የአሜሪካ ቢ52 ቦንብ ጣይ አውሮፕላን በሮማኒያ የአሜሪካ ቢ52 ቦንብ ጣይ አውሮፕላን በሮማኒያ   (ANSA)

ቅድስት መንበር በኒውክሌር የጦር መሣሪያዎች ላይ ያላትን 'ጥልቅ ስጋት' ገልጻለች።

በተባበሩት መንግስታት የጄኔቫ ዋና መሥሪያ ቤት በተካሄደው ስብሰባ ላይ ሊቀ ጳጳስ ኤቶሬ ባሌስትሬሮ በኒውክሌር ጦር መሳሪያዎች ስለሚመጣው "ሕልውና ስጋት" አስጠንቅቀዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

በጄኔቫ በተባበሩት መንግስታት የቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ ሊቀ ጳጳስ ኤቶሬ ባሌስትሬሮ የተባበሩት መንግስታት የኒውክሌር ጦር መሳሪያ አለመስፋፋት ላይ ለቀረበው ኮሚቴ ንግግር አድርገዋል።

ሊቀ ጳጳሱ ለውይይቱ ለተሰበሰቡት "የ2026 ዓ.ም ሁለተኛው የዝግጅት ኮሚቴ የኑክሌር ጦር መሳሪያ አለመስፋፋት ላይ የተደረገው ስምምነት ሁለተኛ ደረጃ አዘጋጅ ኮሚቴ" በሚል ርዕስ - የቅድስት መንበር የኑክሌር መስፋፋትን በተመለከተ ቅድስት መንበርን "በጥልቅ ያሳሰባት ጉዳይ እንደ ሆነ” ገልጿል።

ለንውክሌር ጦር መሳሪያዎች የሚደርገው ወጪ መጨመር

ሊቀ ጳጳስ ባሌስትሬሮ እንደተናገሩት የኑክሌር ጦር መሳሪያዎች አሁን ባለው “አስጨናቂ ለጦርነት ምቹ የሆነ አካባቢ” እና “በቀጠለው የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ማዘመን እና መስፋፋት” ጉዳይ ላይ ቅድስት መበር እንዳሳሰባት ገልጿል።

በኒውክሌር ጉዳዮች ላይ የቫቲካን ዲፕሎማሲ ልዩ ገጽታ የኑክሌር ጦር መሳሪያ መታጠቅ፣ ለመከላከልም ቢሆን፣ ከሥነ ምግባር አኳያ ስህተት ነው። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በቅርቡ የኒውክሌር ጦር መሣሪያዎችን የማምረትም ሆነ የማከማቸት ጉዳዮችን በተመለከተ ያላቸውን ስጋት በመግለጽ ሊቀ ጳጳስ ባለስትሬሮ ያሰመሩበት መርሕ ነው።

ሊቀ ጳጳሱ በመቀጠል “ከኑክሌር ጦር መሣሪያ ጋር በተያያዘ የሚደረጉ ወታደራዊ ወጪዎች ቀጣይ ዕድገት” እና “በእዚህ ጉዳይ ላይ የሚደርገው ሰጣ ገባ መጨመር እና ስለ አጠቃቀማቸው ማስፈራሪያዎችን መግለጽ” ቅድስት መንበር ያሳስባታል ብለዋል። እንዲህ ያሉት ድርጊቶች “በአጠቃላይ የሰውን ልጅ ሕልውና አደጋ ላይ የሚጥሉ ተግባራት ናቸው ሲሉ አክለው ገልጸዋል።

ሶስት ተጨባጭ ሀሳቦች

ሊቀ ጳጳስ ባሌስትሬሮ በመቀጠል ቅድስት መንበር በቀረበው ውይይት ላይ ሦስት ዋና ዋና አስተዋጽኦዎችን ማድረግ እንደምትፈልግ ተናግሯል።

በመጀመሪያ ደረጃ አለመስፋፋት እና ትጥቅ ማስፈታት ከህጋዊ ግዴታዎች በተጨማሪ "ለሁሉም የሰው ቤተሰብ አባላት የስነ-ምግባር ግዴታዎች" መሆናቸውን መገንዘብ አስፈላጊ ነው ብለዋል።

ሊቀ ጳጳስ ባሌስትሬሮ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እ.ኤ.አ. በ2019 ዓ.ም ናጋሳኪን በጎበኙበት ወቅት እንዳሉት “ሰላምና ዓለም አቀፋዊ መረጋጋት የጋራ ጥፋትን በመፍራት ወይም ሙሉ በሙሉ የመጠፋፋት ስጋት ላይ ለመገንባት ከሚደረገው ጥረት ጋር ተያዞ ተፈጻሚነትን ሊያገኙ አይችሉም።  ሊገኙ የሚችሉት ዓለም አቀፋዊ የአብሮነት እና የትብብር ሥነ-ምግባርን መሰረት በማድረግ ብቻ ነው” ሲሉ መናገራቸውን አስታውሰዋል።

በሁለተኛ ደረጃ፣ ሊቀ ጳጳስ ባሌስትሬሮ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለውን የኒውክሌር ጦር መሣሪያ ክምችት ለመቀነስ ያለመ “ከልብ ውይይት” እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል።

እናም በመጨረሻም ሊቀ ጳጳሱ ለኒውክሌር ጦር መሳሪያ የሚወጣው ገንዘብ በተሻለ መልኩ ለሰብአዊ ፕሮጀክቶች ሊውል እንደሚችል ጠቁመዋል። በዚህም ምክንያት፣ “ለጦር መሣሪያና ለሌሎች ወታደራዊ ወጪዎች ከሚውለው ገንዘብ የተወሰነው” የሚደግፈው፣ የቅድስት መንበር የረዥም ጊዜ የድህነት ፈንድ ለመመሥረት ያቀረበችውን ሐሳብ በድጋሚ ገልጿል።  

ሊቀ ጳጳስ ባሌስትሬሮ ንግግራቸውን ሲያጠናቅቁ የቅድስት መንበር “ጽኑ እምነት” ከኑክሌር ጦር መሣሪያ የጸዳ ዓለም “የሚቻልም አስፈላጊም ነው” በማለት በድጋሚ አረጋግጠዋል።

 

24 July 2024, 11:35