በስፔን ውስጥ የሚገኘው በቻንዳቪላ ቤተ መቅደስ በስፔን ውስጥ የሚገኘው በቻንዳቪላ ቤተ መቅደስ  

ቫቲካን ለቻንዳቪላ፣ ስፔን የሐዘንተኛዋ እመቤታችን ቅድስት ማርያም ቤተ መቅደስ እውቅና ሰጠች!

በስፔን ውስጥ በቻንዳቪላ ቤተ መቅደስ ውስጥ ለሐዘንተኛው ቅድስት እመቤታችን ማርያም ያለውን ጥልቅ ፍቅር እና እምነት ማደርን በተመለከተ የመሪዳ-ባዳጆዝ ሊቀ ጳጳስ በላቲን ቋንቋ "ኒሂል ኦብስታት" (ምንም የሚያደናቅፍ ነገር የለም) በተሰኘው መልእክት ባቀረቡት ጥሪ መሰረት በስፔን ሁለት ወጣት ልጃገረዶች መንፈሳዊ ራዕይ አጋጥሟቸዋል በተባለበት ሥፍራ በሁለተኛው የአለም ጦረንት ማብቂያ ላይ ባዩት ርዕይ መሰረት ለዚህ መንፈሳዊ ግልጸት በቅድስት መንበር የእምነት አስተምህሮን የሚከታተለው ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት የግልጸቱን ወይም የራዕይውን ሁኔታ ካጠና በኋላ የአምልኮ ሥፍራ ይሆን ዘንድ ፈቃድ መስጠቱ ተገልጿል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

የእምነት አስተምህሮ የሚመለከተው የቅድስት መንበር ጽሕፈት ቤት የሜሪዳ-ባዳጆዝ ሊቀ ጳጳስ ሆሴ ሮድሪጌዝ ካርባሎ በታቀደው “ኒሂል ኦብስታት” አዋጅ እንዲቀጥል ቅድስት መንበር “ፍቃዱን በደስታ ሰጠች” ስለዚህም “የቻንዳቪላ ቤተ መቅደስ—የአንድ ወራሽ የሆነው ብዙ የቀላል ታሪክ፣ ጥቂት ቃላት፣ እና ግን ብዙ አምልኮ ወደሱ ለመቅረብ ለሚፈልጉ አማኞች፣ የውስጥ ሰላም፣ መጽናኛ እና የመለወጥ ቦታ መስጠቱን ሊቀጥል ይችላል ሲሉ ገልጿል።

በቅድስት መንበር የሐያማኖት አስተምህሮን የሚመለከተው ጸሕፈት ቤት አስተዳዳሪ ብፁዕ ካርዲናል ቪክቶር ማኑኤል ፈርናንዴዝ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በነሐሴ 16/2016 ዓ.ም ባጸደቁት ደብዳቤ ላይ ይህንኑ አስረድተዋል።

እ.አ.አ በ1945 ዓ.ም የስፔኑ ሊቀ ጳጳስ በጻፉት ደብዳቤ መሠረት ሁለት ልጃገረዶች ድንግል ማርያምን እንደ ሐዘንተኛይቱ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ሆና ያዩት በፖርቱጋል ድንበር አቅራቢያ በምትገኘው በኤክትራማዱራ በምትገኘው የስፔን ከተማ ቻንዳቪላ በሚባልበት ሥፍራ እንደ ነበረም በደብዳቤው ላይ ተመላክቶ ነበር።

እ.አ.አ በግንቦት 17/2024 ዓ.ም በቅድስት መንበር የሐይማኖት አስተምህሮዎችን የሚመለከተው ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት በታተመው መመሪያ መሰረት በላቲን ቋንቋ "ኒሂል ኦብስታት" (ምንም የሚያደናቅፍ ነገር የለም) "ብዙ የመንፈስ ቅዱስ ድርጊት ምልክቶች" እውቅና ሰጥቷል፣ ምንም እንኳን "ስለ ክስተቱ ከተፈጥሮ በላይ የሆነ ትክክለኛነት በእርግጠኝነት ባይገለጽም. ." ሲሉ ተናግረዋል።

የማርሴሊና እና የአፍራ ታሪክ

በቻንዳቪላ የእመቤታችን ቤተ መቅደስ ላይ ያለው እምነት የጀመረው በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማብቂያ አካባቢ እነዚህን ክስተቶች በተለዩት ሁለት ልጃገረዶች የአሥር ዓመቷ ማርሴሊና ባሮሶ ኤክስፖሲቶ እና የአሥራ ሰባት ዓመቷ አፍራ ብሪጊዶ ብላንኮ መንፈሳዊ ተሞክሮ ነው። እ.አ.አ ከግንቦት 1945 ዓ.ም ጀምሮ ተመሳሳይ ቦታ ላይ የተከሰተ ክስተት ነበር።

"ማርሴሊና" ካርዲናል ፈርናንዴዝ እንደ ጻፉት ከሆነ "መጀመሪያ ላይ በሰማይ ላይ ጥቁር ቅርጽ አየች። በሌላ ጊዜ ደግሞ ይህ ቅርጽ በከዋክብት የተሞላ ጥቁር መጎናጸፊያ ያለው የሶሮቭስ ድንግል መሆኗ ይበልጥ ግልጽ ሆነ። ይህች ልጅ ከራዕዩ በላይ፣ ድንግል በግንባሯ ላይ የሳመቻትን እና ያቀፈቻት ጥልቅ ልምድ እንዳላት ካርዲናል ገልጿል፣ በጣም የሚያምር መልእክት ነበር ሲሉ አክለው ተናግረዋል።

ምንም እንኳን ቀናቶች እያለፉ ሲሄዱ እሷም ሆነች አፍራ ምስሉ የሐዘን ድንግል መሆኗን ለይተው አውቀውታል፣ ከሁሉም በላይ ጎልቶ የሚታየው የድንግል መገኘት መጽናኛን፣ ማበረታቻን እና በራስ መተማመንን የሚፈጥር ነው። ድንግል ማርሴሊናን በደረቁ መሬት ላይ በሰሌን የተሰራ የእግር መከላከያ ላይ እሾህ እና ሹል ድንጋዮች ላይ በጉልበቷ እንድትሄድ ስትጠይቃት፣ ይህን የምታደርገው ስቃይ እንዲደርስባት አልነበረም፣ ይልቁኑ  ከዚህ በተቃራኒ ‘አትፍሩ፣ ምንም አይደርስባችሁም" የሚለውን ጥንካሬ ለማስተማር እንደ ነበረ ካርዲናሉ በጽሑፋቸው ገልጸዋል።

የማርያም ርህራሄ

“ይህ የድንግል ጥሪ፣ በፍቅሯ እንድትታመን፣” ረድቷታል ያሉት ካርዲናሉ በመቀጠልም  “ለዚህች ምስኪን እና በመከራ የምትሰቃይ ሴት ልጅ ተስፋ ሰጥቷታል፣ እና ደግሞ የክብር ስሜትን እንዲሰማት አድርጓታል። ያ ቀላል መጎናጸፊያ ከሸንበቆና ከሳር የተሠራው እመቤታችን የልጅቷን ጉልበቶች የጠበቀችበት ነገር ነበር፣ የማርያምን ርኅራኄ የሚገልጽ ምልክት አይመስላችሁም ወይ ሲሉ ጥያቄ አንስተዋል።

አክሎም “በተመሳሳይ ጊዜ ይህ የውበት ተሞክሮ ነበር፣ ምክንያቱም ድንግል በስፔን በኤክትራማዱራ ትንንሽ መንደሮች ውስጥ በምሽት ሊደነቅ እንደሚችል በብርሃን ህብረ ከዋክብት የተከበበች ስለነበረች ነው።

አስተዋይ የአገልግሎት ሕይወት

ከተከሰቱት ራእዮች በኋላ ካርዲናል ፈርናንዴዝ እንደተናገሩት ሁለቱ ሴት ልጆች በበጎ አድራጎት ስራዎች በተለይም የታመሙትን፣ አረጋውያንን እና ወላጅ አልባ ህጻናትን ለመንከባከብ ራሳቸውን በመሰጠት “ልባም እና ግልጽ ያልሆነ ሕይወት” መሩ። ያገኙትን የድንግልን ፍቅር መጽናኛ ተቀብለው ኖሩ ሲሉ ጽፈዋል።

የመንፈስ ቅዱስን ተግባር የሚያመለክቱ ብዙ ገጽታዎች

በእነዚህ ሁሉ ምክንያቶች ብፁዕ ካርዲናል ፈርናንዴዝ እንዲህ ሲሉ ጽፈዋል፡- “በዚህ ውብ አምልኮ ውስጥ ማንም የሚቃወመው ምንም ነገር የለም፣ ይህም በቅድስት እናታችን በናዝሬት ማርያም ላይ የምናየው ተመሳሳይ ትህትናን ያሳያል። ከስፔን እና ከፖርቱጋል በመጡ ብዙ ምዕመናን ውስጥ መንፈስ ቅዱስ በዚህ ቦታ ወደ መለወጥ፣ ፈውሶች እና ሌሎች ጠቃሚ ምልክቶች ይለውጣቸውል ብለዋል።

23 August 2024, 15:32