ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ አንድ ቀን ሁላችንም ከክርስቶስ ጋር እንዋሃዳለን ማለታቸው ተገለጸ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ዘወትር እሁድ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለሚሰበሰቡ ምዕመናን በእለቱ ሥርዓተ አምልኮ ላይ በሚነበበው ቅዱስ ወንጌል ላይ ተንተርሰው አስተንትኖ እንደምያደርጉ የሚታወቅ ሲሆን በዚህም መሰረት ቅዱስነታቸው በህዳር 08/2017 ዓ.ም ያደረጉት አስተንትኖ "በዚያን ጊዜ፣ ከመከራው በኋላ ‘ፀሓይ ትጨልማለች፣ “ ‘ጨረቃም ብርሃኗን አትሰጥም፤ ከዋክብት ከሰማይ ይረግፋሉ፤ የሰማይ ኀይላትም ይናወጣሉ።’ “በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ በታላቅ ኀይልና ግርማ በደመና ሲመጣ ያዩታል። እርሱም መላእክቱን ልኮ ከአራቱ ነፋሳት፣ ከምድር ዳርቻ እስከ ሰማያት ዳርቻ ምርጦቹን ይሰበስባል። “ምሳሌውን ከበለስ ተማሩ፤ ቅርንጫፏ ሲለመልም፣ ቅጠሏ ሲያቈጠቍጥ በጋ እንደ ተቃረበ ታውቃላችሁ፤ እንዲሁ ደግሞ እነዚህ ነገሮች መፈጸማቸውን ስታዩ እንደ ቀረበ፣ በደጅም እንደ ሆነ ዕወቁ። እውነት እላችኋለሁ፣ እነዚህ ነገሮች እስከሚፈጸሙ ድረስ ይህ ትውልድ አያልፍም፤ ሰማይና ምድር ያልፋሉ፣ ቃሌ ግን አያልፍም" (ማርቆስ 13፡24-32) በሚለው የቅዱስ ወንጌል ክፍል ላይ ተንተርሰው ባደርጉት አስተንትኖ አንድ ቀን ሁላችንም ከክርስቶስ ጋር እንዋሃዳለን ማለታቸው ተገልጿል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በወቅቱ ያደርጉትን የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ ሙሉ ይዘቱን እንደሚከተለው አሰናድተነዋል፣ ተከታተሉን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

በዛሬው ሥርዓተ አምልኮ ሥነ-ሥረዓት ላይ የተነበበው ቅዱስ ወንጌል ኢየሱስ ታላቅ መከራን ሲገልጽ "ፀሐይ ይጨልማል ጨረቃም ብርሃኗን አትሰጥም" (ማር 13፡24) በማለት ይናገራል። ይህን ስቃይ ሲጋፈጡ ብዙዎች የዓለምን ፍጻሜ ሊያስቡ ይችላሉ፣ ነገር ግን ጌታ እድሉን ተጠቀመበት፣ “ሰማይና ምድር ያልፋሉ ቃሌ ግን አያልፍም” (ማር 13፡3) ሲል አረጋጧል።

ይህንን አገላለጽ ጠለቅ ብለን ልንመለከተው እንችላለን-ምን እንደሚያልፍ እና ምን እንደማያልፍ።

በመጀመሪያ ደረጃ ምን ያልፋል። በሕይወታችን ውስጥ በአንዳንድ ሁኔታዎች፣ ቀውስ ውስጥ ስናልፍ ወይም አንዳንድ ውድቀት ሲያጋጥመን፣ እንዲሁም በአካባቢያችን በጦርነት፣ በዓመፅ፣ በተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት የሚደርሰውን ሥቃይ ስናይ፣ ሁሉም ነገር ወደ ማብቂያው እየመጣ እንደሆነ ይሰማናል። እናም በጣም ቆንጆ ነገሮች እንኳን እንደሚያልፉ ይሰማናል። ቀውሶች እና ውድቀቶች ግን ምንም እንኳን የሚያምም ቢሆንም አስፈላጊ ናቸው፣ ምክንያቱም ሁሉም ነገር የሚገባውን ክብደት መያዝ እንዳለበት ያስተምረናል እንጂ ልባችንን ከዚህ አለም እውነታ ጋር እንዳይነጠል ያስተምሩናል፣ ምክንያቱም ያልፋሉ፡ ሊጠፉ ተወስነዋል።

በተመሳሳይ ጊዜ ኢየሱስ ስለማያልፈው ነገር ተናግሯል። ሁሉም ነገር ያልፋል፣ ግን ቃሉ አያልፍም፡ የኢየሱስ ቃላቶች ለዘለአለም ይኖራሉ። ስለዚህም የመዳንና የዘላለም ተስፋን በያዘው ወንጌል እንድናምን እንጂ በሞት ጭንቀት ውስጥ እንዳንኖር ይጋብዘናል። ሁሉ ሲያልፍ ክርስቶስ ይኖራልና። በእርሱ፣ በክርስቶስ፣ ያለፉትን እና በምድራዊ ህይወታችን አብረውን የሄዱትን ነገሮች እና ሰዎች አንድ ቀን እንደገና እናገኛለን። በዚህ የትንሣኤ ተስፋ ብርሃን እያንዳንዱ እውነታ አዲስ ትርጉም ይኖረዋል፡ ሁሉም ነገር ይሞታል እኛም አንድ ቀን እንሞታለን ነገር ግን ከገነባነው እና ከወደድነው ምንም አናጣም ምክንያቱም ሞት የአዲስ ሕይወት መጀመሪያ ይሆናልና።

ወንድሞችና እህቶች፣ በመከራ፣ በችግር፣ በውድቀት ውስጥም ቢሆን፣ ወንጌሉ ሕይወትንና ታሪክን እንድንመለከት ይጋብዘናል፣ ፍጻሜውን ላለማጣት ሳይሆን ለሚቀረው በደስታ ነው። እግዚአብሔር የወደፊት ሕይወትንና ደስታን እያዘጋጀልን መሆኑን አንዘንጋ።

እናም፣ እራሳችንን እንጠይቅ፡ ከሚያልፉ፣ በፍጥነት ከሚያልፉ ምድራዊ ነገሮች ጋር ተጣብቀናል ወይንስ የሚኖ እና ወደ ዘላለማዊነት ከሚመሩን የጌታ ቃላት ጋር ተያይዘናል? እባካችሁ ይህንን ጥያቄ እራሳችንን እንጠይቅ። ይጠቅመናል።

ስለ እኛ ትማልድን ዘንድ ራሷን ሙሉ በሙሉ ለእግዚአብሔር ቃል የሰጠችውን ቅድስት ድንግል ማርያም በአማላጅነቷ ትርዳን።

18 November 2024, 09:51

የገብርኤል ብሥራት ጥንታዊ መሠርት የያዘና የጌታችን እየሱስ ክርስቶስን ሰው መሆን በማስታወስ በቀን ሦስት ጊዜ ማለትም በንጋት (በአስራሁለት ሰዓት) በቀትር (በስድስት ሰዓት) እንዲሁም በማታ (በአስራሁለት ሰዓት) የሚደገም የጸሎት ዓይነት ሲሆን ጸሎቱ በሚደገምበት ሰዓት ቤተ ክርስቲያንም የመልኣከ እግዚኣብሔርን ደወል በዚሁ ሰዓት ትደውላለች። ይህ ጸሎት መልኣከ እግዚኣብሔር የሚለውን ስያሜ ያገኝው ከጸሎቱ ከመጀመሪያ ስንኝ የእግዚኣብሔር መልኣከ ማርያምን አበሠራት ከሚለው የተወሰደ ሲሆን ጸሎቱ ስለ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ሰው መሆን ይናገራል። ጸሎቱ በሦስት የተከፈሉ አጫጭር ስንኞች ሲኖሩት በእነኚህ በሦስት አጫጭር ስንኞች መሓል ጸጋን የተሞላሽ የሚለው የማርያም ጸሎት ይደገማል። ይህ ጸሎት በሰንበትና በበዓላት ዕለት ልክ በእኩለ ቀን ላይ በዕለቱ ወንጌል ላይ ትንሽ አስተምሮና ገለፃ ከሰጡ በኋላ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በቅዱስ ጴጥሮስ ኣደባባይ ላይ ይህንን ጸሎት ይመራሉ። በመቀጠልም በአደባባዩ ላይ የተገኝው ከተለያየ ቦታ ለንግደት የመጣውን ሕዝብ ሰላምታ ይሰጣሉ።በየትኛውም ጊዜ ከበዓለ ፋሲካ እስከ በዓለ ጰራቅሊጦስ በመልኣከ እግዚኣብሔር ጸሎት ፈንታ የጌታችን እየሱስ ክርስቶስን ትንሣኤ የሚዘክረውን “የሰማይ ንግሥት ሆይ ደስ ይበልሽ” የሚለው ጸሎት የሚደገም ሲሆን በመሓል በመሓሉ ጸጋን የተሞላሽ ማርያም ሆይ የሚለው ጸሎት ይታከልበታል።

መልኣኩ ገብርኤል ማሪያምን አበሰራት የሚለው የቀርብ ጊዜ ጸሎት

ሁሉንም ያንብቡ >