የቫቲካን ፍርድ ቤት የፍትህ ቢሮ የቫቲካን ፍርድ ቤት የፍትህ ቢሮ  ርዕሰ አንቀጽ

“ፍትሃዊ እና ግልፅ የፍርድ አሰጣጥ ሂደት የመከተል አስፈላጊነት”

በሎንደን ከሚገኝ የሕንጻ ግዢ ጋር በተያያዘ የቫቲካን ፍርድ ቤት የሰጠው ፍርድ ፍትሃዊ እና ግልፅ መሆኑ ተነግሯል። የፍርድ ሂደቱን በማስመልከት በቅርቡ በታተመው ውሳኔ ጠቅላላ ዕይታ ላይ የቅድስት መንበር መገናኛዎች ርዕሠ አንቀጽ ዝግጅት ክፍል ሃላፊ አንድሬያ ቶርኔሊ አስተያየቱን አስፍሯል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

በሎንደን ስሎአን ጎዳና የሚገኘውን ሕንፃ ሽያጭ ላይ የተሰጠውን ውሳኔ በተመለከተ ፍርድ ቤቱ ይፋ ያወጣቸውን ረጅም እና ውስብስብ ምክንያቶችን በማንበብ ከሚነሱት በርካታ ጉዳዮች መካከል በተለይም ሁለቱን ማሳወቅ እንደሚፈልግ አንድሬያ ቶርኔሊ ገልጿል።

የመጀመሪያው በቫቲካን ሙዚየሞች ሁለገብ አዳራሽ ውስጥ ከ86 ጊዜ በላይ ችሎቶች የተካሄዱበትን የፍርድ ሂደት የሚመለከት ነው። የፍርድ አሰጣጥ ሂደቱ መከላከያ ከማቆም መብት እና የመገናኛ ብዙሃን መግለጫዎችን ከማረጋገጥ ይልቅ ፍጹም በተቃራኒ መንገድ የተከናወነ ነበር። በፕሬዚዳንት ጁሴፔ ፒኛቶን የሚመራው የፍርድ ቤት ውሳኔ ወንጀሎቹን በድጋሚ በማረጋገጥ እና አንዳንድ ተከሳሾችን ከተጠረጠሩበት ወንጀል ነጻ ማድረጉ የፍትህ አራማጅን ጥያቄ አልተከተለም። ከሁሉም በላይ መስቀለኛ ጥያቄዎችን በክርክሩ መሐል አስቀምጧል። ተከሳሾቹ በሚገባ የተዋቀረ መከላከያ ጣልቃ እንዲገባ ሰፊ ዕድል የሰጠ ሲሆን እውነታዎችን እና ሠነዶችን ምንም ሳያስቀሩ መርምሯል። ምንም እንኳን ቫቲካን እንደ ፈረንሳይ እና ጣሊያን በተቃራኒ የተለየ የምርመራ ሥርዓት ቢኖራትም በቅድመ-ምርመራው ደረጃ በአቃቤ ሕግ እና በመከላከያ መካከል “ኃይለኛው ያሸንፋል” ለሚለው መርህ ቅድሚያን አልሰጠም። እዚህ ላይ ፍትሃዊ የፍርድ ሂደቱ በመከላከል መብት እና ከወንጀል ነጻ መሆንን ግምት ውስጥ በማስገባት መርሆው ሙሉ በሙሉ ዋስትናን በመስጠት ተካሂዷል። ከዚህም በላይ እነዚህ መርሆዎች አሁን ባለው ደንብ ውስጥ በደንብ የተገለጹ ናቸው። የፍርድ ችሎቱ የቅጣት ውሳኔ ምክንያቶች የጣሊያን የዳኝነት መስፈርት ያወጣቸውን የተወሰኑ ፍርዶችን የሚያመለክቱ በመሆናቸው ትኩረትን የሚስቡ ናቸው።

ሁለተኛው የገንዘብ አጠቃቀምን እና የተጠያቂነት አስፈላጊነትን የሚመለከት ነው። ባለፈው ሳምንት በተጠናቀቀው የሲኖዶሳዊነት ጉባኤ ላይ በጸደቀው የመጨረሻ ሠነድ ውስጥ በግልጽነት ላይ ያተኮሩ አንቀጾች ተዘርዝረዋል። ይህም “በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በሥልጣን ላይ ያሉ ሰዎች በድርጊታቸው እና ውሳኔያቸው ሊጠየቁ አይገባም” የሚል አንድምታ ያለው እንደሆነ ተመልክቷል። በፍርድ ቤቱ የተረጋገጠው የልዩ ልዩ ጉዳዮች ሃላፊነት ምንም ይሁን ምን ከ 200 ሚሊዮን ዩሮ ያላነሰ የራፋኤል ሚንቾኔ ፈንድ ውስጥ ያለው አደገኛ ኢንቬስትመንት እጅግ ብዙ ሥራ የተሠራበት አሳዛኝ ታሪክ ነው። “ተጠያቂነትን” ያላካተተ እና እንደ ቤተ ክርስቲያን እውነታ ባለ ግምታዊ የብድር አሠራር መከተል ምን ያህል አስከፊ እንደሆነ ይናገራል። እነዚህ የቤተ ክርስቲያንን ተፈጥሮ እና ልዩነት የማይወክሉ አስተሳሰቦች ናቸው። የሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ተተኪ ተልዕኮን የሚያገለግሉ ንብረቶችን ሲያስተዳድሩ የ ‘መልካም የቤተሰብ አባት’ ጥበብ ሥራ ላይ በሚገኙ ሕጎች ውስጥ በግልጽ የተጠቀሰውን እና እጅግ አስፈላጊ የሆኑ አካሄዶችን ወደ ጎን የሚሉ ወይም የማያውቁ የሚመስሉ አመለካከቶች ናቸው።

ኢንቨስትመንት ማብዛት የሚያስከትለውን ስጋትን ማመዛዘን፣ ከአድልዎ መራቅ ከሁሉም በላይ ደግሞ አንድ ሰው የሚያስተዳድረውን ገንዘብ ለግል ጉዳይ ከማዋል መቆጠብ በሎንደን ከሚገኝ የሕንጻ ግዢ ጉዳይ የምንማረው ትምህርት ነው።

በቅድስት መንበር ሥርዓት ውስጥ ጥፋተኞች ራሳቸው የችሎቱ ርዕሠ ጉዳይ ሆነው እውነታዎች ሁለተኛ እንዳይደገሙ በማሰብ ወደ ብርሃን እንዲወጡ ማድረጋቸው መልካም ነው።

 

31 October 2024, 14:29