ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ   (Vatican Media)

ጳጳስ ክርዚዝቶፍ ጆዜፍ ኑዛዜ ወደ ነፍስ የምያስገባ ቅዱስ በር ነው ማለታቸው ተገለጸ!

የምስጢረ ንስሐን ጉዳዮች የሚመለከተው እና ለዚህ ምስጢር የሚረዳውን ሐዋርያዊ እንክብካቤዎች በበላይነት የሚቆጣጠረው የቅድስት መንበር ጽሕፈት ቤት ዋና እንደራሴ የሆኑት ጳጳስ ክርዚዝቶፍ ጆዜፍ ኒኪኤል፣ በኢዮቤልዩ የቀረበው ጥሪ የመንፈሳዊ እድሳታት፣ መለወጥ እና እርቅ ጊዜን ያንጸባርቃል በማለት የተናገሩ ሲሆን የተከፈቱት ቅዱሳት በሮች አንድ በአንድ በክርስቶስ የተከፈተው የድኅነት ደጅ ምልክት መሆናቸውን ጠቁወዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

 ጳጳስ ክርዚዝቶፍ ጆዜፍ ኒኪኤል “መደሰት የሰውን የፍትህ ወሰን የሚያልፍ እና የሚቀይር ተጨባጭ የእግዚአብሔር ምህረት መገለጫ ነው” ሲሉ ያስረዳሉ።

ለቫቲካን መገናኛ ብዙኃን የሰጡት የምስጢረ ንስሐን ጉዳዮች የሚመለከተው እና ለዚህ ምስጢር የሚረዳውን ሐዋርያዊ እንክብካቤዎች በበላይነት የሚቆጣጠረው የቅድስት መንበር ጽሕፈት ቤት ዋና እንደራሴ የሆኑት ጳጳስ ክርዚዝቶፍ ጆዜፍ ኒኪኤል፣ የቅዱሳንን ሕይወት ማጥናት ጠቃሚነቱ ከፈተኛ መሆኑን እንደምንረዳ ጠቁመው “አርአያነታቸውን ስንመለከት የእግዚአብሔር ጸጋ ትልቁን ድክመቶችን እንኳን እንደሚለውጥ እናያለን። ለኃጢአታችን ይቅርታ ተስፋ እናደርጋለን፣ እናም የቅድስናውን መንገድ በመከተል ድጋፍ እናደርጋለን" ሲሉ ተናግረዋል፥ “በፍፁም ነፃነት መታረም ይቻል ዘንድ ልብን ከኃጢአት ሸክም ነፃ ያወጣል” ብሏል።

የኃጢአያት ካሳን ለማግኘት የሚረዱን ሁኔታዎች

እ.ኤ.አ. በ2025 ዓ.ም በኢዮቤልዩ ዓመት የምልአተ የኃጢአያት ካሳ አገልግሎትን ለመቀበል ምእመናን በቤተ ክርስቲያን የተቀመጡ ልዩ ሁኔታዎችን ማክበር አለባቸው፡ ምስጢረ ንስሐን፣ የቅዱስ ቁርባን ምስጢር ማዘውተር፣ እምነትን በይፋ መግለጽ፣  ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የጸሎት ሐሳብ ጋር በመተባበር መጸልይ፣ የምሕረት ተግባራትን መፈጸም፣ ወደ ቅዱሳት ሥፍራዎች መንፈሳዊ ንግደት ማድረግ፣ ከኃጢአት ሙሉ በሙሉ የመገለል ውስጣዊ ዝንባሌን ማሳደግ፣ ሥጋዊ ኃጢአትምን ጭምር ለማስወገድ መሞከር" ናቸው ሲሉ ገልጸዋል።

ምእመናን ለክርስቶስ

የምስጢረ ንስሐን ጉዳዮች የሚመለከተው እና ለዚህ ምስጢር የሚረዳውን ሐዋርያዊ እንክብካቤዎች በበላይነት የሚቆጣጠረው የቅድስት መንበር ጽሕፈት ቤት ዋና እንደራሴ የሆኑት ጳጳስ ክርዚዝቶፍ ጆዜፍ ኒኪኤል፣  እ.አ.አ 2025ን መደበኛ የኢዮቤልዩ ዓመት የሚያውጀውን ሰነድ በመጥቀስ መንፈሳዊ ንግደት የማንኛውም የኢዮቤልዩ ክስተት ዋና መሰረት ነው ያሉ ሲሆን  "በመሠረቱ መንፈሳዊ ንግደት የክርስቲያኖች የግል ጉዞ በቤዛዊ ፈለግ ነው። የሰውን ሕይወት ትርጉም ይሸፍናል፤ ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ እንዳመለከቱት፣ የክርስትና ሕይወት በሙሉ ሕይወቱን ወደ እግዚአብሔር ቤት የምያደርግበት እንደ ታላቅ ጉዞ ነው። መንፈሳዊ ጉዞን ለማድረግ መነሳት ማለት ካለንበት ሥፍራ ተነስተን በመጓዝ ቦታ መቀየር ማለት ሳይሆን፣ ነገር ግን ውስጣዊ ለውጥን ማምጣት ማለት ነው፣ ራስን መለወጥ ማለት ነው፣ ቦታን ከመለወጥ ይልቅ ራስን መለወጥ ነው፣  (...) በዚህ ረገድ የኢዮቤልዩ ዓመት ጉዞ የሚጀምረው ከጉዞው በፊት ነው፣ በሌላ አነጋገር፣ የመጀመሪያው እርምጃ ከመውሰዱ በፊት በምስጢረ ንስሐ መጀመር ይኖርበታል፣ ይህም ለክርስቶስ የተደረገ ውሳኔ ነው" ሲሉ ተናግረዋል።

ምስጢረ ንስሐ የመንፈሳዊ ንግደት አካል የግድ መሆን ይኖርበታል

የምስጢረ ንስሐን ጉዳዮች የሚመለከተው እና ለዚህ ምስጢር የሚረዳውን ሐዋርያዊ እንክብካቤዎች በበላይነት የሚቆጣጠረው የቅድስት መንበር ጽሕፈት ቤት ዋና እንደራሴ የሆኑት ጳጳስ ክርዚዝቶፍ ጆዜፍ ኒኪኤል፣ በተጨማሪም እንደገለጹት ከሆነ ምስጢረ ንስሐ ገብቶ መናዘዝ እንደ መለወጥ ልምድ የሚታይ የመንፈሳዊ ንግደት ጉዞ አስፈላጊ አካል መሆኑን አመልክተዋል።

በኑዛዜ ወቅት "ኃጢያታችንን ተገንዝበን ለእግዚአብሔር እናቀርባለን፣ ይቅርታውን በመጠየቅ" በማለት የተናገሩት ጳጳስ ክርዚዝቶፍ ኤጲስ በማከልም "ካህኑ መጋቢ ነው፣ ማለትም አገልጋይ፣ እና በተመሳሳይ ጊዜ አስተዋይ የእግዚአብሔር ምሕረት አስተዳዳሪ ነው። እሱ በአደራ ተሰጥቶታል። ‘ኃጢአትን ይቅር ማለት ወይም ማቆየት’ ካለው ከባድ ኃላፊነት ጋር (ዮሐ 20፡23 ተመልከት) ሲሉ ተናግረዋል።

የቅዱስ በር ትርጉም

በሮም በሚገኘው በጳጳሳዊ ባዚሊካዎች ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በሚገኙ ቅዱስ በሮች ውስጥ ማለፍ አስፈላጊ መሆኑን በመጥቀስ፣ የምስጢረ ንስሐን ጉዳዮች የሚመለከተው እና ለዚህ ምስጢር የሚረዳውን ሐዋርያዊ እንክብካቤዎች በበላይነት የሚቆጣጠረው የቅድስት መንበር ጽሕፈት ቤት ዋና እንደራሴ የሆኑት ጳጳስ ክርዚዝቶፍ ጆዜፍ ኒኪኤል፣ ወደ ነፍስ መዳን የሚወስደውና በክርስቶስ የተከፈተው በር ምልክት መሆናቸውን ያስረዳሉ።

"ሕይወትን ለመለወጥ፣ ከእግዚአብሔር እና ከጎረቤት ጋር ለመታረቅ የቀረበን ጥሪን ይወክላሉ። ስለዚህ በእነሱ ውስጥ ማለፍ ከኃጢአት ወደ ፀጋ የሚወስደውን መንገድ ያነሳሳል፣ ይህም እያንዳንዱ ክርስቲያን እንዲተገብረው የተጠራበት ምክንያት ነው። በር መክፈት አንድ መዳረሻ ብቻ ነው ያለው፣ ከእግዚአብሔር ጋር ኅብረት ያለው ሕይወት፣ ብቸኛው የመዳን መንገድ ኢየሱስን መገናኘት ነው" ሲሉ ተናግረዋል።

30 December 2024, 12:01