የብጹዓን ጳጳሳት ጠቅላላ ጉባኤ በጦርነት የሚሰቃዩ ሰዎች ሕመም መጋራት እንደሚገባ አሳሰበ

ቅዱስ ሲኖዶስ ሰኞ መስከረም 27/2017 ዓ. ም. ባወጣው አምስተኛ ዙር መግለጫ የሐማስ ታጣቂዎች በእስራኤል ላይ ያደረሱት ጥቃት አንደኛ ዓመት መታሰቢያን ምክንያት በማድረግ ለሰላም የተደረገ የጸሎት እና የፆም ቀን፣ ሴቶች በቤተ ክርስቲያን ያላቸውን ሚና እና ሊኖር የሚገባውን የእርስ በርስ መገናኛ ድልድዮች ግንባታን በማስመልከት ማብራሪያ ሰጥቷል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ሰኞ ጥዋት በተካሄደው የሲኖዶሱ ስብሰባ ላይ 351 አባላት የተሳተፉ ሲሆን፥ “በመካከለኛው ምሥራቅ እየተካሄደ ባለው ጦርነት ሳቢያ በሰዎች ላይ የሚደርሰውን ስቃይ በማስታወስ ውይይት መካሄዱን የቅድስት መንበር መገናኛ ጽሕፈት ቤት ዋና ተጠሪ እና የጉባኤው የመረጃ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ዶ/ር ፓኦሎ ሩፊኒ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ አስታውቀው፥ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በዚህ አሳዛኝ ቀን በመካከለኛው ምሥራቅ ለሚገኙ ካቶሊክ ምዕመናን መልዕክት መላካቸውን በተጨማሪ ገልጸዋል።

ዶ/ር ፓውሎ ሩፊኒ በመቀጠልም በርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ጥያቄ መሠረት እሁድ ምሽት በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ታላቁ ባዚሊካ ለሰላም የቀረበ የመቁጠሪያ ጸሎት እና ሰኞ ዕለት ታስቦ የዋለውን የጸሎት እና የጾም ቀን በማስመልከት ለሲኖዶሱ ተሳታፊዎች ገለጻ ማድረጋቸውን አስታውቀዋል።

ዶ/ር ፓውሎ ሩፊኒ በመግለጫቸው በሐዋርያዊ ጽሕፈት ቤት የምጽዋት ሰብሳቢ ክፍል አስተባባሪ እና የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት የበጎ አድራጎት ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ሃላፊ ብጹዕ ካርዲናል ኮንራድ ክራየስኪ በተለይም ጋዛ ውስጥ የሚገኝ እና ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለአካባቢው ሕዝብ ያላቸውን ቅርበት ለመግለጽ በየቀኑ የሚያገኟቸውን ብቸኛው ካቶሊካዊ ቁምስና መሪ ካኅን አባ ገብርኤል ሮማኔሊን ለመርዳት ከሰዓት በኋላ የገንዘብ ማሰባሰብያ ጥረት ማድረጋቸውን ገልጸዋል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እሑድ መስከረም 26/2017 ዓ. ም. ይፋ ካደረጓቸው ሃያ አንድ አዳዲስ ካርዲናሎች መካከል 9ኙ በዚህ የገንዘብ ማሰባሰብያ ተነሳሽነት መሳተፋቸውን ዶ/ር ፓውሎ ሩፊኒ ገልጸዋል።

የሲኖዶሱ ጉባኤ ተግባር
የብጹዓን ጳጳሳት ጠቅላላ ጉባኤ የመረጃ ኮሚሽ ዋና ጸሐፊ ሺላ ፒረስ ጉባዔው በውስጠ ደንቡ አንቀጽ 13 መሠረት የመጨረሻውን ሠነድ የሚያዘጋጅ የኮሚቴ አባላትን ለመምረጥ ቀጥሎም በልዩ ልዩ ቋንቋዎች ሪፖርቶች የሚያቀርብበት ዕለት ማክሰኞ መስከረም 28/2017 ዓ. ም. አድርጎ ቀጠሮ መያዙን አስታውቀዋል።

በመጀመሪያው ሳምንት የተዘጋጀውን ሞዴል በመከተል የሲኖዶስ አባላት ለውይይት በሚቀርቡ አጀንዳዎች ላይ ድምጽ በመስጠት ይፋዊ ውይይት እንደሚያደርግ ገልጸዋል። የመጀመሪያዎቹ ሁለት መድረኮች በሥነ መለኮት ዙሪያ፥ የእግዚአብሔር ሕዝብ የተልዕኮው ርዕሠ ጉዳይ” እና “ጳጳስ በሲኖዶሳዊት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለው ሚና እና ሥልጣን” በሚሉ ርዕሠ ጉዳዮች ላይ ረቡዕ መስከረም 29/2017 ዓ. ም. ከሰዓት በኋላ ውይይት ለማካሄድ ቀጠሮ መያዙን የኮሚሽኑ ዋና ጸሐፊ ሺላ ፒረስ ተናግረዋል።

በእስያ አኅጉር የተካሄደው ሲኖዶሳዊ ጉዞ
ቤተ ክርስቲያን በተለያዩ ባህሎች እና ሃይማኖቶች መካከል ግንኙነት የምትፈጥር እና ራሷም ድልድይ መሆን ይኖርባታል ያሉት በሕንድ የቦምቤይ ከተማ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ኦስቫልድ ግራሲያስ፥ ይህ ማለት ለተለያዩ ባህሎች እና ሃይማኖቶች ትኩረት በመስጠት ውይይት እና ሲኖዶሳዊነትን ማጎልበት እንደሆነ አረጋግጠዋል።

ብፁዕ ካርዲናል ኦስቫልድ ግራሲያስ፥ የቅዱስ ሲኖዶስ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት አባል እና የካርዲናሎች ጉባኤ አባል በማድረግ ር ዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ መንበር ሹመት መጀመሪያ ላይ ቤተ ክርስቲያኒቱን ለማስተዳደር እንዲረዳቸው ያቋቋሙት የሥራ ቡድን አባል ናቸው።

ብፁዕ ካርዲናል ኦስቫልድ ግራሲያስ ሰኞ መስከረም 27/2017 ዓ. ም. በተደረገው ገለጻ፥ በሲኖዶሳዊነት ለመራመድ በባሕሎች መካከል ግንኙነት ሊኖር እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል። ከሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ጀምሮ ሌሎችን ባሕሎችን መቀበል እና እርስ በርስ መከባበር የሚለው በሰፊው ትኩረት የተሰጡባቸው ጽንሰ-ሐሳቦች መሆናቸውንም አክለዋል።

ብፁዕ ካርዲናል ግራሲያስ የእስያ አኅጉር የሲኖዶሳዊነት ጉዞን በምሳሌነት ተጠቅመው በሰጡት አስተያየት፥ ቅዱስ ሲኖዶሱ በሐዋርያዊ አገልግሎት አሠራር ላይ ተሃድሶ ማድረግ እንደሚገባ አሁን ውይይት እየተደረገባቸው ያሉት ርዕሠ ጉዳዮች አኅጉራቸው እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ2022 የተወያዩባቸው ርዕሦች እንደ ነበሩ ተናግረዋል።

ሁለት ቁልፍ ነጥቦች አብረው እየሠሩ እና እየተጓዙ እንደሚገኙ የገለጹት ብፁዕ ካርዲናል ግራሲያስ፥ የተለያዩ ባሕሎች ባሉባቸው አገሮች ውስጥ የእግዚአብሔርን መንግሥት መገንባት አስፈላጊ መሆኑን አስረድተው፥ ነገር ግን ሰዎች ሐይማኖታቸው እንዲቀይሩ ማድረግ ትክክል እንዳልሆነ እና ለልዩነቶች ዋጋ መስጠት እንደሚገባ አሳስበዋክል። እነዚህን የመሳሰሉ አስተሳሰቦችን ወይም ጽንሰ-ሐሳቦችን ለማስወገድ ሲኖዶሳዊ አቀራረብ አስፈላጊ ነው ሲሉ አስረድተዋል።

ብፁዕ ካርዲናል ኦስቫልድ ግራሲያስ፥ ለሰላም በተደረገ የጸሎት እና የጾም ዕለት

ተጨማሪ ወንድማማችነት
እስያ ውስጥ የሃይማኖቶች እርስ በርስ መከባበር፣ የምዕመናን መንፈሳዊ እንቅስቃሴዎች እና የእያንዳንዱን ምዕመን የጥምቀት ምስጢር በተመለከተ እንደ ጎርጎሮሳውያኑ እስከ 2023 ድረስ ሁለት መቶ ጳጳሳትን ያሳተፉ ውይይቶች መካሄዳቸውን እና ዛሬም እየተካሄዱ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

ብፁዕ ካርዲናል ግራሲያስ በማከልም ከሌሎች እምነቶች ጋር የሚኖር ግንኙነት እና ትብብር ወሳኝ ነው ሲሉ ገልጸው፥ ቤተ ክርስቲያን ከእንግዲህ እነዚህን የእምነት ተቋማት “ሌሎች ሃይማኖቶች” ልትላቸው እንደማትችል ነገር ግን “አጎራባች ሃይማኖቶች” እንደምትላቸው አስረድተዋል።

በእስያ የሚገኙ ካቶሊክ ብጹዓን ጳጳሳትም የዲጂታል ዓለም አስፈላጊነት ማመናቸውን እና ሲኖዶሱም በእነርሱ ብርታት ሊቀጥል እንደቻለ መመልከታቸውን ገልጸው፥ ነገሮች እንደሚሻሻሉ እርግጠኛ እንደሆነ እና በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የበለጠ ወንድማማችነት እና ፍቅር እንደሚኖር ያላቸውን እምነት ብፁዕ ካርዲናል ግራሲያስ ተናግረዋል።

አንድ ቤተሰብ ነን!
በጋዜጣዊ ገለፃው ወቅት የአውሮፓ ካቶሊክ ብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤ ሊቀ ጳጳስ እና የቪልኒየስ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ጊንታራስ ግሩሻስ ሰኞ መስከረም 27/2017 ዓ. ም. ጠዋት በተካሄደው ሲኖዶሳዊ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር ለዓለም ሰላም የተደረገውን የጸሎት እና የጾም ቀን አባከበር ላይ ትኩረት በመስጠት፥ እንደ መካከለኛው ምስራቅ እና ዩክሬን ባሉ አገራት ውስጥ በጦርነት ምክንያት ከሚሰቃዩት ሕዝቦች ጋር ያላቸውን አጋርነት ገልጸዋል።

“ሁላችንም ስለ ሰላም እና ስለ አንድነት የምንጸልይ አንድ ቤተሰብ ነን" የሚለውን ተሞክሮ ያዳበሩት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ጊንታራስ፥ በአብያተ ክርስቲያናት መካከል ያለውን ግንኙነት ማጠናከር እንደሚያስፈልግ አፅንዖት ሰጥተው፥ “የጋራ ውይይት ማድረግ ተልእኳችን ነው” ሲሉ ተናግረዋል።

ሊቀ ጳጳስ አቡነ ጊንታራስ ግሩሻስ ለሰላም ጸሎት እንዲደረግ ሲያሳስቡ

እየጨመረ የመጣ መደማመጥ
እርስ በርስ መደማመጥ በሲኖዶሱ ጉባኤ መካከል እያደገ የመጣ ጥበብ መሆኑን የታዘቡት የዓለም አቀፍ የገዳማውያት የበላይ ሃላፊዎች ኅብረት (ዩአይኤስጂ) ፕሬዝዳንት እህት ሜሪ ቴሬዝ ባሮን፥ እርስ በርስ የመደማመጥ ችሎታ እየተሻሻለ እንደሚሄድ ያላቸውን እምነት ገልጸው፥ መደማመጥ የሌሎችን እምነት የበለጠ ለመረዳት እንደሚያስችል እና ከተገለሉት ጋርም እንደሚያቀራርብ አስረድተዋል።

የኅብረቱ ፕሬዝዳንት እህት ሜሪ ቴሬዝ በበኩላቸው እንደ ሲኖዶሳዊ ቀስቃሽነት የሚያገለግል ጽ/ቤት ማቋቋማቸውን፣ በባሕሎች መካከል የተደራጁ ቡድኖች መደማመጥን እና የእርስ በርስ ግንኙነትን በማስቀደም የተሻሉ ግንኙነቶችን ለመገንባት ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ እንደሚገአን ተናግረዋል። ከሁሉም በላይ ዓላማው በማኅበረሰቡ የተገፉትን መርዳት እንደ ሆነ ገልጸው በተለይም በሶርያ፣ በሊባኖስ፣ በሩሲያ፣ በዩክሬን፣ በቬትናም፣ በምያንማር እና በኢንዶኔዥያ ሲኖዶሳዊነትን እንዴት መቀጠል ይቻላል? በሚለው ላይ ማተኮሩን አስረድተዋል።

ዛሬ ሴቶች በቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ ምን ቦታ ሊኖራቸው እንደሚችል የተጠየቁት እህት ሜሪ ቴሬዝ፥ “ብዙ አማራጮች እና የአመራር ዕድሎች በኖራቸውን ተናግረው፥ ይሁን እንጂ መመርመር እና መገምገም አለባቸው” ሲሉ መልሰዋል።

በተግባር እንደሚለይ ገልጻለች ምክንያቱም በአንዳንድ አገሮች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሴቶች መሪዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ እና በሌሎች አካባቢዎች የተለየ ቢሆንም ትኩረቱ በቤተ ክርስቲያን የተሾሙ በሚለው ላይ አለመሆኑን ተናግረዋል። ለክህነት አገልግሎት እንደተጠሩ የሚሰማቸው ሴቶች መኖራቸው እውነት ቢሆንም፣ ይህም እንደ መንፈስ ቅዱስ የአገልግሎት ጥሪ መሠረት ሰፋ ያሉ ጉዳዮችን እንደሚዳሥ እና ይህ የሲኖዶሱ ርዕሠ ጉዳይ አለመሆኑን አስረድተዋል።

ብፁዕ ካርዲናል ግራሲያስ ሴቶች በቤተ ክርስቲያን የትኩረት ማዕከል መሆናቸውን ጠቁመው፥ ባለፉት ሦስት የካርዲናሎች ጉባኤ ላይ የሴቶች ሚና በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከሥነ መለኮት እና ከሐዋርያዊ አገልግሎት አንፃር ምን መምሰል እንዳለበት ውይይት መደረጉን ተናግረዋል።

በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚቀርቡ መንፈሳዊ አገልግሎቶችን በተመለከተ የመልካም ምግባር ስጦታዎችን እና ጥሪዎችን በማስመልከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ግሩሻስ እንደተናገሩት፥ የምእመናን እና የቤተሰብ ሚና በተለያዩ ቦታዎች ሊገለጽ እንደሚችል ጠቁመው፥ በመሆኑም ወንዶች እና ሴቶች በቤተ ክርስቲያን ያላቸው ሚና ተገቢ ዋጋ ሊሰጠው እንደሚገባ የቪልኒየስ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ጊንታራስ ግሩሻስ አሳስበዋል።

የብጹዓን ጳጳሳት ሹመትን በማስመልከት ከአጥኚው ቡድን ለቀረቡት ጥያቄዎች ብፁዕ ካርዲናል ግራሲያስ መልስ ሲሰጡ፥ በብጹ ዓን ጳጳሳት ሚና ላይ ያተኮሩ ሁለት ቡድኖች መኖራቸውን ገልጸው፥ አንደኛው በጳጳስ ሚና እና ሁለተኛው በሹመቱ ሂደት ላይ ያተኮረ መሆኑን አስረድተዋል።

ሰኞ መስከረም 27/2017 ዓ. ም. የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ መግለጫ
08 October 2024, 17:10