እስራኤላውያን በጋዛ ሰርጥ በሚገኘው የአል-ማጋዚ የስደተኞች ካምፕ ላይ ያደረሱትን ጥቃት ተከትሎ ፍልስጤማውያን በሕይወት የተረፉ ሰዎችን ፍርስራሾች ስር  እየፈለጉ እስራኤላውያን በጋዛ ሰርጥ በሚገኘው የአል-ማጋዚ የስደተኞች ካምፕ ላይ ያደረሱትን ጥቃት ተከትሎ ፍልስጤማውያን በሕይወት የተረፉ ሰዎችን ፍርስራሾች ስር እየፈለጉ  (AFP or licensors)

በጋዛ ተጨማሪ የተኩስ አቁም ጥሪዎች እየተደረጉ እንደሆነ ተነገረ

የዓለም ጤና ድርጅት ወደ ጋዛ ሰርጥ አፋጣኝ እና ያልተደናቀፈ ሰብአዊ ዕርዳታ እንዲደርስ የሚጠይቅ ውሳኔ አጽድቋል።

  አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

እሁድ ዕለት የዓለም ጤና ድርጅት ስራ አስፈፃሚ ቦርድ በእስራኤል በተያዘው የፍልስጤም ግዛት ስላለው አስከፊ ሁኔታ ለመወያየት በጄኔቫ ልዩ ስብሰባ አካሂዶ ነበር።

እንደ ድርጅቱ ገለጻ በጋዛ ውስጥ ከሚገኙት አጠቃላይ ሆስፒታሎች 14ቱ ብቻ በከፊል የሚሰሩ እንደሆነም አመላክቷል።

ባለፈው ኅዳር 30 ቀን 2016 ዓ.ም. እሁድ ዕለት የተባበሩት መንግስታት የዓለም የምግብ ፕሮግራም ምክትል ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ካርል ስካው በጋዛ ሰርጥ በቂ ምግብ አለመኖሩን እና ሰዎች ለረሃብ መጋለጣቸውን ተናግረዋል።

ይህ ሆኖ እያለ ሃማስ የእስረኛ ልውውጥ ጥያቄው እስካልተመለሰ ድረስ አንድም ታጋች ጋዛን በህይወት እንደማይለቅ ዝቷል።

ሆኖም የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ እንዳሉት በደርዘን የሚቆጠሩ የሃማስ ታጣቂዎች እጃቸውን እንደሰጡ እና ዓለም የሀማስን 'የፍጻሜውን መጀመሪያ' እያየ እንደሆነ ተናግረዋል።

የጠቅላላ ጉባኤ አስቸኳይ ስብሰባ

በሌላ ጉዳይ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ማክሰኞ ዕለት በጋዛ ጉዳይ ላይ ለመወያየት አስቸኳይ ስብሰባ እንደሚያደርግ የተገለፀ ሲሆን፥ ቀደም ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ የተኩስ አቁም ጥሪ አቅርበው እንደነበር ይታወሳል።

ከዚህ ቀደም ብሎ ኔታንያሁ ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በስልክ ባደረጉት ውይይት በጋዛ ስላለው ሰብዓዊ ሁኔታ እንደተወያዩ ተገልጿል።

እንደ የክሬምሊን መግለጫ ከሆነ ውይይቱ በፍልስጤም እና በእስራኤል ግጭት ቀጠና ውስጥ በተለይም 'በጋዛ ሰርጥ ውስጥ ስላለው አስከፊ ሰብአዊ ሁኔታ' ላይ ያተኮረ እንደሆነ ተገልጿል።
 

12 December 2023, 14:26