NIGER-COUP-ECOWAS-SANCTIONS NIGER-COUP-ECOWAS-SANCTIONS  (AFP or licensors)

በቡርኪናፋሶ 170 የሚሆኑ የተለያዩ መንደር ነዋሪዎች በአማጽያን መገደላቸው ተነገረ

በቡርኪናፋሶ 170 ሰዎች በአከባቢው በሚንቀሳቀሱ አማፂያን ተጨፍጭፈዋል ተብሏል።

  አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

በምዕራብ አፍሪካዊቷ ሃገር ቡርኪናፋሶ የካቲት 17 ቀን 2016 ዓ.ም. በሶስት መንደሮች ላይ በተፈጸመ የአማፅያን ጥቃት ሴቶች እና ህጻናትን ጨምሮ 170 የሚጠጉ ሰዎች እንደተገደሉ ተገልጿል።

አንድ አቃቤ ህግ ግድያውን በማስመልከት እንደተናገሩት፥ በኮምሲልጋ፣ ኖርዲን እና ሶሮ መንደሮች ላይ ጥቃት ያደረሱትን ሰዎች ለማግኘት እንዲረዳቸው ምስክሮች ቀርበው ቃላቸውን እንዲሰጡ ጥሪ አድርገዋል።

እስካሁን ድረስ ከጥቃቶቹ ጀርባ የትኛው ቡድን እንዳለ ለማወቅም አልተቻለም።

ይህ በእንዲህ እያለ የሃገሪቱ መንግስት ወታደራዊ አዛዦች “በከተማ ማዕከላት ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ጨምሮ” በታጣቂዎች የሚሰነዘረው አጠቃላይ ጥቃት አስጊ እየሆነ መምጣቱን አስጠንቅቀዋል።

የሀገሪቱ ጦር በ2014 ዓ.ም. ስልጣኑን ቢቆጣጠርም፥ ከሩብ በላይ የሚሆነው የቡርኪናፋሶ ግዛቶች አሁንም ድረስ በአማፂያን ቁጥጥር ስር እንደሚገኙ ይነገራል።

የካቲት 17 ቀን 2016 ዓ.ም. በያቴንጋ ግዛት ውስጥ ባሉ መንደሮች የተፈፀሙት ጥቃቶች ላይ ምርመራ እየተደረገ እንደሚገኝም ተነግሯል ።
 

04 March 2024, 15:39