ከመስከረም 22 -ጥቅምት 17/2017 ዓ.ም የተካሄደው የ16ኛው መደበኛ ጠቅላላ ሲኖዶስ 2ኛው ጉባኤ በቫቲካን ከመስከረም 22 -ጥቅምት 17/2017 ዓ.ም የተካሄደው የ16ኛው መደበኛ ጠቅላላ ሲኖዶስ 2ኛው ጉባኤ በቫቲካን   (VATICAN MEDIA Divisione Foto)

የሲኖዶሱ የመጨረሻ ሰነድ ከቤተክርስቲያን አስተምህሮ እኩል ዋጋ አለው ተባለ!

ከመስከረም 22 እስከ ጥቅምት 17/2017 ዓ.ም የተካሄደው የ16ኛው መደበኛ ጠቅላላ ሲኖዶስ 2ኛው ጉባኤ ማብቂያ ላይ የመጨረሻ ሰነድ ከታተመ በኋላ የተካሄደው ጋዜጣዊ መግለጫ በዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ሲሆን ምእመናን እና ሴቶች ዝቅተኛ ተዋረድ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለመፍጠር የሚያደርጉትን አስተዋጽኦ በመሳሰሉት ዋና ዋና ነጥቦች ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

በጋዜጣዊ መግለጫው፣ በጥቅምት 17/2017 ዓ.ም ቅዳሜ አመሻሽ ላይ፣ በሲኖዶሱ የመጨረሻ ሰነድ ላይ ለመወያየት በተካሄደው የሲኖዶስ መሪዎች፣ ቤተ ክርስቲያኒቱን የምንረዳበትን ቋንቋ እና አመለካከት መቀየር እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።

የ“ዓለማቀፋዊ ቤተክርስቲያን”ን ራዕይ እንደ ዓለማቀፋዊ ኮርፖሬሽን አድርገን መመልከት በመተው፣ ቤተክርስቲያኗ በምትኩ ምእመናን እና ሴቶች የምያበረክቱት የሚገኘውንና እያደገ የሚሄደውን አስተዋጽዖ እንደ “የአብያተ ክርስቲያናት ማኅበር” መታየት አለበት። ቀጣይነት ያለው የሴቶች የድቁና አገልግሎት ጥያቄም ለውይይት ክፍት መሆኑን መግለጫው አክሎ ገልጿል።

የጋዜጣዊ መግለጫው፣ ዋና ዋና የሲኖዶስ መሪዎችን ያካተተ ሲሆን ከእነዚህም መካከል በቫቲካን የቅድስት መንበር የኮሙዩኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት ዶክተር ፓኦሎ ሩፊኒ፣ ብፁዕ ካርዲናል ማሪዮ ግሬች እና ካርዲናል ዣን ክላውድ ሆሌሪች ይገኙበታል።

የሲኖዶሱ ሰነድ ከቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ እኩል ዋጋ አለው

የመጀመሪያው ጥያቄ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የድህረ ሲኖዶስ ማሳሰቢያ ሰነድ ላለመስጠት መወሰናቸው እና ይህ ለወደፊት የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሰነዶች ምን ማለት እንደሆነ ምርጫን የሚመለክት ጥያቄ ነበር።

የሥነ መለኮት ትምህርት ምሁር የሆኑት ዬኔታ ሪካርዶ ባቶቺዮ የጳጳሱ አቋም በላቲን ቋንቋ "ኤፒስኮፓሊስ ኮሙኒዮ" (የጳጳሳት ሕብረት) ጋር የሚስማማ መሆኑን ገልጿል፣ ይህም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በግልጽ ካጸደቁት፣ ሰነዱ የቤተክርስቲያን አስተምህሮ አካል ይሆናል ማለት ነው - እንደ አስገዳጅ ደንብ ሳይሆን እንደ የመመሪያ መርሆች ስብስብ ይሆናል ማለት ነው ሲሉ መልሰዋል።

ብፁዕ ካርዲናል ማሪዮ ግሬች አክለውም ሲኖዶሱ ራሱ ኃያል፣ ውብ የውይይት እና የኅብረት ልምድ ነበር ብለዋል።

ብፁዕ ካርዲናል ዣን ክላውድ ሆሌሪች በበኩላቸው በዚህ ዓመት፣ የሲኖዶሳዊው ዘዴ ሥር እየሰደደ ሲመጣ፣ የተለያዩ አመለካከቶች ግልጽ በሆነ መንገድ ቀርበው እውነተኛ ሲኖዶሳዊነትን ወደ ሕይወት ያመጣሉ ብለዋል።

ቤተ ክርስቲያን እንደ ኅብረት እንጂ እንደ ኮርፖሬሽን አይደለችም።

የመጨረሻው ሰነድ ቤተክርስቲያኗን እንደ “ኮርፖሬሽን” ቅርንጫፎች ያሏት ሳይሆን እንደ የአብያተ ክርስቲያናት ኅብረት በመመልከት አዲስ አቀራረብን ይጠይቃል። “ዓለማቀፋዊ ቤተ ክርስቲያን” የሚለው ቃል በአዲስ መልክ የተቀየሰው በልዩነት ውስጥ ያለውን አንድነት ለማጉላት ነው፣ የአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት እንደ የበታች ደረጃዎች ሳይሆኑ እንደ አንድ የክርስቶስ አካል ልዩ የእምነት መግለጫዎች መመልከት እንደ ሚገባ ተገልጿል።

የስነ-መለኮት ምሁር የሆኑት የእኔታ ባቶቺዮ እንዳብራሩት ከሆነ የሰነዱ "መደበኛ ያልሆነ" ባህሪ ተጽእኖውን አይቀንስም ነገር ግን በብዙ ቁጥር ወደሚታወቅ የአንድነት ጉዞ መንገድ ያመላክታል፣ ይህም የቤተክርስቲያንን አመጣጥ የሚያንፀባርቅ ነው። ይህ ራዕይ ቤተክርስቲያንን ወደ ለውጥ ይጠራል—በሞራል ብቻ ሳይሆን በጥልቀት ግንኙነታዊ ትሥሥር በመፍጠር የበለጠ የተለያየ የቤተክርስቲያን ግንኙነቶችን የሚያበረታታ ነው ሲሉ አክለው ገልጸዋል።

ሥር የሰደደ እና መንፈሳዊ ንግደት

በስደት ወቅት የምስራቃዊ የአምልኮ ትውፊቶችን ለማክበር ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ሲሰጡ፣ የእኔታ አባ ጂያኮሞ ኮስታ የቤተክርስቲያኗን ተልእኮ "ሥር መሰረት መንፈሳዊ ንግደት" መሆኑን ጠቁመዋል። ወደ ማግለል ሳያፈገፍጉ እነዚህን የበለጸጉ ባህሎች ማክበር አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥቷል። የምስራቅ አብያተ ክርስቲያናት ንዋየ ቅድሳታቸውን እንደገና እንዲያገኙ ማድረግ ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶታል ብለዋል።

 ሲስተር ወይም እህት ማሪያ ዴ ሎስ ዶሎሬስ ፓሌንሺያ ጎሜዝ በሜክሲኮ የሚገኙትን ልዩ ልዩ ጉባኤዎችን በምያገለግሉበት ወቅት ያጋጠሟቸውን ተሞክሮ ሲናገሩ ከ30 የሚበልጡ ብሔረሰቦች የተዋሃዱበት ጥምረት እምነትን እንደሚያጎለብት ተናግረዋል።

አባ ኮስታ በተጨማሪም የላቲን ቤተ ክርስቲያን የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ጉልህ ክፍል ብትሆንም ሙሉ በሙሉ አካታች እንዳልሆነች አስረድተዋል። ይህ ልዩነት እምነት በባህሎች ውስጥ ሥር የሰደዱባቸውን የተለያዩ መንገዶች ስለሚያሳይ ጥበቃን የሚፈልግ ሀብት ነው ብለዋል ። “ቤተክርስቲያኗ የተለያየ አስተዳደግ ያላቸው ሰዎች እንደ ወንድም እና እህቶች፣ የአንድ አባት ልጆች አንድነት የሚያገኙበት ማዕከል ሆና ማገልገል አለባት” ሲሉ አባ ኮስታ ተናግሯል።

ለምዕመናን እና ለተሾሙ አገልጋዮች የተዋሃዱ ሚናዎች

የመጨረሻውን ሰነድ አንቀጽ 76 በመጥቀስ፣ ጋዜጣዊ መግለጫው በምዕመናን እና በተሾሙ ወይም በተቀቡ  ሰዎች የሚሰጡ አገልግሎቶች በቤተክርስቲያኗ ውስጥ እንደ ተጨማሪ አገልግሎት እንጂ በተቃዋሚነት መታየት እንደሌለባቸው ጋዜጣዊ መግለጫው አመልክቷል።

ምእመናን አገልጋዮች የካህናቱን አገልግሎት የምያሟሉ "በጎደለ ሙላ" ተደርገው መቆጠር የለባቸውም፣ ነገር ግን ለጋራ ተልእኮ አስተዋፅዖ እንደ ምያበረክቱ በማወቅ በተለይም ቤተክርስቲያኒቱ ዓለማዊ እየሆነ በመጣው የማኅበረሰብ ክፍል ውስጥ የስልጣን ተዋረድን ከመጠበቅ ይልቅ ማሕበራዊ የሆኑ ሥርዓቶችን እና መዋቅሮችን መጠቀም ያስፈልጋል።

ብፁዕ ካርዲናል ሆለሪች እንዳሉት ሥርዓተ አምልኮ አዲስ ልምዶችን ለመላመድ ክፍት ሆኖ እንደሚቆይ፣ ይህም በተገቢው ጊዜ የበለጠ ተሳትፎ እንዲኖራቸው እንደሚያስችል ገልጸዋል። ለምሳሌ በሀገረ ስብከቱ ውስጥ ሰፊ የጉባኤ ተሳትፎን የሚያበረታታ የብራዚል የሥርዓተ አምልኮ መጽሐፍን በመጠቀም በፖርቱጋልኛ ቋንቋ የሚከናወነውን ሥርዓተ አምልኮን በዋቢነት ጠቅሰዋል። የእሁድ እለት ቅዱስ ቁርባን፣ ወንጌልን ያማከለ ማህበረሰቦችን ለመገንባት የትኩረት ነጥብ ሆኖ ያገለግላል ሲሉ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

የሴቶች የድቁና ማዕረግ ጥያቄ አሁንም ክፍት ነው

የቀረው ክፍት ጉዳይ የሴት የድቁና ማዕረግ ጥያቄ ነው። የእኔታ አባ ባትቶቺዮ እንዳብራሩት ከሆነ በብዙ ሴሚናሮች ውስጥ ሴቶች በአገልጋዮች ምስረታ ውስጥ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወቱ፣ ምእመናን ቤተሰቦች እና ሴቶች በስልጠና ጥረቶች ንቁ ተሳትፎ ያደርጋሉ ሲሉ ተናግረዋል።

ብፁዕ ካርዲናል ግሬች፣ ምእመናን ባልና ሚስት ለምስረታ መርሃ ግብሩ አስተዋፅዖ ካደረጉበት የአውሮፓ ሴሚናር የቅርብ ጊዜ ልምድ ሲናገሩ፣ ይህ አሠራር በብዙ የላቲን አሜሪካ አህጉረ ስብከት ውስጥ አለ ሲሉ ገልጸዋል።

ብፁዕ ካርዲናል ሆለሪች ይህ ጉዳይ “በጣም ስስ ጉዳይ” መሆኑን አምነው፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ጉዳዩን አላረጋገጡም ወይም ውድቅ እንዳላደረጉትም፣ ለበለጠ ግንዛቤ ክፍት ጥያቄ አድርገውታል ብለዋል።

"የጥናት ቡድኖች" የወደፊት ዕጣ ፈንታ

የሲኖዶሱ አሥሩ “የጥናት ቡድኖች” ሥራቸውን እስከ ሰኔ ወር ድረስ እንዲያጠናቅቁ የጊዜ ገደብ ተይዟል።

አባ ኮስታ ውጤቶቹ ከችኮላ ውሳኔዎች ይልቅ ለማሰላሰል ተጨማሪ ጊዜ በመስጠት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ባሳሰቡት መሰረት በሲኖዶሱ ውስጥ ተወክለው ለነበሩት ኤጲስ ቆጶሳት ጉባኤዎች እንዲመለሱ ይጠበቃል ብለዋል።

27 October 2024, 11:43