ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካ የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ ባደረጉበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካ የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ ባደረጉበት ወቅት  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ኢየሱስ ይጠበቀናል፣ ያውቀናል፣ ይወደናል አሉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ዘወትር እሁድ እለት በእለቱ በሚነበበው ቅዱስ ወንጌል ላይ ተንተርሰው አስተንትኖ እንደ ሚያደርጉ ይታወቃል። በእዚህ መሰረት ቅዱስነታቸው በሚያዝያ 17/2013 ዓ.ም ከቫቲካን ሆነው ያደረጉት አስተንትኖ በእለቱ ከዮሐንስ 10፡11-18 ላይ በተጠቀሰው የመልካሙ እረኛ ታሪክ በሚገልጸው በቅዱስ ወንጌል ክፍል ላይ መሰረቱን ያደረገ እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን ኢየሱስ እኛን ይጠብቀናል፣ ያውቀናል፣ ይወደናል ማለታቸው ተገልጿል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በወቅቱ ያደረጉትን አስተንትኖ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው አሰናድተነዋል፣ ተከታተሉን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

ዛሬ መልካም እረኛ እሁድ ተብሎ በሚጠራው በዚህ ፋሲካ በዓል በአራተኛው ሳምንት እሁድ ላይ (የጎርጎሮርሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የስርዓተ አምልኮ አቆጣጠር ደንብ መሰረት ማለት ነው) ከዮሐንስ ወንጌል 10:11-18 ተወስዶ የተነበበው ቃል ኢየሱስ በጎቹን የሚከላከል ፣ የሚያውቅና የሚወድ እውነተኛ እረኛ አድርጎ ያቀርባል።

“ቅጥረኛው” የመልካም እረኛ ተቃራኒ ነው ፣ በጎቹ የእርሱ ስላልሆኑ ብዙም ግድ አይለውም። እሱ የሚሠራው ለደመወዝ ብቻ ነው፣ እናም እነሱን ስለመከላከል አያሳስበውም፣ ተኩላ ሲመጣ ይሸሻል እና ብቻቸውንም ይተዋቸዋል (ዮሐ 10፡ 12-13)። በምትኩ ፣ እውነተኛው እረኛ የሆነው ኢየሱስ ሁል ጊዜ ይጠብቀናል እናም በየቀኑ እና በየጊዜው እርሱን ለማዳመጥ ከፈለግን ሁልጊዜ በምናገኘው በቃሉ ብርሃን እና በመገኘቱ ብርታት አማካኝነት ከብዙ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ፣ አደገኛ ሁኔታዎች ያድነናል።

ሁለተኛው ገጽታ መልካም እረኛ የሆነው ኢየሱስ እኛን ያውቀናል የሚለው ነው፣ የመጀመሪያው ገጽታ-በጎቹን ይከላከላል ከሚለው ገጽታ ቀጣይ ሲሆን ሁለተኛው ገጽታ ደግሞ - በጎቹን ያውቃል በጎቹም እርሱን ያውቁታል (ዮሐንስ 10፡14) የሚለው ነው። ኢየሱስ አንድ በአንድ እንደሚያውቀን፣ እኛ በእርሱ የምንታወቅ መሆናችን ፣ ስማችን በእርሱ ዘንድ የታወቀ መሆኑን ማወቁ ምንኛ ያጽናናል! እርሱ እኛን በጅምላ አይደለም የሚያውቀን። እያንዳዳችን ለየት ባለ ሁኔታ ነው የሚያውቀን፣ እያንዳንዳችንን ከነታሪካችን ነው የሚያውቀን፣ እያንዳንዳችንም በእርሱ ዘንድ ዋጋ አለን፣ ሁሉም በመፈጠራቸው ፈጣሪ እና በክርስቶስ ስለተዋጁ። እያንዳንዳችን ኢየሱስ ያውቀኛል ልንል እንችላለን! እያንዳንዳችን ኢየሱስ ያውቀናል! እውነት ነው ፣ እንደዚህ ነው እሱ እንደማንኛውም ሰው ሳይሆን የሚያውቀን ነገር ግን በልባችን ውስጥ ያለውን ፣ ዓላማችንን ፣ በጣም የተደበቀ ስሜታችንን የሚይውቀው እርሱ ብቻ ነው። ኢየሱስ የእኛን ጥንካሬዎች እና ጉድለቶች ያውቃል ፣ እናም እኛን ለመንከባከብ ፣ የስህተቶቻችንን ቁስሎች በምህረቱ ብዛት ለመፈወስ ሁል ጊዜ ዝግጁ ነው። ነቢያት የእግዚአብሔርን ህዝብ እረኛ በተመለከተ ያቀረቡት ምስል በእርሱ ሙሉ በሙሉ ተፈጽሟል-ኢየሱስ ስለ በጎቹ ያስባል ፣ ይሰበስባል ፣ ቁስላቸውን ያክማል፣ ህመሞቻቸውን ይፈውሳል። ይህንን በነቢዩ ሕዝቅኤል መጽሐፍ ውስጥ ማንበብ እንችላለን (ሕዝ 34 11-16)።

ስለዚህ ፣ ጥሩ እረኛ የሆነው ኢየሱስ በጎቹን ይጠብቃል ፣ ያውቃል ፣ እና ከሁሉም በላይ ይወዳል። ለዚህም ነው ነፍሱን ለእነሱ የሚሰጠው (ዮሐ. 10፡15)። ለበጎቹ ማለትም ለእያንዳንዳችን ያለው ፍቅር በመስቀል ላይ እንዲሞት አድርጎታል። ይህ የአብ ፈቃድ ነውና - ማንም እንዳይጠፋ ይፈልጋል። የክርስቶስ ፍቅር አግላይ የሆነ ፍቅር አይደለም፣ ሁሉንም ያቅፋል። እርሱ ራሱ በዛሬው ወንጌል ውስጥ ይህንን ያስታውሰናል “ከዚህ ጒረኖ ያልሆኑ ሌሎች በጎች አሉኝ፤ እነርሱንም ማምጣት አለብኝ። እነርሱም ድምፄን ይሰማሉ፤ አንድ መንጋም ይሆናሉ፤ እረኛውም አንድ” (ዮሐ 10፡16) ይለናል። እነዚህ ቃላት የእርሱን ሁለንተናዊ አሳቢነት ይመሰክራሉ እርሱ የሁሉም እረኛ ነው። ኢየሱስ እያንዳንዱ ሰው የአባቱን ፍቅር እንዲቀበል እና እግዚአብሔርን እንዲገናኝ ይፈልጋል።

እናም ቤተክርስቲያን ይህንን የክርስቶስ ተልእኮ እንድትወጣ ተጠርታለች። በቤተክርስቲያናችን ውስጥ ከሚሳተፉ ሰዎች ባሻገር በተወሰነ ጊዜ ብቻ ወይም በጭራሽ ቤተክርስቲያን ውስጥ የማይሳተፉ ብዙ ሰዎች አሉ። ነገር ግን ይህ ማለት እነሱ የእግዚአብሔር ልጆች አይደሉም ማለት አይደለም - አብ ለሁሉም ሰው መልካም እረኛ ለሆነው ለኢየሱስ ሁሉንም በአደራ ሰጥቷል።

ወንድሞች እና እህቶች ፣ ኢየሱስ እኛን ይጠብቀናል፣ ያውቀናል እንዲሁም ይወደናል። በተልእኮው ደስታ ውስጥ ለመተባበር መልካሙን እረኛ ለመቀበል እና ለመከተል እንችል ዘንድ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እኛን ትርዳን።

25 April 2021, 10:43

What is the Regina Coeli?

The antiphon Regina Coeli (“Queen of Heaven”) is one of four traditional Marian antiphons, the others being Alma Redemptoris Mater, Ave Regina Coelorum, and Salve Regina.

It was Pope Benedict XIV who, in 1742, enjoined the recitation of the Regina Coeli in place of the Angelus during Eastertide, that is, from Easter Sunday to the end of Pentecost. It is recited standing as a sign of Christ’s victory over death.

Like the Angelus, the Regina Coeli is said three times a day, at dawn, at noon, and at dusk, in order to consecrate the day to God and the Virgin Mary.

This ancient antiphon arose, according to a pious tradition, in the 6th century; it is attested in documentary sources from the first half of the 13th century, when it was inserted in the Franciscan breviary. It is composed of four short verses, each ending with an “alleluia.” With the Regina Coeli, the faithful turn to Mary, the Queen of Heaven, to rejoice with her at the Resurrection of Christ.

At the Regina Coeli on Easter Monday of 2015, Pope Francis spoke about the spiritual dispositions that should animate the faithful as they recite this Marian prayer:

“In this prayer, expressed by the Alleluia, we turn to Mary inviting her to rejoice, because the One whom she carried in her womb is Risen as He promised, and we entrust ourselves to her intercession. In fact, our joy is a reflection of Mary’s joy, for it is she who guarded and guards with faith the events of Jesus. Let us therefore recite this prayer with the emotion of children who are happy because their mother is happy.”

መልኣኩ ገብርኤል ማሪያምን አበሰራት የሚለው የቀርብ ጊዜ ጸሎት

ሁሉንም ያንብቡ >