በጎ ፈቃደኞች በአቴንስ ዳርቻ ላይ የተከሰተውን እሳት ለማጥፋት እየታገሉ የሚገኙትን የእሳት አደጋ መከላከያ ሰራተኞችን ሲረዱ በጎ ፈቃደኞች በአቴንስ ዳርቻ ላይ የተከሰተውን እሳት ለማጥፋት እየታገሉ የሚገኙትን የእሳት አደጋ መከላከያ ሰራተኞችን ሲረዱ  (AFP or licensors)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በግሪክ በተከሰተው የሰደድ እሳት ለተጎዱ ሰዎች መጸለያቸው ተነገረ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ ሐሙስ ዕለት ባቀርቡት የመልአከ እግዚያብሄር ጸሎት ወቅት በግሪክ ሰደድ እሳት የተጎዱትን በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን በማስታወስ፥ በአደጋው ለተጎዱት ሰዎች ያላቸውን ቅርበት እና ጸሎት አረጋግጠዋል።

  አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ በግሪክ የተነሳው “አውዳሚ እሳት” እንዳሳሰባቸው የገለጹ ሲሆን፥ ቅዱስ አባታችን “በአሁኑ ጊዜ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል፣ ብዙ ቤተሰቦች ቤት አልባ ሆነዋል፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ለአሰቃቂ ችግር ተጋልጠዋል፣ ከሰብዓዊ ጉዳት በተጨማሪ በአካባቢ ላይ ከባድ አደጋ እየተፈጠረ ነው” ብለዋል።

ለአደጋው ሰለባዎች እየጸለይኩ ነው ያሉት ብጹእነታቸው፥ “በዚህ ከባድ ችግር ምክንያት ስቃይ ውስጥ የገቡ ሰዎችን በአንድነት መንፈስ መርዳት እንደሚቻል በመተማመን ያለኝን ቅርበት ላረጋግጥላቸው እፈልጋለሁ” ብለዋል።

ሰደድ እሳቱን ለመከላከል የተደረገው ጥረት
የሃገሪቱ የእሳት አደጋ ሠራተኞች በከፍተኛ ሁኔታ ሲቀጣጠል የነበረውን ሰደድ እሳት በቁጥጥር ስር ማዋል ችለዋል።

በቃጠሎው ወቅት ወደ 700 የሚጠጉ የእሳት አደጋ መከላከያ ሰራተኞች፣ 29 የእሳት አደጋ መከላከያ አውሮፕላኖች እና ሄሊኮፕተሮች፣ 190 የእሳት አደጋ መከላከያ መኪናዎች፣ የሃገሪቱ የጦር ኃይሎች እና በጎ ፈቃደኞች እሳቱን ለማጥፋት ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል።

ቀደም ሲል ግሪክ የአውሮፓ ህብረት የሲቪል ጥበቃ ሰራተኞችን ያንቀሳቀሰች ሲሆን፥ ወዲያውኑ ከጣሊያን፣ ከፈረንሳይ፣ ከቼክ ሪፐብሊክ እና ከሮማኒያ ተጨማሪ እርዳታ ደርሶላታል።

የአውሮፓ ህብረት የእሳት መከላከያ ጥረቶችን ይደግፋል
በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ የአውሮፓ ህብረት በአከባቢው እየጨመረ የመጣውን ሰደድ እሳት ለመዋጋት 12 አውሮፕላኖችን ማምረት መጀመሩን ያስታወቀ ሲሆን፥ ደቡባዊ አውሮፓ በከባዱ የበጋ ወራት በሰደድ እሳት በተደጋጋሚ እንደሚወድም እና የአየር ንብረት ለውጥ አደጋውን የበለጠ የከፋ ያደርገዋል ተብሎም ይጠበቃል።

የአውሮፓ የአደጋ ጊዜ አስተዳደር ኮሚሽነር እንዳሉት የሰደድ እሳት ወቅቶች እየረዘሙ በሄዱ ቁጥር፣ እንዲሁም አውዳሚ እና ሊተነበይ የማይቻልበት ጊዜ ላይ በደረሰበት ወቅት ህብረቱ የአውሮፓ ህብረትን የእሳት ማጥፊያ ተቋምን አቅም ለማጠናከር እየሰራ ነበር ብለዋል።

እነዚህ የሚመረቱት አውሮፕላኖች ክሮኤሺያ፣ ፈረንሳይ፣ ግሪክ፣ ጣሊያን፣ ፖርቱጋል እና ስፔን ላይ ይሆናሉ ተብሏል።

በሌላ ዜና፣ በሰርቢያ ከፍተኛ የሆነ የአየር ሙቀት የተከሰተ ሲሆን፥ የሙቀት መጠኑ እስከ ነሐሴ አጋማሽ ድረስ ከ35 እስከ 41 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ድረስ እንደሚጨምር ተነግሯል።
 

16 August 2024, 14:41