የሩስያ እና የዩክሬይን ጦርነት የሩስያ እና የዩክሬይን ጦርነት  (AFP or licensors)

ቅድስት መንበር ሲቪሎችን ከአቶሚክ ጨረር ለመከላከል የተገቡ ስምምነቶችን ማጽደቋ ተነገረ

በኒውዮርክ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ገብርኤል ካቻ የሲቪል ማኅበረሰብ ደኅንነት እና ጤና ለአቶሚክ ጨረሮች እንዳይጋለጥ ለመጠበቅ አግባብነት ያላቸውን ስምምነቶች ማፅደቅ ተገቢነት ያለው ነው ብለው፥ በዩክሬን የኑክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ አካባቢ የተፈጠረው ግጭት ከቁጥጥር ውጭ የሆነ የአቶሚክ ጨረር መለቀቁ ከፍተኛ አደጋን በማድረስ ስጋት መፍጠሩን ገልጸዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ቅድስት መንበር የኑክሌር ጦር መሥሪያዎች ክልከላ እና አጠቃላይ የኑክሌር-ሙከራ እገዳ ስምምነት መጽደቅ ይገባል ስትል አጥብቃ ማሳሰቧን በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ገብር ኤል ካቻ ሰኞ ጥቅምት 11/2017 ዓ. ም. የአቶሚክ ጨረር ውጤቶችን አስመልክቶ በአጀንዳ ቁጥር 48 ላይ በተገለጸው ላይ 79ኛው የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ አራተኛ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ተናግረዋል።

ሊቀ ጳጳሱ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአቶሚክ ጨረር ውጤቶች ሳይንሳዊ ኮሚቴ እስካሁን ላከናወናቸው ጉልህ ሥራዎች እና የጨረር ተጽእኖ እና ስጋቶች ላይ ግንዛቤ በማስጨበጥ ለውሳኔው መሻሻል አስተዋጽኦ በማበርከቱ አድናቆታቸውን ገልጸዋል። ቋሚ ታዛቢው፥ “ይህ ጥናት የሰዎች ደህንነት እና ጤናን ለአቶሚክ ጨረር ከመጋለጥ ጋር ተያይዘው ከሚመጡ አደጋዎች ለመጠበቅ ዓለም አቀፍ ጥረቶችን ለመደገፍ አስፈላጊ ነው” ሲሉ አጽንዖት ሰጥተዋል።

በጤና እና በአካባቢ ላይ የሚያስከትላቸው ውጤቶች
የኒውክሌር ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ላይ ከፍተኛ ጭማሪ እንዳሳየ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ካቻ አስጠንቅቀው፥ “መንግሥታት እነዚህ መሣሪያዎች በጤና እና በአካባቢ ላይ የሚያስከትሉትን መዘዞች ከግምት ውስጥ የሚያስገቡ ፖሊሲዎችን መተግበራቸው ወሳኝ ነው” ሲሉ ተናግረዋል።

በዚህም ምክንያት በተለያዩ የጤና ነክ ጉዳዮች ላይ የአቶሚክ ጨረር በሰውነት የደም ዝውውር፣ ኒውሮሎጂካል እና የበሽታ መከላከያ ሥርዓቶች ላይ የሚያሳድረውን ተጽእኖ በማጥናት ላይ ያለውን የኮሚቴውን የሥራ መርሃ ግብር የቅድስት መንበር የምትደግፍ መሆኑን ገልጸዋል።

“በእነዚህ ጠቃሚ ቦታዎች ላይ ምርምርን በማስቀደም የአቶሚክ ጨረር ለሚያስከትለው ተፅእኖ የበለጠ ሰፊ ግንዛቤ ማግኘት እንደሚቻል እና በዚህም የሕዝብ ጤናን እና አካባቢን ለቀጣይ ትውልድ ለማስረከብ ውጤታማ እርምጃዎችን ተግባራዊ ለማድረግ ያስችላል” ሲሉ አስረድተዋል።

በሴቶች እና በልጆች ላይ የሚደርስ ጉዳት
ቋሚ ታዛቢው እንደገለጹት፥ በተሻለ ሁኔታ በሠነድ የተደገፈ የኒውክሌር ፈንጂዎች አጠቃቀም ላይ ፍተሻ በማድረግ በተለይም በሴቶች፣ በሕጻናት፣ በፅንሰ እና በነባር ተወላጆች ላይ የሚደርሰውን ጎጂ ውጤት ነቅፈዋል።

ሊቀ ጳጳሱ በመቀጠልም፥ ቅድስት መንበር በተለይም በዛፖሪዝዝሂያ የኑክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ አካባቢ ያለውን ግጭት በተመለከተ ከቁጥጥር ውጭ የሆነ የአቶሚክ ጨረር መለቀቅ ቅድስት መንበርን በከፍተኛ ስጋት ውስጥ እንዳስገባት ገልጸው፥ የዚህ መሣሪያ ኢላማ መሆን አካባቢን አደጋ ላይ የሚጥል ብቻ ሳይሆን በአቅራቢያው ያሉትን ሕዝቦች ጤና እና ደህንነት አደጋ ላይ መጣሉን ሊቀ ጳጳስ ካቻ አስታውሰዋል።

“ይህ ሁኔታ በግጭት ዞኖች ውስጥ ከሚገኙት የኑክሌር ተቋማት ጋር ተያይዘው የሚመጡ አደጋዎችን ለመቀነስ፣ ለሰዎች እና ለጋራ መኖሪያ ምድራችን ደኅንነት ቅድሚያ እንዲሰጠው አስቸኳይ ትኩረት እና እርምጃ እንዲወሰድ ይጠይቃል” ሲሉ አሳስበዋል።

የውል ስምምነት አስፈላጊነት
ቋሚ ታዛቢው ሊቀ ጳጳስ አቡነ ገብርኤል ካቻ በዚህ ረገድ የኑክሌር ጦር መሣሪያ ክልከላ እና አጠቃላይ የኑክሌር-ሙከራ እገዳ ስምምነትን ለማጽደቅ ቅድስት መንበር ጥሪ ማቅረቧል ተናግረው፥ እነዚህ ስምምነቶች ለጎጂ ጨረር መጋለጥን ለመከላከል እና ለመቀነስ፣ አካባቢን ለመጠበቅ እና ንጹሃን ሰዎችን ከአቶሚክ ጨረር አደጋ ለመከላከል አስፈላጊ መሣሪያዎች ናቸው” ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።

 

22 October 2024, 17:32