በተባበሩ መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት በጋዛ ጦርነት ላይ ውይይት ሲያካሂድ በተባበሩ መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት በጋዛ ጦርነት ላይ ውይይት ሲያካሂድ  (2024 Getty Images)

ቅድስት መንበር በግጭት ምክንያት የሚገደሉት ሕፃናት ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን አስታወቀች

በተባበሩ መንግሥታት ድርጅት የቅድስት መንበር ተወካይ ሞንሲኞር ሮበርት መርፊ በኒውዮርክ በተካሄደው የፀጥታው ምክር ቤት ጉባኤ ላይ ሕፃናትን እና የጦር መሣሪያን በመታገዝ የሚካሄዱ ግጭቶችን በማስመልከት ባሰሙት ንግግር፥ ግጭቶች ባሉባቸው እካባቢዎች እየጨመረ የመጣውን ግፍ ለመከላከል ተጨባጭ እርምጃ እንዲወሰድ አሳስበዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን
በተባበሩት መንግስታት የቅድስት መንበር የቅድስት መንበር ምክትል ቋሚ ታዛቢ ሞንሲኞር ሮበርት መርፊ፥ በዓለም ዙሪያ በትጥቅ ትግል የሚገደሉ ሕጻናት ጥር በእጅጉ መበራከቱን ገልጸው የዓለም ማኅበረሰብ ጥበቃ አለማድረጉን በማስታወስ ተቃውሞአቸውን ገልጸዋል።

ሞንሲኞር ሮበርት መርፊ ይህን የገለጹት የፀጥታው ምክር ቤት ያለፈው ሐሙስ ሰኔ 20/2016 ዓ. ም. በ25ኛው ጉባኤ ላይ በአንቀጽ 1261 ያሰለፈውን ውሳኔ እና 75ኛው የጄኔቭ ስምምነቶችን ምክንያት በማድረግ ባካሄደው ግልጽ ውይይት ወቅት እንደ ነበር ታውቋል።

ከ2022 ወዲህ በትጥቅ ትግል የተገደሉት ህጻናት ቁጥር በሦስት እጥፍ ጨምሯል
ሞንሲኞር ሮቤርት መርፊ በመግለጫ በትጥቅ ትግል የሚገደሉ ህጻናት በተለይም ፈንጂ መሣሪያዎች ከፍተኛ ጉዳት በሚያደርሱባቸው አካባቢዎች የሚሞቱ ሕጻናት ቁጥር መጨመሩ አሳሳቢ እንደሆነ ተናግረዋል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ የአቶ አንቶኒዮ ጉቴረዝ የቅርብ ጊዜ ሪፖርት እንዳመለከተው፥ እንደ ጎርጎሮሳውያኑ ከ 2022 ዓ. ም. ጀምሮ በትጥቅ ትግል የሚሞቱት ሕጻናት ቁጥር በሦስት እጥፍ መጨመሩ ሲነገር፥ ይህም በልዩ ልዩ የዓለም ክፍሎች በጦርነት ምክንያት ከሚሞቱ ሰዎች ቁጥር መካከል ከፍተኛው እንደሆነ ታውቋል።

በሺህ የሚቆጠሩ ሕጻናት የልጅነት ጊዜያቸውን ተነፍገዋል
ሞንሲኞር ሮቤርት መርፊ ቅድስት መንበር ያላትን ስጋት ሲገልጹ፥ ለህፃናት አስተማማኝ መሸሸጊያ መሆን በሚገቡ በተለይምለ በትምህርት ቤቶች፣ በሆስፒታሎች እና በአምልኮ ሥፍራዎች ሳይቀር ሞትን የሚያስከትሉ የጦር መሣሪያዎች ጥቅም ላይ መዋላቸውን አስታውሰው፥ ሕጻናትን ለውትድርና አገልግሎት መመልመልን ጨምሮ የሕጻናትን እና ቀላል የጦር መሣሪያ ሕገ-ወጥ ዝውውር በሕጻናት ላይ እያደረሰ ያለውን ተጽዕኖንም ጠቁመዋል።

“እነዚህ ግፎች በሕፃናት ላይ የሚደርሱት ተጽእኖ ቀላል አይደለም” ያሉት ሞንሲኞር ሮቤርት መርፊ፥ “በሺዎች የሚቆጠሩ ሕጻናት የልጅነት ጊዜያቸውን በደስታ እንዲያሳልፉ የማድረግ እና የመከታተል መሠረታዊ ግዴታ እንዳለብን እንገነዘባለን” ብለዋል።

የሕጻናት እና የትጥቅ ትግል አጀንዳዎችን ቶሎ ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል
የቫቲካን ልኡካን ለተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት ባቀረቡት ሦስት ነጥቦች፥ የመጀመሪያው ሕፃናትን ከአደጋ ለመከላከል የሚያግዝ ሰብዓዊ ዕርዳታ ወሳኝ እንደሆነ፥ ሁለተኛው የትጥቅ ትግል በልጆች ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለመገደብ የጦር መሣሪያ ምርትን፣ ክምችት እና አጠቃቀምን ማቆም እንደሚያስፈልግ፥ በመጨረሻም የፀጥታው ምክር ቤት የሥራ ቡድን እስካሁን ተግባራዊ ያላደረጋቸውን ሕጻናትን እና የትጥቅ ትግል የሚመለከቱ አጀንዳዎች ተግባራዊ ለማድረግ ሁኔታዎችን ማመቻቸት ለተግባራዊነታቸውም ዋስትና መስጠት እንደሚገባ ሞንሲኞር ሮቤርት መርፊ አሳስበዋል።

“ይህን ተግባራዊ አለማድረጉ ውድቀትን በማስከተል አንዳንድ ለአደጋው ተጋላጭ በሆኑ ሕጻናት ላይ ተጨባጭ ውጤት አለው” በማለት አክለው አስገንዝበዋል።


 

01 July 2024, 16:49