይም አሁን ባለው የሰው ልጅ ዋጋ የመገልገያ እና የሃብት መመዘኛዎች ላይ ብቻ የመተማመን ሰፊ ዝንባሌ ላይ በወደቀበት ሁኔታ መጠበቅ አስፈላጊ ነው” ብለዋል ።

የማህበራዊ ፍትህ እጦት የድህነት መነሻ እንደሆነ ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን አፅንዖት ሰጥተው በመግለጽ፣ አሁን ባለንበት ዓለም ካሉት ታላላቅ ኢፍትሃዊ ድርጊቶች አንዱ እንደሆነ እና “ብዙ ያላቸው በአንፃራዊነት ጥቂቶች ሲሆኑ ምንም የሌላቸው ደግሞ ብዙ ናቸው” ካሉ በኋላ፥ ይህ ደግሞ ብዙውን ጊዜ ወደ ጭፍንነት እና አክራሪ ሃይማኖተኝነት መጣበቅን ወደሚያመጣው የትምህርት እጦት ያጋልጠናል ብለዋል።

ዕዳ እና ወንድማማችነት

ከግለሰቦች ድህነት በተጨማሪ “የውጭ ዕዳዎችን መቋቋም ስለማይችሉ" አገሮች የጠቀሱት ካርዲናል ፓሮሊን፥ “እዳ የተገባበት መርህ መከበር አለበት የሚለውን መርህ እንደገና እያረጋገጥን ነው” ካሉ በኋላ፥ “የሕዝቦችን መሠረታዊ በህይወት የመቆየት እና የመልማት መብት ለማክበር” በህዝቦች መካከል ወንድማማችነትን እንደገና ማስፈን ያስፈልጋል ብለዋል።
 

13 May 2024, 16:38