በአውስትራሊያ ሰሜናዊ ግዛት የሚገኘው እና በዩኔስኮ የዓለም ቅርስ ቦታ ተብሎ የተመዘገበው የካካዱ ብሄራዊ ፓርክን የሚያሳይ ጠቋሚ ምልክት በአውስትራሊያ ሰሜናዊ ግዛት የሚገኘው እና በዩኔስኮ የዓለም ቅርስ ቦታ ተብሎ የተመዘገበው የካካዱ ብሄራዊ ፓርክን የሚያሳይ ጠቋሚ ምልክት 

የአውስትራሊያ መንግስት በሰሜኑ የሃገሪቱ ክልል የሚገኘውን የዩራኒየም ማዕድን ማምረቻ ውል እንዳይታደስ ከለከለ

የሰሜን አውስትራሊያ ክልላዊ መንግስት ጃቢሉካ ከሚባለው ዩራኒየምን ከሚያመርተው እና ከሚያከማቸው ተቋም ጋር የነበረውን የማዕድን ኪራይ ውል ለማደስ ፈቃደኛ አለመሆኑ የተነገረ ሲሆን፥ ይህንን እርምጃ በቦታው የሚገኙ ነባር ተወላጆች ቅርሶች እና መብቶች እንዲጠበቁ የሚሟገቱ አክቲቪስቶች በደስታ እንደተቀበሉት ተነግሯል።

  አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

ጃቢሉካ በአውስትራሊያ ሰሜናዊ ክልል ውስጥ በሚገኙ ነባር ህዝቦች በሆኑ የሚራር ጎሣ አባላት መሬት ላይ የተገነባ የዩራኒየም ማከማቻ እና ማበልጸጊያ ተቋም ነው።

የሰሜን አውስትራሊያ ክልል መንግስት በካካዱ ብሔራዊ ፓርክ በስተደቡብ በኩል ላይ በሚገኘው የጃቢሉካ ዩራኒየም ማምረቻ ተቋም የማዕድን ኪራይ ውል እድሳት ላለማድረግ የተደረሰው ውሳኔ በብዙዎች ዘንድ “ታሪካዊ” ተብሎም ተገልጿል።

የሃገሪቱ ሰሜናዊ ክልል ይሄንን ነሐሴ 5 ቀን 2016 ዓ.ም. ላይ የሚያበቃውን የሊዝ ውል ላለማደስ የተነሳሳው የፌደራል መንግስት ውሉን እንዳያድስ የሰጠውን ምክር ተከትሎ እንደሆነም ተነግሯል።

ጃቢሉካ እ.አ.አ. በ1991 ዓ.ም. የማዕድን የሊዝ ውል ተፈቅዶለት የነበረ ቢሆንም፥ በ1998 ዓ.ም. ሚራር ተብለው በሚታወቁት በነባር የመሬት ባለቤቶች ዘንድ ከፍተኛ ቁጣ አስነስቶ የማዕድን ቦታውን እስከማዘጋት የደረሰ ከፍተኛ ውዝግብ እና ተቃውሞ አስከትሎ ነበር።

የሚራር ጎሳ አባል በሆነው ኢቮን ማርጋሩላ የሚመራው ህብረት ከአውስትራሊያ ዙሪያ ከተውጣጡ ቡድኖችን እና የመብት ተሟጋቾች ጋር አስደናቂ ጥምረት በመፍጠር ከፍተኛ እንቅስቃሴ ሲያደርግ እንደነበረ የተገለጸ ሲሆን፥ የሃገሪቱ መንግስት በአሁኑ ወቅት የጃቢሉካ የዩራኒየም ማከማቻ ቦታን ወደ ካካዱ ብሔራዊ ፓርክ የማካተት ሂደቱን ተግባራዊ ለማድረግ የተለያዩ ሥራዎችን እንደጀመረም ተነግሯል።

የማዕድን ሀብት እና የሰሜን አውስትራሊያ ሚኒስትር የሆኑት ማዴሊን ኪንግ ውሳኔው አስርት ዓመታትን ያስቆጠረው ውዝግብ እንዲያበቃ የሚያደርግ መሆኑን ጠቁመው፥ “በጃቢሉካ ማዕድን ኪራይ ውል ውስጥ የሚሳተፉ ሁሉንም ወሳኝ ባለድርሻ አካላት አግኝተው ማነጋገራቸውን” በመግለጽ፥ “ይህ ውሳኔ ለሁሉም ወገኖች ግልጽነት እና እርግጠኝነት ይሰጣል” ሲሉ ተናግረዋል።

እ.አ.አ. በ 1981 በዩኔስኮ የዓለም ቅርስ ስፍራ ተብሎ የተመዘገበው የካካዱ ብሄራዊ ፓርክ፥ ለም መሬቶችን እና ወንዞችን የሚያካትት፣ የተለያዩ የእምነበረድ ድንጋዮች የሚገኙበት እንዲሁም ከ2,000 በላይ የሆኑ የእፅዋት ዝርያዎች እና የዱር አራዊቶች መኖሪያ ሥፍራ ሲሆን፥ በዓለም ላይ ካሉት የዩራኒየም ክምችቶች ከሚገኙበት ውስጥ አንዱ እንደሆነም መረጃዎች ያሳያሉ።

ይህ ሥፍራ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘው እ.አ.አ. በ 1970 ዎቹ መጀመሪያ ላይ ሲሆን፥ ለረጅም ዓመታት የሚራር ህዝብ ተብለው በሚታወቁት ነባር የአከባቢው ነዋሪዎች እና በትላልቅ የማዕድን አምራች ኩባንያዎች መካከል ውስብስብ የሆነ አለመግባባት ከተፈጠረ በኋላ፣ በ 2017 ዓ.ም. ዕድሜያቸው አስር ሺዎች ዓመታትን ያስቆጠሩ የአገሬው ተወላጆች መኖሪያ የነበሩ ቅሪቶች በአካባቢው ተገኝቷል።

የሥነ ምድር አጥኚዎች እንዳረጋገጡት አከባቢው ነባር ህዝቦች መጥረቢያዎችን እና የስለት መሳሪያዎች የሚሰሩበት ቦታ እንደነበረም ተገልጿል።

በሲድኒ በተካሄደው ጉባኤ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኔዝ ጉዳዩን አስመልክተው እንደተናገሩት “ይህ የነባር ህዝቦች እና የቶረስ ስትሬት ደሴት ህዝቦች “ከመሬቱ ጋር ለነበራቸው አስደናቂ እና ዘላቂ ግንኙነት ተጨማሪ ማረጋገጫ” መሆኑን በማንሳት አጽንኦት ሰጥተው ገልጸዋል።

ሚኒስትሩ በማከልም “የሚራር ህዝቦች ከ60,000 ለሚበልጡ ዓመታት ምድራቸውን ይወዱ እና ይንከባከቡ ነበር” ካሉ በኋላ፥ “ይህ ውብ የአውስትራሊያ ክፍል በዓለም ላይ ካሉት እጅግ ጥንታዊ የሆኑ የአለት ላይ ጥበባት መገኛ ሥፍራ ናት” ብለዋል።

በ 2012 ዓ.ም. አንድ የማዕድን ኩባንያ 46,000 ዓመታት ዕድሜ ያስቆጠረውን ከድንጋይ የተሰሩ የጥንት ህዝቦች ጥንታዊ መኖሪያን በማፍረሱ ከፍተኛ ውዝግብን በማስነሳት የተቃውሞ ማዕበልን ካስከተለ በኋላ፥ የነባር ተወላጆችን ቦታዎች ለመጠበቅ የሚወጡ ዕቅዶች መበረታታት ጀምረዋል።

በጃቢሉካ ላይ የተላለፈው ውሳኔ በምእራብ አውስትራሊያ በኩል አድርገው የሚያልፉ ጀልባዎች እገዳ እና ‘አየርስ ሮክ’ ተብለው የሚታወቁትን ሞኖሊት ኡሉሩ የተሰኙትን ትላልቅ የእምነበረድ ድንጋዮችን ማውጣት መከልከሉን ተከትሎ መሆኑም ተገልጿል።

እነዚህ አከባቢዎች ለአውስትራሊያ ነባር የአከባቢው ህዝቦች ዘንድ አለቶች ብቻ ያሉበት ሥፍራ ሳይሆን፥ “የተቀደሱ” ሥፍራ ተደርገው የሚታዩ፣ እስትንፋስ ያላቸው መልክዓ ምድሮች ናቸው።
 

05 August 2024, 15:43